የእስራኤል እና ሐማስ ግጭት የነዳጅ ዋጋን እንዳያሻቅበው ተሰግቷል

9 ጥቅምት 2023, 08:16 EAT በእስራኤል እና ጋዛ ያለው ሁኔታ ከመካከለኛው ምስራቅ የሚነሳውን የነዳጅ አቅርቦት ሊያስተጓጉል ይችላል በሚል ስጋት ዛሬ ሰኞ የነዳጅ ዋጋ በ4 በመቶ አሻቅቧል። የአሜሪካን የነዳጅ ዋጋ ማሳያ ተደርጎ የሚወሰደው ዌስት ቴክሳስ ኢንተርሚዲየት የተሰኘው ተቋም የነዳጅ ዋጋን ወደ 86 ዶላር ከፍ አድርጓል። የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋም በእስያ ገበያ ጨምሯል። እስራኤልና ፍልስጤም ነዳጅ ላኪ ባይሆኑም […]

የሐማስን ጥቃት ተከትሎ አሜሪካ የጦር መርከቦቿን ወደ እስራኤል አስጠጋች

9 ጥቅምት 2023, 08:10 EAT አሜሪካ የአውሮፕላን ተሸካሚዎችን፣ የጦር መርከቦችን እና ጄቶች ወደ ምሥራቃዊ ሜዲትራኒያን ባህር እያስጠጋች መሆኑን ገለጠች። ለእስራኤል ተጨማሪ መሳሪያዎችን እና ጥይቶችን እንደምትሰጥም አስታውቃለች። አሜሪካ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው ሐማስ በደቡብ እስራኤል ላይ ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ሲሆን ፕሬዝዳንት ባይደን ጥቃቱን “ከዚህ በፊት ታይቶ የማያውቅና አሰቃቂ” ሲሉ ጠርተውታል። አሜሪካ ዜጎቿ ስለመገደላቸው እና በምርኮ ከተወሰዱት […]

ኮሚሽኑ የዕርዳታ ሥርጭትን የሚያስተጓጉል የፀጥታ ችግር እንዳልገጠመው ተናገረ

October 9, 2023 – EthiopianReporter.com  ዜና ኮሚሽኑ የዕርዳታ ሥርጭትን የሚያስተጓጉል የፀጥታ ችግር እንዳልገጠመው ተናገረ ዮናስ አማረ ቀን: October 8, 2023 የብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በአማራ ክልል ለድርቅ ተጎጂዎች የሚያደርገው የዕለት ደራሽ ዕርዳታ አቅርቦትን የሚያውክ የፀጥታ ችግር እስካሁን እንዳልገጠመው አስታወቀ፡፡ ባለፈው ሳምንት አማራ ክልልን ጨምሮ በድርቅ ወደ ተጎዱ ሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች የዕርዳታ ማሠራጨት ሥራ መጀመሩን ኮሚሽኑ […]

ዓለም አቀፍ ኢንዱስትሪዎችንና አዳዲስ ድርጅቶችን ያገናኛል የተባለው ጉባዔ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

October 9, 2023 – EthiopianReporter.com  ዓለም አቀፍ ኢንዱስትሪዎችንና አዳዲስ ድርጅቶችን ያገናኛል የተባለው ጉባዔ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው ዓለም አቀፍ ኢንዱስትሪዎችንና አዳዲስ የሥራ ሐሳቦች ያሏቸውን ዜጎች በአንድ መድረክ ያገናኛል የተባለው ‹‹እንቆጳ ጉባዔ››፣ የፊታችን ጥቅምት 1 እና 2 ቀን 2016 ዓ.ም. በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በዲጂታል ኢንተርፕርነርሽፕ፣ በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሥራ ፈጠራ…

በሽንኩርት ነጋዴዎች ላይ የእስር ዕርምጃ የወሰደው ሐረሪ ክልል በዳቦ ነጋዴዎች ላይም እቀጥላለሁ አለ

October 9, 2023 – EthiopianReporter.com  በሽንኩርት ነጋዴዎች ላይ የእስር ዕርምጃ የወሰደው ሐረሪ ክልል በዳቦ ነጋዴዎች ላይም እቀጥላለሁ አለ የሽንኩርት ዋጋን ያለቅጥ አንረዋል ባላቸው የሐረር ከተማ ነጋዴዎች ላይ የእስር ዕርምጃ የወሰደው የሐረሪ ክልል ንግድ ልማት ኤጀንሲ፣ በዳቦ ነጋዴዎችም ላይ ተመሳሳይ ዕርምጃ እንደሚወስድ አስጠነቀቀ፡፡ የሽንኩርት ዋጋን ያላግባብ ያስወድዳሉ ያላቸውን ሦስት ዋና ዋና ነጋዴዎችን ጨምሮ 17…

