አሜሪካ የቻይናው ፕሬዚዳንት በፑቲን ላይ ጫና እንዲያደርጉ ጠየቀች
March 21, 2023 – BBC Amharic 21 መጋቢት 2023, 07:56 EAT አሜሪካ የሩሲያ ወታደሮች በዩክሬን እየፈጸሙት ያለውን “የጦር ወንጀል” እንዲያቆሙ የቻይናው ፕሬዚዳንት በቭላድሚር ፑቲን ላይ ጫና እንዲያደርጉ ጠየቀች። አሜሪካ ይህንን ያለችው የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ከጦርነቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሞስኮ ማቅናታቸውን ተከትሎ ነው። ፕሬዚዳንት ፑቲን እና አቻቸው ዢ ጂንፒንግ ዛሬ መጋቢት 12፣ 2015 ዓ.ም እንደገና ተገናኝተው […]
ትራምፕ ሊታሰሩ ይችሉበታል በተባለው ቀን የአሜሪካ ፖሊስ በተጠንቀቅ ላይ ይገኛል
March 21, 2023 – BBC Amharic 21 መጋቢት 2023, 08:23 EAT የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እየተደረገባቸው ካለው ምርመራ ጋር ተያይዞ በዚህ ሳምንት የሚታሰሩ ከሆነ ሊፈጠር የሚችለውን አለመረጋጋት ለመቆጣጠር በተለያዩ ከተሞች የአሜሪካ ፖሊስ ዝግጅቱን እያደረገ መሆኑ ተሰምቷል። ባለስልጣናት በኒውዮርክ፣ ዋሽንግተን ዲሲና ሎሰአንጀሎስ ከተሞች የተሰማራው የፖሊስ ሃይልን አጠናክረዋል። የማንሃታን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ትራምፕ ከአንዲት የወሲብ ፊልም ተዋናይት ጋር […]
በአፈናና ድብደባ ኢትዮጵያዊነትን ከኢትዮጵያውያን ውስጥ ማውጣት አይቻልም!
March 21, 2023 አገር ጭንቅ ላይ ብትሆንም ብዙ ምሁራን ችግር ያለ እስከማይመስል ድረስ ዝምታን የመረጡ ቢሆንም ኢትዮጵያዊነት እንዲጎለበት በተረዱትና በሚመስላቸው መልኩ የቻሉትን እያደረጉ ካሉ ጥቂት ምሁራን ውስጥ አንዱ የሆነው የታሪክ መምህሩና ተመራማሪው ታዬ ቦጋለ መጋቢት 8/2015 ዓ.ም ባልታወቁ ሰዎች ታፍኖ ከተወሰደ በኋላ ድብደባ ተፈጽሞበታል ተለቋል። በተመሳሳይ ሁኔታ የየኛ ቲቪ ጋዜጠኛ የሆነው አቶ ንጉሴ ብርሃኑ ማንነታቸዉ […]
በመቀሌ የትግራይ መከላከያ ሰራዊት አባላት ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ
March 21, 2023 – Konjit Sitotaw ስልጣን ከእጃቸው የወጣ ሰዎች በተለይ አድዋዎች ያስተባበሩት ሰልፍ ነው ተብሎለታል። በመቀሌና በኩሓ አከባቢ የሚገኙ ሕወሓት ባለፉት ሁለት አመታት በጦርነቱ ያሰማራቸው የትግራይ መከላከያ ሰራዊት አባላት ተብለው የተገለፁ የሕወሓት ወታደሮች መቀሌና ኩሓ አከባቢ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸው ተሰማ ። እነዚህ በጦርነቱ የተሳተፉ ከመቀሌ እንደስላልሴ እስከ ኩሓ በሚወስደው መንገድ ላይ ሰልፉ የተደረገ ሲሆን የጸጥ […]
የኢትዮጵያ መንግሥት በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የቀረበበትን ክስ በፍፁም እንደማይቀበለው አስታወቀ
March 21, 2023 የኢትዮጵያ መንግሥት በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የቀረበበትን የሰብአዊ መብት ጥሰት ክስ በፍፁም እንደማይቀበለው አስታወቀ መግለጫው በአገሪቱ አንድን ወገን በሌላኛው ላይ ለማነሣሣት ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል ቆስቋሽ መግለጫ ነው ብሎታል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በሰሜን ኢትዮጵያ በተፈጠረው ጦርነት ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተከስቷል ሲል የደረሰበትን ድምዳሜ የኢትዮጵያ መንግሥት በፍፁም እንደማይቀበለው የውጭ […]
