በኮሮና ቫይረስ ለእልቂት ከመዳረጋችን በፊት ስለበሽታው ያለንን የተዛባ አመለካከት ማስተካከል ግድ ይለናል!

From: Habtamu Girma Demiessie (ሀብታሙ ግርማ ደምሴ) <ruhe215@gmail.com>  በኮሮና ቫይረስ ለእልቂት ከመዳረጋችን በፊት ስለበሽታው ያለንን የተዛባ አመለካከት ማስተካከል በኮሮና ቫይረስ ለእልቂት ከመዳረጋችን በፊት ስለበሽታው ያለንን የተዛባ አመለካከት ማስተካከል ግድ ይለናል! ******** ሀብታሙ ግርማ (በጅግጅጋ ዩኒቨርሲት ኢኮኖሚክስ ረዳት ፕሮፌሰር፤ ኢ–ሜይል፡– ruhe215@gmail.com) ********* የኮሮና ቫረስ ኢትዮጵያ ገባ ከተባለ አስር ቀናት አለፉ፤ በእነዚህ ቀናት በስራ ምክንያት በተዘዋወርኩባቸው ድሬዳዋ፣ ሐረር […]

በኬንያና በሶማሊያ ድንበር የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ ኢትዮጵያ የበኩሏን እንድትወጣ የአውሮፓ ኅብረት ጠየቀ

ፖለቲካ 22 March 2020 ዮሐንስ አንበርብር በኬንያና በሶማሊያ መካከል የተፈጠረው ግጭትና የፖለቲካ ውጥረት ሥጋት ያደረበት የአውሮፓ ኅብረት፣ የሁለቱ አገሮች መሪዎች ችግሩን በውይይት እንዲፈቱ ኢትዮጵያ የበኩሏን ሚና እንድትወጣ ጠየቀ።  የአውሮፓ ኅብረት ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ፣ በኬንያና በሶማሊያ መካከል የተፈጠረው ውጥረትና ወታደራዊ እንቅስቃሴ በእጅጉ እንዳሳሰበው ይፋ አድርጓል። በሶማሊያ ራስ ገዝ ግዛት በሆነችው ጁባላንድ የጦር ኃይልና በሶማሊያ ማዕከላዊ […]

ክብር ረፍት ለጓድ መኮንን ደጀኔ (መኩሪያ)

መጋቢት 10/2012 ዓ.ም ክብር ረፍት ለጓድ መኮንን ደጀኔ (መኩሪያ)  (ከ1941-2012 ዓ.ም) የኢሕአፓ ድርጅታዊ የሀዘን መግለጫ! አቶ መኮንን ደጀኔ ወልደሰንበት (በኢሕአፓ ድርጅታዊ ስማቸው “መኩሪያ”) በሸዋ ክፍለ ሀገር፣ በየረርና ከረዩ አውራጃ በ1941 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ የ1ኛ ደረጃና 2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በናዝሬት አጼ ገላውዴዮስ ሁ/ደ/ት/ቤት ከተከታተሉ በኋላ ባህርዳር በሚገኘው ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ገብተው ሞያዊ ስልጠና ወስደዋል፡፡ እስከ 1966 ዓ.ም ድረስ […]

ፋኖ/አርበኛን በተመለከተ መታወቅ ያለበት ዋና ነጥብ!!!

የፀረ አማራው ቅጥረኛ የጥፋት ኃይል ብአዴን ባለሥልጣናትና አንዳንድ ያገዛዙ ቅጥረኞች “በሀገሪቱ ከመንግሥት ውጭ የታጠቀ ኃይል ሊኖር አይችልም አይገባምና ጎንደር በፋኖና አርበኞች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ትክክል ነው!” ሲሉ ተደምጠዋል!!! ሲጀመር ከጥንት ጀምሮ እስከ አሁንም ፋኖም ሆነ አርበኛ ሕገወጥም ኢመደበኛም የሆነ ታጣቂ ኃይልና አደረጃጀት አይደለም!!! አገዛዙ ፋኖንም ሆነ አርበኞችን “በእኔ ቁጥጥር ስር ካልሆናቹህ!” ካላለ በስተቀር ፋኖም […]

አማራ ሆይ! ትናንትናም፣ ዛሬም፣ ነገም ቀንደኛውና ቁ. 1 ጠላትህ ብአዴን ነው!!!

አማራ ሆይ! ትናንትናም፣ ዛሬም፣ ነገም ቀንደኛውና ቁ. 1 ጠላትህ ብአዴን ነው!!! ፀረ አማራው ብአዴን በተለይ ከሰኔ 15ቱ የፀረ አማራ ብሔርተኝነት ትግል የአገዛዙ የግፍ ዘመቻ በኋላ በተለያዩ የፈጠራ ክሶችና ስም ማጥፋቶች ፋኖን ለመምታትና በሕዝብ ለማስጠላት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል!!! ከሰሞኑ ደግሞ ይሄንን የጠላት ሥራውን በከፍተኛ ዘመቻ ተያይዞታል፡፡ አገዛዙ ጎንደር ባሠማራው ኃይሉ በፋኖ ስም ዝፊያ፣ ግድያና ሌሊት […]

እጅግ አሳዛኝ ሰበር ዜና!!!

ዋነኛው የአማራ ጠላት ብአዴን የሚሉት የወያኔ/ኦህዴድ አህያና ባንዳ የጥፋት ኃይል ቀደም ባለው ጊዜ አገዛዙ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈጽመውን ግፍ ተቃውሞ ከጓዶቹ ጋር በረሃ በመግባት አገዛዙን ሲፋለም የኖረውን የአማራ ሕዝብ ባለውለታ አርበኛ መሳፍንትንና ጓዶቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል ዛሬ ከቀኑ 11 ሰዓት አካባቢ በመሞከሩ ዳባት ላይ ከፍተኛ ውጊያ ተከፍቷል!!! ከዚህ ጋር በተያያዘ ጎንደር ላይ ሦስት ሰዎች በጥይት […]

ተስፋችን ጨንግፏል!!!

እነ እስክንድር ነጋ የፓርቲ ምሥረታ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን በመኢአድ ጽ/ቤት ባደረጉ ወቅትና ባልደራስና መኢአድ መቀናጀታቸውን ወይም መጣመራቸውን ባስታወቁ ወቅት በጻፍኳቸው ሁለት ጽሑፎች እነ እስክንድር “ሀገር አቀፍ ፓርቲ ነን!” ከሚሉት የላቀ ሁሉን አቀፍ አቅም ስላላቸው ፓርቲ ሲመሠርቱ ፓርቲውን ሀገር አቀፍ ማድረግ ሲችሉ የአዲስ አበባ ፓርቲ አድርገው ስለመሠረቱትና ለውጥ ለማምጣት ደግሞ የግድ ከሀገር አቀፍ ፓርቲ ጋር መቀናጀት ስለሚኖርባቸው […]