የሲቪክ ድርጅቶችና ዩኒቨርሲቲዎች ለዴሞክራሲና ሰብዓዊ መብቶች መከበር በጋራ እንዲሠሩ ጥሪ ቀረበ

October 9, 2023 – EthiopianReporter.com  ዜና የሲቪክ ድርጅቶችና ዩኒቨርሲቲዎች ለዴሞክራሲና ሰብዓዊ መብቶች መከበር በጋራ እንዲሠሩ ጥሪ ቀረበ ሲሳይ ሳህሉ ቀን: October 8, 2023 የሰቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ከሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር ያላቸውን ግንኙነት በማሻሻል፣ ለዴሞክራሲ ሥርዓት መዳበርና ለሰብዓዊ መብቶች መከበር በጋራ እንዲሠሩ ጥሪ ቀረበ፡፡ በኢትዮጵያ በመማር ማስተማር ላይ የሚንቀሳቀሱ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከሲቪክ ማኅበረሰብ […]

የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ራሱን ለዓለም አቀፍ ባለሀብቶች ለማስተዋወቅ ወደ ለንደን አቀና

October 9, 2023 – EthiopianReporter.com  በዮሐንስ አንበርብር October 8, 2023 የሰነዶች ሙዓለ ንዋይ ገበያ አክሲዮን ማኅበር በተመሰረተበት ወቅት የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ (Ethiopian Securities Exchange (ESX) ዓለም አቀፍ ባለሀብቶችን ለመሳብና የኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ ለማስተዋወቅ፣ የመጀመሪያ የውጭ ጉዞውን ወደ እንግሊዝ ለንደን ከተማ አደረገ። በዚሁ መሠረት ሰኞ መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም. በለንድን ከተማ ራሱን ማስተዋወቂያ ትዕይንት የሚያካሂድ […]

የህንዱ ሥጋ ላኪ ኩባንያ የአስመጪነት ፈቃድ ካልተሰጠው ሥራውን ሙሉ በሙሉ እንደሚያቆም አስታወቀ

October 9, 2023 – EthiopianReporter.com  የህንዱ ሥጋ ላኪ ኩባንያ የአስመጪነት ፈቃድ ካልተሰጠው ሥራውን ሙሉ በሙሉ እንደሚያቆም አስታወቀ በኢትዮጵያ ሁለት ድርጅቶችን የሚያንቀሳቅሰው የህንዱ ግዙፍ ሥጋ አምራች የሆነው አላና ግሩፕ፣ ሥጋ ወደ ውጭ ልኮ በሚያገኘው የውጭ ምንዛሪ የአስመጪነት (ኢምፖርት) ሥራ ለማከናወን የሚያስችለውን ፈቃድ ካላገኘ ሥራውን ሙሉ ለሙሉ እንደሚያቆም አስታወቀ፡፡ የግሩፑ አካል የሆነው አክሸከር ኢትዮጵያ…

የአፍሪካ መሪዎች በእሥራዔል-ጋዛ ጦርነት ዙሪያ አስተያየታቸውን እየሰጡ ነው

October 9, 2023 – VOA Amharic  የሃማስ ታጣቂ ቡድን በእሥራዔል ላይ የፈፀመውን ድንገተኛ ጥቃት ተከትሎ የእስራኤል መንግሥት በይፋ ጦርነት ካወጀ በኋላ፣ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች አስተያየታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ። በእሥራዔል እና በሃማስ ታጣቂዎች መካከል ጋዛ ላይ በታወጀው ጦርነት ዙሪያ አስተያየታቸውን ከሰጡ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች መካከል፣ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር የሆኑት ሙሣ ፋኪ ማሃማት “የእሥራዔል-ፍልስጥዔ… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ […]

ሐማስ ማነው? በጋዛ ሰርጥስ ምን ተፈጠረ? ሊያውቋቸው የሚገቡ ወሳኝ ጥያቄዎች

ከ 1 ሰአት በፊት የፍልስጥኤሙ ታጣቂ ቡድን ሐማስ ታይቶ የማይታወቅ የተባለለትን የተቀናጀ ጥቃት እስራኤል ላይ ሰንዝሯል። ተዋጊዎቹም በጋዛ ሰርጥ አቅራቢያ የሚገኙ ነዋሪዎችን ገድለዋል፣ አግተዋል። ስለተሳታፊዎቹ እና ስለጥቃቱ ቦታዎች ማወቅ ያለብዎት ነገር ወሳኝ መረጃዎችን እንደሚከተለው አጠናቅረናል። ሐማስ ማን ነው? ሃማስ የጋዛን ሰርጥ የሚያስተዳድር የፍልስጥኤም እስላማዊ ታጣቂ ቡድን ነው። ሃማስ እስራኤልን ለማጥፋት ቃል የገባ ሲሆን በአውሮፓውያኑ 2007 […]