የቻይናው ኢንዱስትሪ ግሩፕ በገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን መሬት ለማልማት ተስማማ

በኤልያስ ተገኝ October 9, 2024 የቻይናው ቾንግቺንግ ኩንኋንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ (Chongqing Kunhuang International Industry Group -CKIIG)፣ በስድስት ቢሊዮን ብር (50 ሚሊዮን ዶላር) በገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በንዑስ ተቋራጭነት መሬት ለማልማት ተስማማ፡፡ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የንዑስ ተቋራጭ አልሚነት ስምምነት የተፈራረመው የቻይና ዓለም አቀፍ ኢንዱስትሪ ግሩፕ፣ በገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ውስጥ ከሚገኘው መሬት 20 ሔክታር የሚሆነውን በማልማት […]

ሦስት የመድኃኒት ፋብሪካዎች ወደ ሥራ ሊገቡ ነው

በኤልያስ ተገኝ October 9, 2024 ሦስት የአገር ውስጥ የመድኃኒት አምራች ፋብሪካዎች በተያዘው ዓመት ወደ ሥራ እንደሚገቡ ተገለጸ፡፡ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የተገነባውን የመድኃኒት ፋብሪካ ጨምሮ፣ ሌሎች ሁለት የአገር ውስጥ የመድኃኒት አምራች ፋብሪካዎች በተያዘው ዓመት ወደ ሥራ ይገባሉ ተብሏል፡፡ በኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን የመድኃኒት አምራቾች ኢንስፔክሽንና ሕግ ማስፈጸም ክፍል መሪ አስፈጻሚ አቶ ጌታቸው ገነቴ ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ […]

በአማራ ክልል የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን የሚቀበሉበትን ጊዜ ማራዘማቸው ተሰማ

ማኅበራዊ በአማራ ክልል የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን የሚቀበሉበትን ጊዜ ማራዘማቸው ተሰማ ተመስገን ተጋፋው ቀን: October 9, 2024 በፀጥታ ችግር ምክንያት የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ነባር የቅድመና የድኅረ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎችን የሚቀበሉበትን ጊዜ ማራዘማቸው ታወቀ፡፡ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የአካዴሚ ፕሮግራም ዳይሬክተር ሰዋለም ሙሌ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በየመንገዱ የሚታየው የፀጥታ ችግር ምክንያት ተማሪዎችን በተፈለገው ጊዜ መቀበል አልተቻለም፡፡ በደባርቅ አካባቢ ከመስረከም 1 እስከ […]

ሰላሳ ሦስት ዓመታት የተሻገረ የብሔር ፖለቲካ የግል ትዝታና ትዝብት በኢትዮጵያ (ግንቦት 1983 – ጥቅምት 2017 ዓ.ም.)

ልናገር ሰላሳ ሦስት ዓመታት የተሻገረ የብሔር ፖለቲካ የግል ትዝታና ትዝብት በኢትዮጵያ (ግንቦት 1983… አንባቢ ቀን: October 9, 2024 በሁሴን አዳል መሐመድ (ዶ/ር)  የብሔር ፖለቲካ የትናንት፣ ዛሬና ነገ ትስስር ፋይዳን  የማያገናዝብ ግትር  ኋላቀር ፖለቲካ ነው። ዛሬ ላይ ሆኖ ስለነገው ለመተንበይ ትናንትን ጭምር  ማወቅ ያስፈልጋል። ትናንትን በጭፍን ጥላቻ ማየት ዛሬ የቆምንበትን መሠረት በመናድ ነገን በትክክል የምናይበትን ዓይናችንን […]

የዘመመችው የመምህራን ጎጆ

ልናገር የዘመመችው የመምህራን ጎጆ አንባቢ ቀን: October 9, 2024 በአንዋር አወል ሞ. ባሳለፍነው ሳምንት አነጋጋሪ ከነበሩ ማኅበራዊ ጉዳዮች አንደኛው ቢቢሲ የአማርኛው ክፍል ዕጩ ዶክተሮች የሚገፉት አሰቃቂ ኑሮን አስመልክቶ የሠራው ዘለግ ያለ ሐተታ ነበር፡፡ ጽሑፉን ተከትሎም አዳሜ ለአንድ ለሦስት ቀን ሌላ አጀንዳ አልነበረውም፡፡ አብሶ በትምህርት ቤቶች አካባቢ ‘ኤጭ! አሁንስ በዛ!’ እስክንል ድረስ አየሩን የተቆጣጠረው ርዕሰ ጉዳይ […]

የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ሥጋትና ጦሱ

የእሳት አደጋ ሠራተኞች በሮኬት ጥቃት የተፈጠረውን እሳት ሲያጠፉ ዓለም የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ሥጋትና ጦሱ በጋዜጣዉ ሪፓርተር ቀን: October 9, 2024 እስራኤል የኦክቶበር ሰባቱን የሐማስ ጥቃት አንድ ዓመት ባሰበችበት ሰኞ ዕለት፣ ሂዝቦላህ ሃይፋ በተሰኘች ግዛቷ ባደረገው የሚሳይል ጥቃት ከአሥር በላይ እስራኤላውያን ተገድለዋል፡፡  ባለፈው ሳምንት በዕለተ ማክሰኞ ኢራን በእስራኤል ላይ 200 ያህል ሚሳይሎችን አስወንጭፋ በተወሰነ ደረጃ የእስራኤል […]