የትግራይ የሽግግር መንግስት ምስረታ መጓተት
March 11, 2023 – DW Amharic ሳልሳይ ወያነ ትግራይ በምህጻሩ ሳወት አስቀድሞ በትግራይ የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም ሲወተውት እንደነበር ያስታውሳል። ያኔ ግን ባንዳ የሚል ስም እንደተሰጣቸው የገለጹልን የድርጅቱ የውጭ ጉዳይ ክፍል ኃላፊ አቶ ኃይሉ ከበደ ከሰላም ስምምነቱ እስከ ሽግግር መንግሥቱ ምስረታ አቃፊና አሳታፊ አይደለም ይላሉ።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
እግር ኳስ ከ90 ወደ 60 ደቂቃ ያጥር ይሆን? ወይስ በተጨማሪ ደቂቃዎች ከፍ ይላል?
March 11, 2023 – BBC Amharic ከ 8 ሰአት በፊት የኳታሩ የዓለም እግር ኳስ ውድድርን ሊዮኔል ሜሲ በስተመጨረሻ ታላቁን የእግር ኳስ ዋንጫ የሳመበት ሆኖ ተመዝግቧል። ነገር ግን የዶሃው ውድድር ሌላ መነጋገሪያ የነበረው ጉዳይ አራተኛ ዳኞች ወደላይ የሚሰቅሉት የጨዋታው ጭማሪ እና ቀሪ ደቂቃዎች ማሳያ ሰሌዳ ነበር። ከዚህ ጋር በተያያዘም የ2022 ዓለም ዋንጫ በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በጣም ረዥም […]
የትግራይ ኃይሎች አባላት ስለደም አፋሳሹ ጦርነት እና ስለሰላም ስምምነቱ ምን ይላሉ?
ከ 8 ሰአት በፊት ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ላይ የበላይነትን ይዞ የቆየው ህወሓት ከማዕከላዊው መንግሥት ገለል ከተደረገ በኋላ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስተዳደር ጋር ፍጥጫ ውስጥ ገብቶ ቆይቶ ነበር። ውስጥ ውስጡን ሲብላላ የነበረው ፖለቲካዊ ውጥረት በኮሮናቫይረስ ምክንያት በአገሪቱ ውስጥ መካሄድ የነበረበት ምርጫ መራዘም እና የትግራይ ክልል ደግሞ በተናጠል ምርጫ ማካሄዱን ተከትሎ ውዝግቡን ወደ […]
ኢራንና ሳኡዲ አረቢያ ከ7 ዓመታት በኋላ ግንኙነታቸውን ለማደስ ተስማሙ
March 11, 2023 – BBC Amharic ከ 7 ሰአት በፊት የመካከለኛው ምሥራቅ ሁነኛ ባላንጣ ሆነው ላለፉት ሰባት ዓመታት ሲቆራቆሱ የቆዩት ኢራንና ሳኡዲ አረቢያ ግንኙነታቸውን በአዲስ መልክ ለመጀመር ተስማሙ። ይህ ያልተጠበቀ ዜና የተሰማው የሁለቱ ወገን ባለሥልጣናት ለአራት ቀናት በዝግ ከመከሩ በኋላ ነው። የሁለቱ አገሮች ባለሥልጣናት ምክክር የተደረገው በቻይና ሲሆን ሁለቱን ባላንጣዎች በማቀራረብ የቻይና መንግሥት ሁነኛ ሚና ተጫውቷል። ሳኡዲ […]
አሜሪካ ኪሳራ ያጋጠመውን ባንክ የደንበኞች ተቀማጭ ገንዘብ ተቆጣጠረች
March 11, 2023 – BBC Amharic ከ 7 ሰአት በፊት የአሜሪካ ተቆጣጣሪዎች ከፍተኛ ኪሳራ የገጠመውን ሲልከን ቫሊ ባንክን ዘግተው የደንበኞቹን ተቀማጭ ገንዘብ ተቆጣጠሩ። ባንኩ በሁለት አስርት ዓመታት ታይቶ የማይታወቅ ከፍተኛ ውድቀትም ውስጥ በመግባቱ ነው ይህ ውሳኔ የተላለፈው። ባንኩ የአሜሪካ መንግሥትን ቦንድን የሸጠው በከፍተኛ የወለድ ተመን ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የገጠመውን ኪሳራ ለመሸፈን ገንዘብ ለማሰባሰብ እየሞከረ እንደነበረ ተገልጿል። ባንኩ […]
የሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ ‘አቀነባባሪ’ የፍርድ ሂደት በጊዜያዊነት ቆመ
