አሜሪካ ለደቡብ ሱዳናውያን የሰጠችውን ቪዛ በሙሉ ሰረዘች

ከ 8 ሰአት በፊት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ደቡብ ሱዳን ከአሜሪካ የተባረሩ ዜጎቿን ለመቀበል ዳተኛ በመሆኗ ምክንያት የደቡብ ሱዳን ፓስፖርት ለያዙ የተሰጠ ማንኛውም ቪዛ መሰረዙን አስታወቁ። ሩቢዮ ቅዳሜ ዕለት በሰጡት መግለጫ አገራቸው ማንኛውም የደቡብ ሱዳን ዜጋ ወደ አሜሪካ በየትኛውም መንገድ እንዳይገባ እንደምታግድ ተናግረዋል። “የደቡብ ሱዳን የሽግግር መንግሥት ወደ አገራቸው የሚመለሱ ዜጎቹን በወቅቱ ባለመቀበሉ” […]

እስራኤል በጋዛ በሕክምና ባለሙያዎቹ ላይ በተፈፀመው ግድያ ስህተት መስራቷን አመነች

ከ 6 ሰአት በፊት የእስራኤል ጦር ወታደሮቹ በደቡባዊ ጋዛ መጋቢት 14/2017 ዓ.ም. በ15 የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ግድያ ላይ ስህተት መሥራታቸውን አመነ። የፍልስጤም ቀይ ጨረቃ ማሕበር አምቡላንሶች፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የእሳት አደጋ መኪና በራፋህ አቅራቢያ በእስራኤል ጦር የተኩስ እሩምታ ተከፍቶባቸው 15 የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ተገድለዋል። እስራኤል መጀመሪያ ላይ ወታደሮቿ ተኩስ የከፈቱት መኪኖቹ የፊት መብራትና የአምቡላንስ […]

“እጃችሁን አንሱ” በሚል በዩናይትድ ስቴትስ ዋና ዋና ከተሞች ፀረ-ትራምፕ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ

ከ 6 ሰአት በፊት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጥር ወር መንበረ ስልጣኑን ከተረከቡ ወዲህ ትልቅ ነው የተባለ የተቃውሞ ሰልፍ በዩናይትድ ስቴትስ በሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች ተካሄደ። “የእጃችሁን አንሱ” የተቃውሞ መሪዎች በ50 የአሜሪካ ግዛቶች በሚገኙ በአንድ ሺህ 200 አካባቢዎች ሰልፎችን ለማድረግ አስበው ነበር። በቦስተን፣ ቺካጎ፣ ሎስ አንጀለስ፣ ኒውዮርክ እና ዋሽንግተን ዲሲን ጨምሮ በሌሎች ከተሞችም በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች […]

ሁለት የእንግሊዝ የፓርላማ አባላት ወደ እስራኤል እንዳይገቡ ተከለከሉ

ከ 6 ሰአት በፊት እስራኤል ሁለት የብሪታንያ የሕዝብ እንደራሴዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ወደ አገሯ እንዳይገቡ መከልከሏን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዴቪድ ላሚ ቅዳሜ ዕለት ባወጡት መግለጫ አስታወቁ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ አባላት ወደ እስራኤል ያቀኑት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ነበር ተብሏል። የእስራኤል ባለስልጣናት ሁለት የሌበር ፓርቲ የፓርላማ አባላት ወደ አገሯ እንዳይገቡ መከልከሏን እና ማሰሯን የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ […]

“ሆስፒታል ውስጥ ከሌላ ልጅ ጋር መቀያየሬን በ70 ዓመቴ አወቅኩ”

ከ 8 ሰአት በፊት ሱዛን የዘረ መል መመርመሪያ መሣሪያ ገዝታ ነበር በቤቷ ምርመራ ያደረገችው። ውጤቱን ስታይ ማመን ተሳናት። አሁን በ70ዎቹ አጋማሽ ላይ ትገኛለች። ስለ አያቷ ብዙም አታውቅም ነበር። “ከአየርላንድ የሚመዘዝ የዘር ግንድ እንዳለ ባስተውልም ስህተት ይመስለኝ ነበር” ትላለች። ነገሩን ችላ ብላው ብትቆይም የኋላ ኋላ እውነታውን ማወቋ አልቀረም። ስለ ቤተሰቧ የምታውቀው ሁሉ ስህተት መሆኑን ደርሳበታለች። በ1950ዎቹ […]