ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በምሁራን እና በፖለቲከኞች እንዴት ይታወሳሉ?

ከ 5 ሰአት በፊት በአሁኑ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሃድያ ዞን ምሥራቅ ባዶዋቾ ሾኔ ከተማ አቅራቢያ ባለች ገጠራማ መንደር መጋቢት 1942 ዓ.ም. የተወለዱት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ኬንያ ውስጥ በህክምና ላይ ሳሉ በ74 ዓመታቸው አርፈዋል፡፡ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የምሥራቅ ባደዋቾ በሾኔ፣ በኩየራ፣ በአዳማ የተከታተሉ ሲሆን፣ የከፍተኛ ደረጃ ትርምህርትን ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በአሜሪካ ተምረዋል። […]

የኢትዮጵያ መንግሥት ለውስጣዊ ግጭት ምን ያህል የድሮን ጥቃት እየተጠቀመ ነው?

ከ 5 ሰአት በፊት አቶ ንጉሥ በለጠ* በድሮን ጥቃት በአንድ ጀምበር ሕይወታቸው ከተመሳቀለባቸው ግለሰቦች መካከል አንዱ ናቸው። በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ባለቤታቸውን ጨምሮ ስምንት ቤተሰቦቻቸው እንደተገደሉባቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። የካቲት 11/2016 ዓ.ም. ሞጃ እና ወደራ ወረዳ ‘አይሱዙ’ በተባለ ተሽከርካሪ ላይ በተፈጸመው የድሮን ጥቃት ከሳሲት ወደ ጋውና ሲጓዙ የነበሩ ከ20 በላይ የአንድ ቤተሰብ አባላት […]

ሄዝቦላህ በሊባኖስ 9 ሰዎች ለሞቱበት እና 3 ሺህ የሚደርሱ ለቆሰሉበት ፍንዳታ እስራኤልን ተጠያቂ አደረገ

ከ 4 ሰአት በፊት በሊባኖስ የሚገኙ የሄዝቦላህ አባላት መረጃ ለመለዋወጥ የሚጠቀሙባቸው በእጅ የሚያዙ ‘ፔጄሮች’ ፈንድተው አንድ ሕፃንን ጨምሮ ዘጠኝ ሰዎች ሲሞቱ ወደ ሦስት ሺህ የሚጠጉ ሰዎች መቁሰላቸውን የአገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር አስታወቀ። በቤይሩት እና በሌሎች በርካታ ክልሎች በተመሳሳይ ሰዓት በደረሰው ፍንዳታ ከቆሰሉት ከ2 800 በላይ ሰዎች መካከል በሊባኖስ የኢራን አምባሳደር ይገኙበታል። ፔጀር አነስተኛ ገመድ አልባ […]

በ17 የአሜሪካ ግዛቶች ለሚገኙ የምርጫ አስፈጻሚዎች ምንነቱ ያልታወቀ እሽግ በፖስታ ተላከ

ከ 4 ሰአት በፊት ከሳምንታት በኋላ የሚደረገውን ምርጫ ለሚያስተባብሩ በ17 የአሜሪካ ግዛቶች ለሚገኙ የምርጫ ኃላፊዎች የተላከ እሽግ ፖስታ ላይ ምርመራ እያደረጉ እንደሚገኙ ኤፍቢአይ እና የአሜሪካ ፖስታ አገልግሎት ገለጹ። የአሜሪካ ፌዴራል ምርመራ ቢሮ ባልደረቦች እሽጎችን ከተቀባዮቹ መሰብሰባቸውን የገለጹ ሲሆን፣ አንዳንዶቹ ምንነቱ ያልታወቀ ነገር እንደተገኘባቸው አመልክተዋል። ሆኖም ግን በእሽጎቹ ምክንያት የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል። እሽጎቹ ከኒው ዮርክ […]

ሴቶችን ለወሲብ ንግድ በማዘዋወር ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር የዋለው አሜሪካዊው ራፐር ዲዲ ዋስትና ተከለከለ

ከ 4 ሰአት በፊት ሴቶችን ለወሲብ ንግድ በማዘዋወር የተጠረጠረው ታዋቂው አሜሪካዊ ራፐር በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ በዋስትና እንዲለቀቅ የቀረበው ጥያቄ ውድቅ ሆነ። በኒው ዮርክ የሚገኘው ፍርድ ቤት የፌዴራል ዳኛ፤ ሙዚቀኛው ከሀገር ሊጠፋ ስለሚችል በቁጥጥር ሥር እንዲቆይ አቃቤ ሕግ ያቀረበውን ጥያቄ ተቀብለው ዋስትና ከልክለዋል። የ54 ዓመቱ ዲዲ ሰኞ አመሻሹን ነው በቁጥጥር ሥር የዋለው። ራፐሩ ከአውሮፓውያኑ 2008 […]