በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስም በሀገርና በሕዝብ ላይ የሚደርሰው በደል ይቁም! (ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ)

14/03/2018 ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በመላ ሀገሪቱ የተፈጠረው ፖለቲካዊ ችግር ስር እየሰደደ መሄዱ የማያሳስበው አንድ ዜጋ አይኖርም፡፡ ላለፉት 27 ዓመታት ሲከማቹ የመጡ በርካታ ኢህአዴግ ሰራሽ ችግሮች ዛሬ ላይ ሕዝባዊ ቁጣን በማስነሳት ሰላምና መረጋጋታችን ብርቱ ፈተና ላይ ወድቋል፡፡ ገዢው ፓርቲ ይህንን እንደሰደድ እሳት የሚቀጣጠል ችግር የሕዝብን ድምፅ በማድመጥ ተገቢውን ምላሽ ከመስጠትና አገራዊ መግባባትን ከመፍጠር ይልቅ ሀገሪቱን እንደገና […]

የኃይሌ ገ/ሥላሴ ችግሩ፣ በሀብት መክበሩ! (በፈቃዱ ዘ ኅይሉ)

14/03/2018 ሻለቃ ኃይሌ ገ/ሥላሴ የዛሬ 8 ዓመት ገደማ፣ በመስከረም ወር 2003ቱ የኢሕአዴግ ጉባዔ ላይ ተገኝቶ ንግግር አድርጎ ነበር። እናም “እናንተ ፖለቲካውን ሥሩ፣ ንግዱን ለኛ ተዉልን” የሚል ንግግር አድርጓል። ንግዱን አልተዉለትም። ሆኖም ምንጩ በሚታወቀው ሀብቱ እየተፎካከራቸው ነው። እነርሱ በወቅቱ የፈለጉት በሕዝቡ የሚወደደውን ሰው ወደ መድረካቸው በማምጣት ከሕዝባዊ መውደዱ መሻማት/መፎካከር ነበር። ከዚያ ቀጥሎ ለመጀመሪያ ግዜ ክብረወሰን ሲሰብር […]

አስቸኳይ ጊዜ አዋጁንና ሰላማዊ ዜጎች ጭፍጨፋ በጥብቅ አናወግዛለን! (ጎጃም ዓለምአቀፍ ትብብር)

March 14, 2018 መጋቢት 9 ቀን፤ 2010 ዓ/ም ከጎጃም ዓለምአቀፍ ትብብር የተሰጠ መግለጫ ሃገራችን ኢትዮጵያን ለ27 አመት በዘር ከፋፍሎ አስጨንቆ እየገዛ ያለው የወያኔ ቡድን በአገሪቱና በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ሰቆቃ ፈጽሟል። አሁንም ህዝቡን እንደጠላት ሃይል ጅምላ ጭፍጨፋውን አጠናክሮ ቀጥሎበታል። በዚህ በያዝነው ሳምንት በሞያሌ የተፈፀመው ጭፍጨፋ የወያኔ ተደጋጋሚ ሕዝብን በፍርሃት ዓለም ጠርንፎ እየቀጠቀጡ የመግዛት አላማና ፖሊሲ እንጂ […]

አንተ እንደ መርዶክዮስ ፤ እኔም እንደ አስቴር ልሁን (ለምለም ፀጋው)

ለምለም ፀጋው   በዙፋን ተቀምጦ፣ አጃቪው በአደራሽ ጠጁን እየጠጡ፣ ጮማ ሲቃመጡ፣ አፈ ሙዝ አንግተው፣ ማን አለብን ብለው እንጦጦ ላይ ወጡ። ልጆቻቸው ሁሉ ኢሮፕ፣ አሜሪካ ትምሀርትን በመቅሰም ሲንደላቀቁብን፤ እባክህ አዳምጠኝ ጋሻ ጃግሪ አተሁን። ጭጭ ማለትም ይብቃ፤ ወንድምህ፣ እህትህ፣ በጥይት ሲወቃ። አዕምሮህን ግዛው የምልህን አዳምጥ፤ ጊዜያዊ ለሆነው ለእንጀራ አትቋምጥ። አንተ እንደ መርዶክዮስ ሁን እኔም እንደ አስቴር ልሁን። […]

ኦሮሚኛ ተጨማሪ የፌዴራል ቋንቋ! ለፕሮፈሰር ጌታቸው ኃይሌ የተሰጠ መልስ –

ኦሮሚኛ ተጨማሪ የፌዴራል ቋንቋ! ለፕሮፈሰር ጌታቸው ኃይሌ የተሰጠ መልስ ባይሳ ዋቅ – ወያ **** “የቋንቋዎች ትምህርት አስፈላጊነት” በሚል ርዕስ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ በቅርቡ በኢትዮ ሚዲያ ገጽ ላይ ያሰፈሩትን የግል አስተያየት ካነበብኩ በኋላ፣ ኦሮምኛን ሁለተኛ የፌዴራሉ የመሥርያ ቋንቋ የማድረግ ጥያቄ ባግባቡ የተረዱት ስላልመሰለኝ፣ በበኩሌ በሳይንስ ጥናት የተደገፈ መረጃ ባይኖረኝም እንደ አንድ ኦሮሞ ግለሰብ እስከ ዛሬ ካየሁትና […]

