አሜሪካ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ያለው ኹኔታ እንዳሳሰባት ገለጸች
September 29, 2023 አሜሪካ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ያለው ኹኔታ እንዳሳሰባት ገለጸች አርብ መስከረም 18 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) አሜሪካ በኢትዮጵያ የአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ያለው ግጭት መባባስ እንዳሳሰባት በመግለጽ፤ ግጭቱ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈለግለትና በፖለቲካዊ ንግግር እንዲፈታ እንደምትፈልግ አስታውቃለች። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሃላፊ አንቶኒ ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በስልክ መነጋገራቸውን የአሜሪካ የውጪ […]
በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ሁኔታ እያሽቆለቆለ መምጣቱ እንዳሳሰበው የተባበሩት መንግስታት ገለፀ
September 29, 2023 በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ሁኔታ እያሽቆለቆለ መምጣቱ እንዳሳሰበው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽ ገለፀ ኮሚሽኑ ዛሬ ከጀኔቫ ባወጣው መግለጫ በአንዳንድ የኢትዮጵያ ክልሎች ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት መባባሱ በጣም ያሳስበናል ብሏል። በአማራ ክልል በኢትዮጵያ ወታደሮች እና በክልሉ ፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተቀሰቀሰውን ግጭት እና በጎርጎሪያኑ ነሃሴ 4 ቀን የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ […]
በኦሮሚያ ክልል በመንግስት የጸጥታ አካላትና በታጠቁ ኃይሎች በንጹሃን ላይየሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ተፈጸሙ
September 29, 2023 – Konjit Sitotaw በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በመንግስት የጸጥታ አካላትና በታጠቁ ኃይሎች በንጹሃን ላይ እየተፈጸሙ ያሉ ዘርፈ ብዙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች መንግስት በአስቸኳይ እንዲያስቆም ኢሰመጉ ጠየቀ። የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ትናንት ባወጣው መግለጫ መንግስት በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች እየተፈጸሙ ላሉት የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በቂ ትኩረት አለመስጠቱን ገልጿል። ኢሰመጉ በመግለጫው እንዳመለከተው በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ […]
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አገልጋይ ካህናት እና ምዕመናን በኦሮሞ ነፃ አውጪ ሠራዊት ታረዱ
September 29, 2023 ዜና ሰማእታት…! (ዘመድኩን በቀለ) “…መስከረም 15/2016 ዓም በኦሮምያ ክልል በአርሲ ሀገረ ስብከት በሆንቆሎ ወረዳ ቤተ ክህነት ቦሌ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ዕጣ የወደቀባቸው ምስኪን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አገልጋይ ካህናት እና ምዕመናን የኢሬቻ በዓል ከመከበሩ በፊት በኦሮሞ ነፃ አውጪ ሠራዊት የታረዱት የሚከተሉት ናቸው። https://t.me/ZemedkunBekeleZ/22998 “…የካህኑ ሚስትና ልጅ፣ መ/ር ዳዊት ጌታቸው፣ አበጀ ከበደ፣ ሞገስ […]
