ኢቮን አኪ ሳውይር የ 2024 የጀርመን አፍሪቃ ሽልማት አሸናፊ

September 25, 2024 – DW Amharic  የጀርመን አፍሪቃ ድርጅት እንደሚለው አኪ ሳውይር በፕሮጀክቶቻቸው በቱሪዝም፣ በቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ መሠረተ ልማትን በማስፋፋት፣ እና በአረንጓዴ ኤኮኖሚ የስራ እና የውረታ ወይም የኢንቬስትመንት እድሎችን እየፈጠሩ ነው። ከዚህ ሌላ በትራንስፖርት ዘርፍም አዳዲስ ሃሳቦችን ያፈልቃሉ። … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

በዓለማችን ከሶስት ሕፃናት አንዱ ‘አርቆ የማየት ችግር’ እንዳለባቸው አንድ ጥናት ጠቆመ

ከ 2 ሰአት በፊት በዓለማችን ከሶስት ሕፃናት አንዱ ቅርባቸው ያለ ነገር እንጂ አርቀው ማየት አንደማይችሉ አንድ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተሠራ ጥናት አመለከተ። አጥኚዎቹ እንደሚሉት የኮቪድ ወረርሽኝ በሕፃናት ዕይታ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳድሮ ያለፈ ሲሆን ሕፃናት ወጣ ብለው ከመጫወት ይልቅ ስክሪን ላይ ብዙ ሰዓት ማሳለፋቸው ጎድቷቸዋል። ራቅ ያለ የማየት ችግር አሊያም በሳይንሳዊ አጠራሩ ማዮፒያ ዓለማችንን የሚያሰጋት […]

በእስራኤል የአየር ጥቃት ስር በምትገኘው ሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በምን ሁኔታ ላይ ናቸው?

ከ 3 ሰአት በፊት እስራኤል ተደጋጋሚ ጥቃት እየፈፀመችባት ባለችው ሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስጋት ላይ መሆናቸውን ለቢቢሲ ገለፁ። ቢቢሲ ካነጋገራቸው በቤይሩት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መካከል አንዷ የሆነችው ትዝታ ነዋሪነቷ በደቡባዊ ሊባኖስ ቢሆንም የእስራኤል ጥቃት ግን እርሷ ከምትኖርበት ራቅ ያሉ አካባቢዎች ላይ እየደረሰ መሆኑን ተናግራለች። የአየር ድብደባ ሲደርስ እርሷ በምትኖርበት አካባቢ እንደሚሰማ፣ ከአየር ድብደባው የተነሳ ቤቶች እንደሚነቃነቁም ትናገራለች። […]

ግብፅ ለሶማሊያ ያስታጠቀችው ከባድ መሳሪያ ያስከተለው ውጥረት

ከ 3 ሰአት በፊት ካለፈው እሁድ መስከረም 12/2017 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሰኞ ድረስ የሞቃዲሾ ወደብ ዝግ ሆኖ መቆየቱን የወደቡ ሠራተኞች ይናገራሉ። ነገር ግን የግብፅ የጭነት መርከብ ወደ ወደቡ ደርሳ ጭነቷን እስክታራግፍ ድረስ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ፈጽሞ አላወቁም ነበር። በወደቡ የተራገፉት የጦር መሳሪያዎች በከባድ መኪና ተጭነው እና እየተጎተቱ በከተማዋ ጎዳናዎች ላይ ሲተላለፉ ነበር፣ የወደቡ መደበኛ እንቅስቃሴ […]

አሜሪካዊው ራፐር ዲዲ 11ኛ ክስ ቀረበበት

ከ 2 ሰአት በፊት ሴቶችን ለወሲብ ንግድ በማዘዋወር ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር የዋለው አሜሪካዊው ራፐር ዲዲ (ሾን ዲዲ ኮምብስ) የፍርድ ቤት ቀጠሮ እየተጠባበቀ ባለበት ወቅት 11ኛ ክስ ቀረበበት። 11ኛዋ ከሳሽ ታሊያ ግሬቭስ ስትሆን እአአ በ2001 ዲዲ እና የግል ጠባቂው አደንዛዥ መድኃኒት ሰጥተው እንደደፈሯትና ድርጊቱንም በቪድዮ እንደቀረፁት ተናግራለች። ዲዲ ላይ የቀረቡት ክሶች ከ1990ዎቹ የጀመሩ ናቸው። ራፐሩ ወንጀሎቹን […]

እስራኤል ሊባኖስ ላይ የፈጸመችው ጥቃት ‘እልቂት’ አስከትሏል ሲል የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ

ከ 2 ሰአት በፊት የሊባኖስ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በአገራቸው እየተፈጸመ ያለውን የእስራኤል የአየር ጥቃት “እልቂት” ሲሉ ገለጹ። እስራኤል ለሁለት ቀናት በታጣቂው የሄዝቦላህ ቡድን ላይ በፈጸመችው ጥቃት ሆስፒታሎች ተጎጂዎችን ለማስተናገድ እየታገሉ ነው ተብሏል። ሰኞ ዕለት በጥቃቱ ከተገደሉት 550 ሰዎች መካከል ህጻናትና ሴቶችን ጨምሮ አብዛኛዎቹ ሲቪሎች መሆናቸው “ግልጽ” ነው ሲሉ ዶክተር ፊራስ አቢያድ ለቢቢሲ ተናግረዋል። እስራኤል በበኩሏ […]