ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ – የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል በአፈና አይገታም !

2019-08-19 የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል በአፈና አይገታም ! * ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የብሔራዊ ምክር ቤት የ1ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ጉባዔ ማጠናቀቂያ የተሰጠ መግለጫ የህዝባችን ሁለንተናዊ ትግል አምጦ የወለደው አብን የአማራ ህዝብ መሰረታዊ የኅልዉና፣ የፍትኅና የእኩልነት ጥያቄዎችን በመለየትና አማራዉን በማደራጀት የተጋረጠበትን የኅልውና አደጋ በመቀልበስ ከሌሎች ወንድም ሕዝቦች ጋር በእኩልነትና በፍትኃዊነት የሚኖርባትን ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ በምርጫ ቦርድ […]

ትንቢትን በሤራና በግድያ ማስቀረት አይቻልም! (ትንቢቱ ደረሰ – ከአዲስ አበባ)

2019-08-19 ትንቢትን በሤራና በግድያ ማስቀረት አይቻልም! ትንቢቱ ደረሰ –ከአዲስ አበባ የባህር ዳሩን የአማራ ባለሥልጣናት ጭፍጨፋ አስመልክቶ ሄኖክ የሽጥላ በዩቲዩብ ያቀረበውን ሀተታ ተከታተልኩ፡፡ እነአቢይና ወያኔዎች ይህን ግድያ ማቀነባበራቸውን በፊትም የምንጠረጥረው ነገር ነው፡፡ በተለያዩ አጋጣሚዎች እንደተገለጸው የአማራ ጠላቶች እጅግ ከመብዛታቸውም በተጨማሪ አንዳንድ ወፍዘራሾች “ከናካቴው የለም” የሚሉትን ይህን ጎሣ በማጥፋት ረገድ ሁሉም ይተባበራሉ — እነሱ ራሳቸው የማይስማሙና እንደዐይጥና […]

ወደ ሱዳን ሲያመሩ መተማ ላይ የተፈተሹ የመከላከያ መኪኖች መሳሪያ የጫኑ መሆናቸው ተሰማ

August 19, 2019 አይፈተሹም የተባሉ የመከላከያ ሰራዊት መኪናዎች በሕዝብ ተቃውሞ እንዲቆሙ ተደርጓል። መተማ ላይ አምስት የመከላከያ መኪናዎች ወደ ሱዳን ለማለፍ ሲሞክሩ “አንፈተሽም” በማለታቸው ከሕዝቡ ጋር አለመግባባት ተፈጥሮ በሕዝብ ተቃውሞ እንዲቆሙ ከተደረገ በሆላ ተፈትሽው በመሳሪያ የሞሉ እንደነበር ተገለጸ። የመከላከያ ሰራዊት አባላት “ወደ ዳርፉር እየሄድን ነው” ቢሉም ማለፊያም ሆነ ወደ ዳርፉር የሚሄዱበትን ማስረጃ ማቅረብ አለመቻላቸው ተገልጿል። የመኪናዎቹ […]

አበባው አበበ ማን ነው??. ከማኮነን ተስፋየ ፌስ ቡክ የተወሰደ

ሁሌ እናስታውሳቸው ተቀብሮ እንዳይቀር አኩሪ ታሪካቸው!!!!!!! አበባው አበበ ማን ነው??. ከአሢምባ የተገኘ መረጃ፤.… (የዚህ ገፅ አንባቢዎቼ የምናውቀውን በማጋራት የታሪክን ክፍተት አብረን እንሙላ) አበባው አበበ በ ሐረር ክ/ሃገር በጂጂጋ ከተማ በ ኢሕአፓነት ተጠርጥሮ በደርግ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች በግፍ የተገደለ ገና የሰባተኛ ክፍል ተማሪ የነበረ ሮጦ ያልጠገበ ወጣት ነበር። መንግስቱ ኅ/ማርያም ልክ ያሁኖቹ የደርግ ቱልቱላዎች እንደሚያስቀምጡት አገር […]

“ከተማ አስተዳደሩ የወሲብ ንግድን በህግ ወንጀል የማድረግ ስልጣን የለውም” የህግ ባለሙያ – ቢቢሲ/አማርኛ

August 18/2019 ከሰሞኑ የአዲስ አበባ አስተዳደር የጎዳና ልመናና የወሲብ ንግድን ለማገድ ረቂቅ ህግ ማዘጋጀቱን ተከትሎ በብዙዎች ዘንድ በርካታ ጥያቄዎች እየተነሱ ነው። ከእግዱ አላማ አንስቶ እስከተደረጉ ዝግጅቶች፣ እንዲሁም የአስተዳደሩ ስልጣን ባሉና በተያያዙ ጉዳዮች ውይይቶች ቀጥለዋል። ረቂቅ ህጉ በአሁኑ ወቅት ለካቢኔ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ ብቻውን መወሰንም ስለማይችል ባለድርሻ አካላት በተለይም የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የተለያዩ […]

