ሞሮኮ የ2030 የዓለም ዋንጫን ለማዘጋጀት ጥያቄ አቀረበች
March 15, 2023 – BBC Amharic ከ 3 ሰአት በፊት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2030 የሚካሄድን የዓለም ዋንጫ ለማዘጋጀት ሞሮኮ ትላንት በይፋ ጥያቄዋን አቀረበች። ጥያቄዋን ለፊፋ በይፋ ያረበችው ሞሮኮ የዓለም ትልቁን የእግር ኳስ ሁነት የምታዘጋጅ ሁለተኛዋ የአፍሪካ ሀገር ለመሆን ተስፋ አድርጋለች። ሞሮኮ ውድድሩን ለማዘጋጀት ጥያቄ ስታቅብ ይህ ለስድስተኛ ጊዜ ነው። ሞሮኮ ወድድሩን ለማዘጋት ያላት ፍላጎት ሩዋንዳ በተካሄደ ሥነ-ስርዓት […]
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ጉብኝት
March 15, 2023 – DW Amharic የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፣ ከዛሬ መጋቢት አምስት እስከ መጋቢት ስምንት ቀን 2015 ድረስ ወደ ኢትዮጵያና ኒጀር እንደሚያቀኑ መስሪያ ቤታቸው ያወጣው መግለጫ ያመለክታል። አንቶኒ ብሊንከን፣ በአዲስ አበባ በሚያደርጉት ጉብኝት በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭትን ለማስቆም የተደረሰው የሰላም ስምምነት አተገባበር እና የሽግግር ፍትህ ጉዳይ ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ ተገልጿል። የኢትዮጵያንና የአሜሪካን ፖለቲካዊ ጉዳዮች በቅርበት […]
ከብሊንከን አጀንዳ አንደኛው የትህነግ(ሕወሓት) ከሽብርተኝነት መዝገብ መነሳት ነው።
March 15, 2023 – Getachew Shiferaw ትህነግ ከሽብርተኝነት መዝገብ መነሳት የለበትም! ብሊንከን ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ የትህነግንና የፌደራል “መንግስት” አመራሮች አግኝቶ እንደሚያወያይ ይጠበቃል። አጀንዳ ይሆናሉ ከተባሉት መካከል አንደኛው የትህነግ ከሽብርተኝነት መዝገብ መነሳት ነው። ነገር ግን ይህ ጉዳይ ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል። 1) አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የፀጥታ ተቋማትን መረጃ ተጠቅሞ በሚመስል በተደራጀ መልኩ ባጋራው መረጃ እንዳስረዳው 7000 ያህል የትህነግ ነፍሰ […]
በኤርትራ ወታደሮች አድዋ በማርያም ሸዊቶ መንደር በትንሹ 300 ሰዎች መገደላቸዉን አንዲት እናት ተናገሩ።
March 15, 2023 – DW Amharic የኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)የሰላም ስምምነት ከመፈራረማቸው ከሳምንት በፊት የኤርትራ ወታደሮች አድዋ አካባቢ በምትገኘው በማርያም ሸዊቶ መንደር በትንሹ 300 ሰዎች መገደላቸዉን አንዲት የመንደርዋ ነዋሪ ተናገሩ። በዚች ትንሽ መንደር የሚኖሩት የ63 ዓመቷ አዛውንት ወ/ሮ አብረኸት ሀጎስ በወቅቱ ስለነበረው ሁኔታ እንዲሁም በቤተሰባቸው ላይ ስለደረሰባቸው ጥቃት ለዶቼ ቬሌ የእንሊዘኛ ክፍል በምስል […]
የአንቶኒ ብሊንከን የኢትዮጵያ ጉብኝትና አንደምታዉ
March 14, 2023 – DW Amharic “ኢትዮጵያ ውስጥ እየሆነ ያለውን፣በጸጥታውም አካባቢ ያለውን ሁኔታ ለመገምገም እና የትግራዩን ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያውያን በንፁሃን ዜጎች ላይ እየተወሰደ ያለው የጅምላ ጥቃትና ጭፍጨፋ ዘርን መሰረት ያደረገ ጨፍጨፋ፣ ለማስቆም መንግስት ላይ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ይመስለኛል።”… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
በጣና ሐይቅ ህገወጥ ዓሳ ማስገር የደቀነዉ አደጋ