ባጃጆች ወደ ሥራ የተመለሱ ቢሆንም ወከባና እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑን ገለጹ
March 21, 2023 በአዲስ አበባ ታግዶ የነበረው የባጃጅ ትራንስፖርት ተፈቅዶ ወደ ሥራ የተመለሱ የባጃጅ ባለንብረቶች፣ ከፍተኛ ወከባና እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡ ባለንብረቶቹ ከተማ አስተዳደሩ እግዱን አንስቻለሁ ካለ በኋላ በየአካባቢው የሚገኙ ፖሊሶች ሥራችንን በነጻነት ተንቀሳቅሰን እንዳንሠራ እንቅፋት ሆነውብናል ብለዋል፡፡ አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው ባለንብረቶች፣ ወደ ሥራ ተመልሰው ከወጡ በኋላ በሚደርስባቸው እንግልት ሥራ ለማቋረጥ ተገደዋል፡፡ ፖሊሶች […]
ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው ጃራ አካባቢ የተጠለሉ ወገኖች አቤቱታ
March 21, 2023 – DW Amharic ከኦሮሚያ ክልል ወለጋ ዞኖች በየአካባቢዎች በነበሩ ግጭቶች ምክንያት በተለያዩ ጊዜዎች ተፈናቅለው በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ጃራ የመጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች በቂ ድጋፍ አላገኘንም አሉ። የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት ችግሩ መኖሩን አረጋግጧል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
ታዋቂው የብዝሃ ሕይወት ሳይንስቲስት ሎሬት ዶ/ር ተወልደ ብርሃን ገብረእግዚአብሄር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
March 21, 2023 ታዋቂው የብዝሃ ሕይወት ሳይንስቲስት ሎሬት ዶ/ር ተወልደ ብርሃን ገብረእግዚአብሄር ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷል። ሎሬት ዶ/ር ተወልደ ብርሃን ባደረባቸው ሕመም በአገር ውስጥ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በ83 ዓመታቸው ትናንት ሰኞ መጋቢት 11/2015 ለማክሰኞ አጥቢያ 9፡00 ላይ በሞት መለየታቸውን ደራሲ እና ጋዜጠኛው ዘነበ ወላ አስታውቋል። ዶክተር ተወል ደብርሃን በአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ አገልግሎት የተከበረ ሥም […]
ዘመነን ፍቱት – መስከረም አበራ
March 21, 2023 የአማራ ህዝብ ላይ የሚወርደውን ዘር ተኮር ጭፍጨፋ እና ከጭፍጨፋው ቀጥሎ ያለው የሁሉ ሰው ዝምታ(በተለይ የአማራው የራሱ ዝምታ በታሪክ የምናፍርበት ነው)፣የፌደራል/ክልል መንግስታት ምንም እንዳልተፈጠረ ባሸበረቀ ፓርክ ላይ የንጉስ ራት እየበሉ ስብሰባ መክፈት መዝጋት በኢትዮጵያ ላይ ብቻ የሚከናወን “አስደናቂ” ነገር ይመስለኛል። ይህን አስመልክቶ ስለሚያልቀው ንፁህ አማራ ነፍስ የምንሞግት ጥቂት ድምፆች ስማችን “ህዝብ ለህዝብ በሰላም […]
ኬንያ፤ የኑሮ ዉድነት ያስነሳዉ ተቃዉሞ
March 21, 2023 – DW Amharic የኬንያ ፖሊስ በሃገሪቱ የሚታየዉን የኑሮ ዉድነት በመቃወም በተጠራ ሰልፍ ቢያንስ አንድ ሰዉ ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት መገደሉ ተሰማ ። ፖሊስ ሰልፉን በአስለቃሽ ጢስ እና ዉኃ በመርጨት በትኗል። ኦዲንጋ የኑሮ ዉድነትና፤ «በተሰረቀ የምርጫ ዉጤት» ስልጣን ላይ የሚገኙትን ፕሬዚዳንት ሩቶን በመቃወም ዜጎች ተቃዉሞዋቸዉን እንዲቀጥሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