ምርጫ ቦርድ ሆይ ስህተትን ማረም የታላቅነት ምልክት ነው – ከ Batero Belete ከፌስ ቡክ የተወሰደ

የፓለቲካ ፓርቲዎች እና የምርጫ ረቀቅ ህጉን አስመልክቶ የተነሱ ዋና ዋና ጥያቄዎችና መልሶቻቸው በሚል ርእስ ምርጫ ቦርዱ ካቀረባቸው ውስጥ የሚከተለው ይገኛል:: ጥያቄ 2- የፓለቲካ ፓርቲዎች ለምስረታ ለአገራዊ ፓርቲ 10 ሺህ የድጋፍ ፊርማ እና ለክልል ፓርቲ ምስረታ 4 ሺህ የድጋፍ ፊርማ እንዲያሰባሰቡ በረቂቅ ህጉ ውስጥ ለምን ተካተተ? መልስ – የፓለቲካ ፓርቲዎች ህዝባዊ መሰረት እንዲኖራቸው ከመፈለግ አንጻር፣ ከአገሪቷ […]

ጥያቄ- ለአንዳርጋቸው ጽጌ፣ ለፕሮፌሰር መሥፍን ወልደማርያም እና ለመንግሥቱ ሃይለማርያም

ታጠቅ ዙርጓ : August 16/2019 የነገድና የጎሳ (tribe and ethnic) ማንነት መገለጫ ፦ ቋንቋ፣ ማኅበራዊ ባህል ፣ልማዳዊ አኗኗር፣ ማኅበራዊ ሥነ–ልቦና (language,social culture, customary habits and psycho-social dynamic) ከሆኑ አማራ እነዚን ማንነቶች የሉትም ማለት ነውን? የኦሮሞችን፣ የትግሬዎችን፣የአፋሮችን ፣ የሱማሌዎችን፣ የጉራጌዎችን፣ የወላይታዎችን ወዘተ.. ማንነት የሚገለጸውና የሚለየው ከላይ በተጠቀሱትን እሴቶች ከሆነ አማራ እነዚህን እሴቶች ለምን አይኖሩትም? ከየትኛው ጭብጣዊ […]

በአዲስ አበባ ከተማ የማንነት ጥያቄ ላይ የኢትዮጵያ ክፍላተሃገር ህብረት ያለው አቋም

  ነሓሴ 9 ቀን 2011 ዓም(15-08-2019) አዲስ አበባ ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያም አዲስ አበባ ነች! ማንኛውም በመንግሥታዊ ስርዓት የሚመራ አገር ሥርዓተ መንግሥቱን በአንድ አካባቢ በቆረቆረው ከተማ መዘርጋቱ እንግዳ አይደለም።መንግሥት ወይም ስርዓት ያለመንበር ወይም ያለከተማ ሊመሰረት አይችልም።የሁሉም አገር ስርዓትና የከተማ አመሰራረት ታሪክ ጊዜና ቦታው ቢለያይም ተመሳሳይ ነው። ኢትዮጵያ መንግሥታዊ ስርዓት መስርታ እንደ አገር ከተዋቀረችበትና በተጓዘችበት ታሪኳ ሁኔታው ባስገደደውና […]

ፍትህ ወዴት አለሽ ?! ለግፉአን’ስ ተጠያቂው ማነው ?! ይድነቃቸው ከበደ

August 17, 2019 ክልል የመሆን ጥያቄን ” በግልበት ወይም በህግ አስከብሩ ” ፤ የተባሉትን ትዕዛዝ በመቀበል ፤ እራሱን ኤጄቶ እያለ በሚጠራ ስብስብ አስተባባሪነት እና መሪነት በተፈጸመ አሰቃቂ የጅምላ ጥቃት ከ60 በላይ ሰዎች በግፍ ተገድለዋል ፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ፣ ለዘመናት ከኖሩበት የተፈናቀሉም ብዙዎች ናቸው ፣ አብያተ ክርስቲያናትን ጨምሮ መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል፣ ንብረትም […]

ወንጀላኛ ፈቶ ወንጀል የሌለበት የሚያስር አፓርታይዳዊ አገዛዝ – ወንድወሰን ተክሉ

August 17, 2019 ከ60 በላይ ህይወት በተጨፈጨፈበትና 17 አብያተ ክርስቲያናትን ጨምሮ ከሶስት መቶ በላይ ቤቶች ውድመት ተጠርጥረው የታሰሩት ኤጄቶዎች ዛሬ ተፈቱ። በእነ ታሪኩ ለማ መዝገብ ክስ ተመስርቶባቸው በእስር ላይ የነበሩት ዘጠኝ ኤጄቶች ዛሬ ነሀሴ 10 ሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት በ50 ሺህ ብር የዋስ መብታቸው ተጠብቆ ከእስር ተለቀዋል። የዋስ መብታቸው የተጠበቀላቸውና ከእስር የወጡት፦ […]