March 11, 2023 – BBC Amharic ከ 6 ሰአት በፊት የሩዋንዳን የዘር ጭፍጨፋ በዋነኝነት አቀነባብረዋል የሚባሉት ፌሊሴ ካቡጋ በሄግ እየተካሄደ ያለው የፍርድ ሂደት በጊዜያዊነት ቆመ። የ90 ዓመቱ ካቡጋ በሄግ የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት እየተዳኘ ይገኛል። ጠበቆቻቸው የመርሳት ህመም ስላለበት ፍርድ ለመቅረብ ብቁ አይደለም ማለታቸውንም ተከትሎ ነው በጊዜያዊነት የቆመው። ካቡጋ ከ26 ዓመታት ዓደን በኋላ ነው ከሶስት ዓመታት […]
ሺ ጂንፒንግ ለሦስተኛ ዘመን የቻይና ፕሬዝዳንት በመሆን ቃል መሐላ ፈጸሙ
March 11, 2023 – BBC Amharic ከ 6 ሰአት በፊት የቻይናው ሺ ጂንፒንግ ለሦስተኛ ዙር አገሪቱን ለመምራት ቃለ መሐላ ፈጸሙ። ሺ የሕይወት ዘመን መሪ ቢሆኑም በደንቡ መሠረት የቻይና የተወካዮች ምክር ቤት በሚባለው አዳራሽ ተገኝተው ቃለ መሐላ ፈጽመዋል። የ69 ዓመቱ ሺ በቻይና ታሪክ ከፍተኛ ሥልጣንና የፖለቲካ ቁጥጥር ካላቸው መሪዎች ተርታ ይመደባሉ። በቻይና መንግሥት መዋቅር ከፍተኛው ሥልጣን የሚመነጨው ከፓርቲው […]
የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ውይይትን የተቃወሙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ስብሰባ ረግጠው ወጡ – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
March 11, 2023 በሃሚድ አወል የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አማራጮችን በተመለከተ በትላንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ሲካሄድ በዋለው ውይይት ላይ ከታደሙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ውስጥ የተወሰኑት፤ ስብሰባውን በተቃውሞ ረግጠው ወጡ። ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ተቃውሟቸውን የገለጹት፤ ከሽግግር ፍትሕ በፊት “የሀገራዊ ምክክር ሊቀድም” እና “ግጭቶች ሊቆሙ ይገባል” በሚሉ ሁለት ምክንያቶች ነው። የፖለቲካ ፓርቲዎቹን ትላንት አርብ መጋቢት 1፤ 2015 […]
ኢትዮጵያ “የብሔር ፖለቲካዊ ግጭት አዙሪትን ለመስበር” የሚረዱ እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚገባት የአሜሪካ ከፍተኛ ዲፕሎማት አሳሰቡ – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
March 11, 2023 ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት ወደ ፊት ለማራመድ “ለብዙ አስርት ዓመታት ወደ ኋላ የመለሳትን የብሔር ፖለቲካዊ ግጭት አዙሪት ለመስበር የሚረዱ እርምጃዎች መውሰድ” እንደሚገባት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ ተናገሩ። እኚሁ የሀገሪቱ ከፍተኛ ዲፕሎማት፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት የሻከረው የኢትዮጵያ እና አሜሪካ መደበኛ ግንኙነት “ወደ ነበረበት ተመልሷል” […]
የብሊንከን ጉብኝት የሚያተኩረው በሕወሓት የመኖር ሕልውና ላይ ብቻ ነው !
March 11, 2023 ብሊንከን ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት ስለመላው ኢትዮጵያውያን ተጨንቀው አሊያም ስለ አሜሪካና ኢትዮጵያ ኝኙነት ተጠበው አስበው ሳይሆን በዋናነት ትኩረታቸው በሕወሓት የመኖር ሕልውናን የማስቀጠል እና ጠንካራ ሆኖ ወጥቶ በአሜሪካ አጋርነቱ እንዲቀጥል እንዲሁም ወልቃይትና ጠገዴን ለማስመለስ የአብይ አስተዳደር ከሱዳን ጋር በመቀናጀት ማድረግ ያለበትን አሜሪካ መተባበር ያለባትን ስትራቴጄ ለመነጋገር መሆኑ ታውቋል። የአሜሪካ መንግስት መግለጫ በዝርዝር የሰጣቸው መግለጫዎች […]