ባለመረጋጋት እና በጫና ምክንያት የፍኖተ ሰላም ሆስፒታል ሥራ ማቆሙን ባለሙያዎች ተናገሩ
29 መስከረም 2023, 07:53 EAT የአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ፍኖተ ሰላም በተደጋጋሚ በነበረ ግጭት፣ ባለመረጋጋቱ እና ባለሙያዎች ደረሰብን ባሉት ጫና ምክንያት በከተማዋ ያለ ሆስፒታል ሥራ ማቆሙ ተነገረ። ባለፉት ሳምንታት በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በክልሉ ተባብሶ በቀጠለው ግጭት ምክንያት፣ በተለያዩ አካባቢዎች የሕክምና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ላይ ጫና መፈጠሩን ባለሙያዎች ለቢቢሲ […]
ተመራማሪዎች የስድስት ሺህ ዓመታት ዕድሜ አለው የተባለ ጥንታዊ ጫማ አገኘን አሉ
29 መስከረም 2023, 16:08 EAT ከሳር ተሰርቶ ስድስት ሺህ ዓመታት ገደማ ዕድሜ አለው ተብሎ የተገመተ ጥንታዊ ጫማን በስፔን በአንድ ዋሻ ውስጥ ማግኘቱን ተመራማሪዎች አስታወቁ። በአውሮፓ ውስጥ ከተገኙ ቀደምት ጫማዎች መካከል በእድሜ ቀዳሚ ነው የተባለው ይህ ጫማ ስፔን ውስጥ በሚገኝ የሌሊት ወፎች ዋሻ ውስጥ ነው የተገኘው። በ19ኛው ክፍለ ዘመን በማዕድን አውጪዎች ተዘርፏ ከተባለው ዋሻ ውስጥ በርካታ […]
የመጀመሪያው ጥቁር የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስትር የአፍሪቃ ጉብኝት
September 29, 2023 – VOA Amharic ሎይድ ኦስቲን፣ የመከላከያ ሚኒስትር ከኾኑ በኋላ የመጀመሪያቸው የኾነውን የአፍሪቃ ጉብኝት አጠናቀው፣ ዛሬ ኀሙስ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ተመልሰዋል። ከመከላካከያ ሚኒስትሩ ጋራ የተጓዘችው የአሜሪካ ድምጿ የፔንታጎን ዘጋቢ ካርላ ባብ፣ ጉዟቸውን አስመልክቶ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። … … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
“የራሴን የማራቶን ክብረ ወሰን ደግሜ የማሻሻል ዕቅድ አለኝ” አትሌት ትዕግሥት አሰፋ
ከ 4 ሰአት በፊት አትሌት ትዕግሥት አሰፋ ተወልዳ ያደገችው ከአዲስ አበባ ጥቂት ኪሎ ሜትሮች በምትርቀው ሆለታ ነው። ስድስት ልጆችን ለታደለው ቤተሰብ እርሷ የመጨረሻ ልጅ ናት። ሆለታ ውስጥ አራዳ ምሥራቅ ሜዳ በሚባል ትምህርት ቤት የተማረችው ትዕግሥት፣ በትምህርት ቤት በሚደረግ ውድድር ነበር ወደ አትሌቲክሱ የገባችው። በሩጫው 400 ሜትር፣ 800 ሜትር እንዲሁም ግማሽ ማራቶን ሮጣለች። አገሯን በአፍሪካ ሻምፒዮና፣ […]
በአየርላንድ የጂምናስቲክ ውድድር ተለይታ ሜዳሊያ ያልተሰጣት ጥቁር ታዳጊ ጉዳይ ውዝግብ አስነሳ
ከ 1 ሰአት በፊት በአየርላንድ የጂምናስቲክ ውድድር ከሁሉም ነጮች ተለይታ ሜዳሊያ ያልተሰጣት የ10 ዓመት ጥቁር ታዳጊ ጉዳይ ውዝግብ አስነሳ። ባለፈው ዓመት በደብሊን በተካሄደ ዝግጅት ላይ አንዲት ባለስልጣን ለሁሉም ተሳታፊዎች ሜዳሊያ ካደሉ በኋላ ጥቁር ታዳጊዋን አልፈው ሲሄዱ የሚያሳይ ቪዲዮ በቅርቡ ወጥቷል። በርካቶች ይህ ፍጹም ዘረኝነት ነው ሲሉም ድርጊቱን አውግዘውታል። ጉዳዩን አስመልክቶ የአየርላንድ ጂምናስቲክ ለቤተሰቦቿ ይቅርታ የጠየቀ […]
በስዊድን የወሮበላ ቡድኖች ጥቃት በመጨመሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጦር አዛዡ ጋር ሊመክሩ ነው
ከ 4 ሰአት በፊት በስዊድን የወሮበላ ቡድኖች የሚያደርሱት ጥቃት እየጨመረ መሄዱን ተከትሎ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከጦር አዛዣቸው ጋር ለመነጋገር ጠርተዋቸዋል። ምክክራቸውም የጦር ኃይሉ እነዚህን ጥቃቶች ለመቀነስ እንዴት ሊያግዝ ይችላል በሚለው ላይ ያተኩራል። በጠቅላይ ሚኒስትሩና በጦር ኃይሉ መሪ ምክክሩ ላይ የፖሊስ አዛዡም የሚሳተፉ ሲሆን የጦር ኃይሉ ምን አይነት ተሳትፎ ሊኖር ይችላል በሚለው ጉዳይ ላይ ይመክራሉ። በስዊድን […]
