ከቡርቃ ዝምታ: ወደ ፊንፊኔ ጫጫታ !! (አሥራደው ከፈረንሳይ)

2019-06-23 ከቡርቃ ዝምታ: ወደ ፊንፊኔ ጫጫታ !! አሥራደው ከፈረንሳይ ኳኳታ የሃሳብ ድህነት መግለጫ መሆኑን ብናምንም፤ ከአፍ ወለምታው በስተጀርባ ያለውን ትልቅ ስብራት ወጌሻም አይጠግነው !! ማስታወሻ : በዚህ ርዕስ መጣጥፍ ለማቅረብ አስቤ ከጎረምሶችቹ ጋር አብሮ አቧራ ላለማቡነን ስል ትቼው ነበር፤ ሆኖም ጎረምሶቹ የሚያቦኑት አቧራ ዛሬም እያገረሸ በማስቸገሩ፤ ማለት የሚገባኝን ለማለት ወሰንኩ፤ እናም ይኸው:: አገር እበት ወልዳ […]

ብጄኔራል አሰምነው ጽጌ! የዘመናችን ታናሹ በላይ ዘለቀ – ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethio semay)

June 24, 2019 ቅዳሜ ከከተማየ ወጣ ብየ ነበር። አንድ ወዳጄ ደውሎ አዲስ ዜና አለ አለኝ። ስንጓዝበት የነበረው ድልድይ ረዥም እና  ስልክ ለማስተላለፍ ስለማያመች “በደምብ ማድመጥ ስላልቻልኩ ዘጋሁት”። ትኩስ የተባለውን ዜና ለማድመጥ ቸኩዬ ሲመሻሽ እቤት ስገባ ላንድ የቅርብ ወዳጄ ስልክ ደውየ፤ ምን ተፈጠረ? አልኩት። የሆነውን ሁሉ ነገረኝ። በስፋት ለማወቅ ድረገጾች ላይ ስፈትሽ ወዳጄ ከነገረኝ ጋር ተመሳሳይ […]

“ራሴን ለአማራ ሕዝብ ሰጥቻለሁ።” – ዶ/ር አምባቸው መኮንን

June 24, 2019 ትንቢታዊ ቃልኪዳን? “ራሴን ለአማራ ሕዝብ ሰጥቻለሁ።” – ዶ/ር አምባቸው መኮንን ከዶ/ር አምባቸው መኮንን፤ የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ጋር የዛሬ ሁለት ሳምንት ተነጋግረን ነበር። ዛሬ በሕይወት የሉም። ከሁለት ቀናት በፊት ከሌሎች የሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር ለስብሰባ በተቀመጡበት ቢሮ የጸጥታ አስከባሪ ኃይል አባላት መለያ ልብስ በለበሱ ሰዎች በተከፈተ ተኩስ ሕይወታቸው ማለፉ ተነግሯል። ዶ/ር አምባቸው በቃለ ምልልሳችን ወቅት “ራሴን ለአማራ ሕዝብ […]

መንግስት “መፈንቅለ መንግስት” ያለው የባሕርዳር እና አዲስ አባባ ቀውስ ብዙ ጥያቄዎችን አስነስቷል

June 23, 2019 ሰማኽኝ ጋሹ (ዶ/ር) መንግስት ሁኔታዎችን ተቆጣጥሮ የባህር ዳርን አካባቢ ሰላም ማስጠበቁ የሚያስመስግን ነገር ነዉ። ግጭቶች ከዚህ በላይ ቢባባሱ ብዙ እልቂት ሊደርስ ይችል እንደነበር መገመት ይቻላል። ከሚወጡት መረጃዎች ለመረዳት እንደሚቻለዉ በጀነራል አሳምነዉ ፅጌና በክልሉ መስተዳድር መካከል የክልሉን ፀጥታ አከባበር በተመለከተ አለመግባባቶች ነበሩ። የክልሉና የፌዴራል መንግስቱ ጥቃቱ የተፈፀመዉ በጀነራሉ እንደሆነም በግልፅ አሳዉቀዋል። ነገር ግን […]

