በሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ የሚሠሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች መታገድ እንዳሳሰበው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ገለጸ

December 28, 2024 – VOA Amharic  ኮሚሽኑ ዛሬ  ባወጣው መግለጫ ቀድሞ የታገዱ ድርጅቶቹ አቤቱታ እንደደረሰው ገልጾ ጉዳዩን እየተከታተለ ባለበት ወቅት “ተመሳሳይ ይዘት ባለው እና ተቋማቱ የፈጸሟቸውን ከባድ የሕግ ጥሰቶች በዝርዝር ባላስቀመጠ ደብዳቤ“ ተጨማሪ ሁለት ድርጅቶች መታገዳቸውን አሳሳቢ ሆኖ እንዳገኘው ገልጿል፡፡ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ በተደጋጋሚ  የሚተላለፉ እገዳዎች የሲቪክ ምኅዳሩን በማጥበብ እና በማኅበር የ…

ዶክተር ቴድሮስ እስራኤል በየመን ከፈጸመችው የአየር ጥቃት “በሕይወት ለመትረፌ እርግጠኛ አልነበርኩም” አሉ

ከ 4 ሰአት በፊት የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ዶክተር ቴድሮስ አድሐኖም ገብረ እየሱስ እስራኤል በየመኗ መዲና ሰንዓ ዓለም አቀፍ ማረፊያ ከፈጸመችው የአየር ጥቃት “በሕይወት ለመትረፌ እርግጠኛ አልነበርኩም” አሉ። እስራኤል ሐሙስ፣ ታህሳስ 17/ 2017 የሰንዓ የዓለም አቀፍ ማረፊያ ላይ የአየር ጥቃት ስትፈጽም በስፍራው የነበሩት ዶክተር ቴድሮስ ወደ አውሮፕላኑ ሊሳፈሩ ነበር። ከጥቃቱ ያመለጡት ዶክተር ቴድሮስ ከክስተቱ በኋላ […]

ሰርቢያዊያን ለምን ይሆን በየቀኑ 5፡52 ላይ ተቃውሞ የሚያሰሙት?

ከ 5 ሰአት በፊት በየዕለቱ ልክ ከረፋዱ 5 ሰዓት ከ52 ደቂቃ ላይ በሰርቢያ የሚገኙ መንገዶች ለ15 ደቂቃዎች ዝግ ይደረጋሉ። መኪኖች ይቆማሉ፤ ህዝቡ ጸጥ ይላል። ይህም በህዳር ወር በሰርቢያ ሁለተኛዋ ትልቅ ከተማ ኖቪ ሳድ በባቡር ጣቢያ ላይ ጣሪያው ወድቆ ህይወት መቅጠፉን ለማሰብ የሚደረግ ነው። ነዋሪዎች በየ ፍትህ እንዲሰጥ ይጠይቃሉ። የ15 ደቂቃው ተቃውሞ ጣሪያው ወድቆ የተገደሉትን 15 […]

ትራምፕ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቲክ ቶክ እገዳን እንዲያዘገይ ጠየቁ

ከ 4 ሰአት በፊት ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቲክ ቶክ እገዳን “ፖለቲካዊ መፍትሄ” ለመስጠት እየሰሩበት በመሆኑ እንዲያዘገየው ጠየቁ። ጠበቆቻቸው አርብ እለት ለፍርድ ቤቱ ትራምፕ “ቲክቶክ መታገዱን ይቃወማሉ” እንዲሁም “ስልጣን ከተረከቡ በኋላ ችግሮችን ለመፍታት ፖለቲካዊ መፍትሔ መጠቀም ይፈልጋሉ” ሲሉ ለፍርድ ቤት የሕግ አስተያየታቸውን አስገብተዋል። ጥር 2 /2010 ዓ.ም. ፍርድ ቤቱ የቲክ […]

ሩሲያ ለተከሰከሰው የአዘርባጃን አውሮፕላን ተጠያቂ ልትሆን ትችላለች- አሜሪካ

ከ 5 ሰአት በፊት የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ በታህሳስ 16/ 2017 ዓ.ም. ለተከሰከሰው እና 38 ሰዎች ለሞቱበት የአዘርባጃን አየር መንገድ አውሮፕላን “አሜሪካ ያሏት ቅድመ መረጃዎች’ ሩሲያ ተጠያቂ ልትሆን እንደምትችል ያሳያል አሉ። ሚስተር ኪርቢ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራርያ ባይሰጡም አሜሪካ በአደጋው ላይ ለሚደረገው ምርመራ ድጋፍ ለማድረግ ፈቃደኝነቷን መግለጿን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። አውሮፕላኑ የካስፒያን ባህርን አቋርጦ […]