ሃሰተኛ መድሃኒቶችን ለገበያ ያቀረቡ ተፈረደባቸው -BBC

14 ማርች 2018 Image copyrightAFPአጭር የምስል መግለጫባሳለፍነው ዓመት በአይቮሪ ኮስት 50 ቶን የሚመዝን ሃሰተኛ መድሃኒት እንዲወገድ ተደርጎ ነበር የቤኒን ፍርድ ቤት ሃሰተኛ መድሃኒቶችን ሸጠዋል ያላቸውን የህክምና እቃዎች አምራች ኩባንያ ከፍተኛ አመራሮችን አሰረ። በምዕራብ አፍሪካ ሃሰተኛ መድሃኒቶችን ለመቆጣጠር ከፍተኛ እንቅስቃሴ እየተካሄደ ይገኛል። መድሃኒቶች ሃሰተኛ ናቸው የሚባሉት ይዘዋል የተባለው ንጥረ-ነገር ሳይኖራቸው ወይም አነስተኛ ሆኖ ሲገኘ ነው። አብዛኛውን […]

የሁለት ወታደሮች ወግ (ትዝብት – ጌታቸው ሽፈራው እንደዘገበው))

14/03/2018 ~የቂሊንጦ እስርቤት የደህንነትና ጥበቃ  ኃላፊ የነበሩት ዋና  ኦፊሰር ገ/ማርያም  ወልዳይ ዛሬ ታህሳስ 24/2010 ዓም  በፌደራል  ከፍተኛ ፍርድቤት  ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት በእነመቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ክስ መዝገብ በተከሰሱት  ላይ መስክረዋል።1ኛ ተከሳሽ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ምስክሩ እሱንና አቶ በቀለ ገርባን ለማስገደል ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን፣  በቂሊንጦ ቃጠሎ ወቅት የተገደሉ እስረኞች በጅምላ ተቀብረው ቀብሩ ላይ እስር […]

የኢትዮጵያ መንገዶች ከነዳጅ ቦቴ ነጻ ሆነዉ ዋሉ (እስራኤል ሰቦቃ)

14/03/2018 በአጠቃላይ ሀገሪቷ በነዳጅ ቦቴዎች ላይ የተጣለው ነዳጅ ማቆም ኣድም ተግባራዊ ሆኗል። ዋነኛዉን የሀገሪቷ የንግድ መስመሮች ከቦቴ ነጻ ሆነዉ መዋላቸዉን ከያቅጣጫዉ የሚደርሱ ዘገባዎች ያመለክታሉ። ከነዳጅ ተኣቅቦው ጋር በተያያዘ መልኩ በርዕሰ መዲናይቷ ቤንዚን የሚሸጠዉ በውረፋ ሲሆን ኣንዳንድ ነዳጅ ማዲያዎች 5 ሊትር ብቻ ላንድ መኪና እንደሚሸጡ ለማወቅ ተችሏል(ይህ እንግድህ ኮታ መሆኑ ነዉ)። ርዕሰ መዲናይቷ ሸገርም ሳትወድ በግድ […]

የትግራይ ወያኔ የአማራ እናቶች ልጅ እንዳይወልዱ የማምከን እና የዘር ማጥፋት ወንጀል እየሰራ እንደሆነ ተጋለጠ

March 13, 2018 የትግራይ ወያኔ የአማራ እናቶች ልጅ እንዳይወልዱ የማምከን እና የዘር ማጥፋት ወንጀል እየሰራ እንደሆነ ተጋለጠ ከዚህ በታች የምትመለከቱት በእስራኤል የቴሊቭዝን ፕሮግራም የተሰራ ፕሮግራም እንደሚያጋልጠው የትግራይ ወያኔ የአማራ እናቶች ልጅ እንዳይወልዱ የማምከን ስራና የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈጸመ ይገኛል። የትግሬ ወያኔ ለአማራ እናቶች ያለፈቃዳቸው ልጅ እንዳይወልዱ የሚያደርግና የሚያመክን ዲፖ ፓሮቨራ (Depo-Provera) የተባለውን የማምከኛ መርፌ እየወጋቸው […]

የደደቢቶች ቀብር ዋዜማ… (መኮንን ሀብተጊዮርጊስ ብሩ (ዶ/ር))

March 13, 2018 ዋይ ዋይ አትበይ …የሀገሬ ባልቴት ይልቅ ጨፍሪልን… አዉሬን ሲቀብሩት። ይህች ምድር ብዙ አምባገነኖችን አስተናግዳለች። የደደቢት በርሃ የፈጠረቻቸዉን ባንዳ ህወኣትን ጨምሮ በርካታ የእንግዴ ልጅ ሊሆኑ የሚገቡ የፍጥረት ስህተቶችን ይህች ምድር ታዝባለች። ምነዉ ዉሃ ሆነሽ በቀረሽ ሊባሉ የሚገባቸዉን የሰዉ ልጅ አምሳያ ግን ግብረ ሳጥናኤላዊ የሰቆቃ ተዉሳኮችንም ታቅፋለች…..። የእናት ሆድ ዥንጉርጉር እንዲሉ የሌላዉ ሰላም ….. […]