March 14, 2023 – DW Amharic ህገወጥ የዓሳ ማስገር ሀብቱን እያመናመነው መሆኑን የጣና ሐይቅ አካባቢ ነዋሪዎችና ባለሙያዎች ተናገሩ፡፡ ያልተፈቀዱ የዓሳ ማስገሪያ መሳሪያዎችን መጠቀምና ወቅቱን ያልጠበቀ ማስገር ዋናዎቹ የችግሩ ምንጮች ናቸውም ተብሏል፡፡ በጣና ሐይቅ ላይ ብቻ ከ5000 በላይ አስጋሪዎች እንዳሉ የአማራ ክልል የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ጽ/ቤት አመልክቷል፡፡… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
የቻይናው ሺ ከሳዑዲ እና ኢራን ሥምምነት በኋላ በዓለም ትልቁን ድርሻ ይፈልጋሉ
ማርች 13, 2023 ቪኦኤ ዜና የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ፣ ቤጂንግ ሳኡዲ አረብያ እና ኢራን የተቋረጠ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለመቀጠል የተስማሙበትን ንግግር በማስተናገድ የዲፕሎማቲክ ድል ከተቀዳጀች በኋላ ቻይና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ትልቅ ሚና እንድትጫወት ጥሪ አድርገዋል፡፡ ሺ ይህን የተናገሩት ኢኮኖሚውንና ማኅበረሰቡን ለመቆጣጠር የሚያስችላቸውን የታማኞች መንግሥት የመሰረቱበትን የህግ አውጭዎች ስብሰባ ካካሄዱ በኋላ መሆኑን የአሶሴይትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል፡፡ […]
* ወልደሕይወት – የ17ኛው ክፍለ ዘመን ፈላስፋ፤
* ወልደሕይወት – የ17ኛው ክፍለ ዘመን ፈላስፋ፤ አገራት በተለያዩና ባፈሯቸው ሀብቶች (ተፈጥሯዊም ይሁን ሰው ሠራሽ) ይታወቃሉ። ዜጎቻቸው በሠሯቸው ሥራዎች ወይ ከፍ፤ ወይም ደግሞ ዝቅ ሊሉ ይችላሉ። በጀግኖቻቸው “ሌጋሲ” ታፍረውና ተከብረው ይኖራሉ። ፈላስፎቻቸው ባራመዷቸው ፍልስፍናዎች ይፈረጃሉ። ባላቸው ተፈጥሯዊ አቀማመጥም ሆነ በአየር ንብረታቸው ይለያሉ። ባፈሯቸው ምሁራን፣ ሳይንቲስቶችና ተመራማሪዎችም እንደዛው። በሥነጽሑፍ ሥራዎቻቸው ደረጃ ይወጣላቸዋል። ባይሆን ኖሮ ብዙዎቹን ባላወቅናቸው፤ […]
በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎች የገቢ ማሰባሰቢያ የሙዚቃ ኮንሰርት ሊካሄድ ነው -ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
March 14, 2023 በሃሚድ አወል በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚውል ገቢ ለማሰባሰብ፤ በቀጣዩ ወር ሚያዚያ 15፤ 2015 የሙዚቃ ኮንሰርት ሊካሄድ ነው። ከኮንሰርቱ የሚገኘው ገቢ በቦረና ዞን ውሃ ጉድጓድ ለማስቆፈር እንደሚውል በኮንሰርቱ ላይ የሚሳተፉት አርቲስቶች ዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 5 በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል። የኦሮሞ አርቲስቶች ማህበር እና “ቪዥን ኢንተርቴይመንት” የተባለ የፕሮዳክሽን ድርጀት […]
“ከአንዳንድ ክልሎች ወደ አዲስ አበባ የሚደረገው ከፍተኛ ፍልሰት መንግስትን በመጣል በኃይል ስልጣን ለመቆጣጠር ያለመ ነው”- ከንቲባ አዳነች አቤቤ – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
March 14, 2023 በአማኑኤል ይልቃል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “መንግስትን ለመጣል ከአንዳንድ ክልሎች ከፍተኛ ፍልሰት” እየተደረገ መሆኑን አስታወቀ። ወጣቶችን በማነሳሳት “ወደ ጥፋት ለመግባት” እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑንም የከተማ አስተዳደሩ ገልጿል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይህንን ያስታወቀው፤ ዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 5፤ 2015 በተጀመረው የከተማዋ ምክር ቤት ጉባኤ ላይ በቀረበ ሪፖርት ነው። የከተማ አስተዳደሩን የአፈጻጸም ሪፖርት በንባብ ያቀረቡት […]