በብራዚል በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ ሁሉም ተሳፋሪዎች ሞቱ

ከ 4 ሰአት በፊት በብራዚል፣ ሳዎ ፖሎ ግዛት በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ ሳቢያ 61 ሰዎች ሞቱ። ካስካቫል ከተባለ አካባቢ ወደ ሳዎ ፖሎ ጉአርሎስ አውሮፕላን ማረፊያ እየተጓዘ ነበር። የተከሰከሰው ቪንሄዶ የተባለ ከተማ ውስጥ እንደሆነ አየር መንገዱ አስታውቋል። ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አውሮፕላኑ ወደ መሬት ሲምዘገዘግ የሚያሳዩ ቪድዮዎች ወጥተዋል። ኤቲአር 72-500 አውሮፕላኑ 57 ተሳፋሪዎችና 4 የበረራ ሠራተኞች ይዞ ነበር። […]

አልጄሪያዊቷ ቦክሰኛ ኢማኔ ኸሊፍ የወርቅ ሜዳሊያ አሸነፈች

ከ 4 ሰአት በፊት በዘንድሮው የፓሪስ ኦሎምፒክ ከፍተኛ ውዝግብን ያስተናገደችው አልጄሪያዊቷ ቦክሰኛ ኢማኔ ኸሊፍ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆነች። ባለፈው ዓመት በተካሄደው የሴቶች የዓለም ቦክስ ሻምፒዮና ላይ የጾታ ብቃት መመዘኛ ፈተናዎች አላለፉም በሚል ከታይዋኗ ቦክሰኛ ሊን ዩ ቲንግ ጋር በውድድሩ እንዲታገዱ ከመደረጋቸው ጋር ተያይዞ በፓሪስ ኦሎምፒክስ መወዛገቢያ ሆነው ነበር። ይህንንም ተከትሎ ዘረኛ እና ጾተኛ የሆኑ ዘለፋዎችን […]

ከአገር የኮበለሉት የባንግላዴሽ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ አገራቸው እንደሚመለሱ ልጃቸው ተናገረ

ከ 4 ሰአት በፊት በህዝባዊ ተቃውሞ ከአገር የኮበለሉት የባንግላዴሽ ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ ሃሲና ምርጫ ሲታወጅ ወደ አገራቸው እንደሚመለሱ ልጃቸው ሳጂብ ዋዜድ ጆይ ተናገረ። አድሏዊ በተባለ የመንግሥት የስራ ቅጥር ኮታ ጋር ተያይዞ በተነሳው የተማሪዎች ተቃውሞን ተከትሎ በተነሳው ከፍተኛ ሁከት የተነሳ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ስልጣን ለቀው ወደ ህንድ ኮብልለዋል። ለሳምንታት በዘለቀው ህዝባዊ ተቃውሞ የተነሳ ከ500 በላይ ሰዎች የተገደሉ […]

በዚምባብዌ የ11 ዓመት ልጃቸውን በመኪና ገጭቶ የገደለው አሜሪካዊ ዲፕሎማት ይቅርታ እንዲጠይቅ ቤተሰቦቿ ተማፀኑ

ከ 4 ሰአት በፊት የ11 ዓመት ልጃቸውን በመኪና የገጨው አሜሪካዊ ዲፕሎማት ይቅርታ እንዲጠይቃቸው ቤተሰቦቿ ተማፀኑ። ልጃቸውን አሜሪካዊው ዲፕሎማት እንደገጨ ይታመናል። ቤተሰቦቿም ዲፕሎማቱ ወደ ዚምባብዌ ተመልሶ በአካል ይቅርታ እንዲላቸው ጠይቀዋል። ዲፕሎማቱ ያለመከሰስ መብት እንዳለው ቢያውቁም ቤተሰቡን ይቅርታ ማለት እንዳለበት ተናግረዋል። ሩቫራሺ ታካማሃንያ የተባለችው ታዳጊ በዲማ ከተማ ወደ ትምህርት ቤት እየሄደች ሳለ ዲፕሎማቱ እየነዳው በነበረ መኪና መገጨቷ […]

በኦሊምፒክ ላይ ውዝግብ ስላስነሳው የአልጄሪያዊቷ ቦክሰኛ የፆታ ጉዳይ ሳይንስ ምን ይላል?

ከ 5 ሰአት በፊት የአልጄሪያዊቷ ቦክሰኛ ኢማን ኸሊፍ እና የታይዋኗ ሊን ዩ-ቲንግ የሜዳሊያ ሥነ ሥርዓት ምሥሎች ከፓሪስ ኦሊምፒክ አይረሴ ዝርዝሮች ውስጥ እንደሚገቡ ይጠበቃል። ባለፈው ዓመት በተካሄደው የሴቶች የዓለም ሻምፒዮና ውድድር መስፈርቶችን ባለማሟላታቸው ሁለቱም ከውድድሩ ውጪ ተደርገው ነበር። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሁለቱን ቦክሰኞች በፓሪስ የሴቶች ቦክስ ውድድር እንዲካፈሉ ማድረጉ የማያባራ ክርክር አስነስቷል። ክርክሩ በጦፈበት በዚህ […]