በገለልተኛ አካል ሳይጣራ ጀነራል አሳምነውን መክሰስ ኢፍትሃዊነት ነው – ግርማካሳ

June 23, 2019 June 23 2019 የትላንቱ ቀን በጣም የሚያሳዝን ቀን ነው። ለሞቱት ነፍስ ይማር ፣ ለወዳጅ ዘመድም መጽናናቱን ይስጥልን እላለሁ። ከነ ዶ/ር አምባቸውና ጀነራል ሰአረ መኮንን በተጨማሪም ስማቸው የተጠቀሰ ያልተጠቀሰም ብዙ ሞተዋል። ጀነራል አሳምነውንም ገድለዉታልም ይባላል። ያ ሁሉ መሆን አልነበረበት ፣ ግን ሆኗል። እግዚአብሄርን የተመሰገነ ይሁን፣ ዛሬ ነገሮች ተረጋግተው ነው የዋሉት። የፈሰሰ ደም ስለመኖሩ […]

ስለመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውና ስለግድያው እስካሁን የምናውቀው – ቢቢሲ / አማርኛ

ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ባህር ዳር ውስጥ የተከሰተው ነገር ለብዙዎች ያልተጠበቀ ነበር። ድንገት ከአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድሩ ቢሮ አካባቢ የተሰማው ተኩስ ለሰአታት ቀጥሎ ከተማዋን ያደናገጠ ሲሆን፤ ምን እንደተከሰተ ሳይታወቅ ቆይቶ የተኩስ ልውውጡ በሌሎች አካባቢዎችም አጋጥሟል። የተኩሱ ምክንያት የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ መሆኑ በፌደራል መንግሥት ከተነገረ በኋላ እንደ ባህር ዳሩ ከባድ ባይሆንም አዲስ አበባ ውስጥ በጦር ኃይሎች ጠቅላይ […]

ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የተገደሉት በጠባቂያቸው መሆኑ ተገለፀ – ቢቢሲ / አማርኛ

23 Jun 201923 Jun 2019 በትናንትናው ዕለት የተደረገውን መፈንቅለ መንግሥት ሙከራና ግድያዎችን በተመለከተ ቢቢሲ አማርኛ ቀጥታ ዘገባ ይዞላችሁ ይቀርባል። ጭምቅ ሃሳብ በአማራ ክልል የተሞከረው መፈንቅለ መንግሥት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ተገድለዋል የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንን መገደላቸው ተረጋገጠ የክልሉ ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ብርጋዴየር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ከመፈንቅለ መንግሥቱ ጀርባ መሆናቸው ተገልጿል […]

ጀግናው? ዶ/ር አብይ እነሆ! ዶ/ር ዘላለም እሸቴ

2019-06-23 ጀግና? ደግ ሰው እሺ። ትሁት ሰው፥ አዋቂ ሰው፥ አስተማሪ ሰው፥ ታታሪ ሰው፥ ቢባል ይሁን ያስማማናል። ግን አንዳንዶች ጀግንነትን ከዶ/ር አብይ ብርታት ጎራ አይመድቡትም። ይልቁንም የጀግነንት ማነስ ከድክመቱ ጋር ያያይዙታል። ጀግና አይደለም ይሉናል። ወሬ ብቻ ተባለ። እኔም ብሆን በዶ/ር አብይ ክስተት ተስፋ ሰንቄ፥ ከዚያ ፈንጥዤ፥ ደግሞም ተደናግሬ ሳበቃ የማታ ማታ የደረስኩበትን ላካፍላችሁ። ትንሽ በሞኝነቴ ታገሡኝና፥ […]

ዐብይ መርዝ (መስፍን አረጋ)

2019-06-23 ዐብይ አህመድ፣ ዐብይ አህመድ ያህያ ሥጋ አልጋ ሲሉት ዐመድ፡፡ መንደርደርያ ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው፡፡ የዚህ ጦማር ዓላማ ደግሞ /መደመር/ የሚሰኘው ያብይ አህመድ /የመቀነስ/ ጎርፍ ጦቢያን ጠራርጎ ከመውሰዱ በፊት ጦቢያውያን እንዲገድቡት ለማሳሰብ ነው፡፡ እኔ እራሴ መስፍን አረጋ ይህ የዐብይ ጎርፍ እያሳሳቀ ከወሰደኝ አያሌ ጦቢያውያን ውስጥ አንዱ ነበርኩ፡፡ ጎርፉ ከማሳሳቅ አልፎ አጃጅሎኝ ስለነበር፣ ጎርፉን በማሞገስ የሚከተለውን […]