በአሙሩ ወረዳ በታጣቂዎች በደረሰ ጥቃት ሶስት ሰዎች ተገደሉ

June 8, 2024 – DW Amharic  በሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ ከትናንት በስቲያ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች አስታወቁ፡፡ በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎች በሞተር ሳይክል ወደ አጋምሳ ከተማ ሲጓዙ እንደነበር ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የሙቀቱ መጨመር በድሬ ዳዋ በህመምተኞች ላይ ስጋት አሳድሯል

June 8, 2024 – DW Amharic  በድሬደዋ የሚስተዋለው የሙቀት መጨመር ነዋሪውን እንደ ደም ግፊት ባሉ በሽታዎች ለሚታመሙ ሰዎች ስጋት መፍጠሩን ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። በቁጥር ደረጃ ጉልህ ባይባል እንኳ በአየር ሁኔታው ላይ ለውጥ መኖሩን የሚቲዎሮሎጂ ተቋም አስታውቋል። በዚህም በአስተዳደሩ የመንግስት ሰራተኞ የስራ ሰዓት መግቢያ እና መውጫ ላይ ማሻሻያ ተደርጓል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

«ኮሮናን ማመስገን ባይቻልም ትክክለኛው ፍላጎቴን ያሳየኝ ነው»

June 8, 2024 – DW Amharic  ኑሃሚን ትርፌ በአጭር ጊዜ ውስጥ በፋሽን ዲዛይን ስራ ተሰማርታ ስራዎቿን ከሀገር ውጪ ድረስ ለማስተዋወቅ የበቃች ወጣት ኢትዮጵያዊት ናት። በቅርቡ ናይሮቢ በተካሄደው የምስራቅ አፍሪቃ የጨርቃጨርቅ እና የቆዳ ዓውደ ርዕይ ስላቀረበቻቸው ስራዎቿ እና «ዕውን አደረኩት» ስለምትለው የልጅነት ህልሟ የምትለን ይኖራል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የመጪው 2017 በጀት ከዘንድሮው በ169.5 ቢሊዮን ብር የበለጠ ሆኖ ተዘጋጀ

7 ሰኔ 2024 የሚኒስትሮች ምክር ቤት፤ የ2017 ዓ.ም. በጀት ዓመት “አንድ ትሪሊዮን [ብር] የሚጠጋ” እንዲሆን ወሰነ። ለቀጣዩ በጀት ዓመት የተዘጋጀው የአገሪቱ በጀት 971.2 ቢሊዮን ብር መሆኑን ቢቢሲ ከገንዘብ ሚኒስቴር ምንጭ ተረድቷል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀጣዩ ዓመት በጀት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳለፈው ዛሬ አርብ ግንቦት 30/2016 ዓ.ም. እንደሆነ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የ2017 […]

አዲሱ የጥምር መንግሥት በደቡብ አፍሪካ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ምን ይዞ ይመጣ ይሆን?

ከ 7 ሰአት በፊት የጨቋኙ የአፓርታይድ ሥርዓት መገርሰስ ለሰውነታቸው መታወቂያ ሲታገሉ ለነበሩ ደቡብ አፍሪካውያን የነጻነት ችቦን የፈነጠቀ ነበር። ከሰው በታች አድርጎ በቆዳ ቀለማቸው ምክንያት ያወረዳቸውን፣ ክብርን የነፈጋቸውን ሥርዓት ታግለው የጣሉበት ድል ነው። የበርካታ ጥቁሮች ተስፋ በለመለመበት የመጀመሪያው ምርጫ የነጻነት ታጋዩ ኔልሰን ማንዴላ ወደ ሥልጣን መጡ። ደቡብ አፍሪካውያንም የነጻነት ተምሳሌት ያደረጉት የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኤኤንሲ) ሥልጣን […]

ተመድ የእስራኤልን ጦር በህጻናት ላይ ጥሰቶችን በሚፈጽሙ ዝርዝር ውስጥ አካተተ

ከ 6 ሰአት በፊት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የእስራኤል ጦር በህጻናት ላይ ጥሰቶችን በሚፈጽሙ ዝርዝር ውስጥ እንዲካተት ውሳኔ አስተላለፈ። የመንግሥታቱ ድርጅት ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈው ከመስከረም 26 በኋላ በጋዛ በእስራኤል ጥቃት የተገደሉ ህጻናት ከ15 ሺህ 500 በላይ መሆናቸው ከተገለጸ በኋላ ነው። የእስራኤል ጦር ህጻናትን ከጉዳት መከላከል ባለመቻሉ በጥሰት ፈጻሚነት ዝርዝር ውስጥ መካተቱን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የእስራኤል አምባሳደር […]

የዴንማርኳ ጠቅላይ ሚኒስትር በኮፐንሃገን ጎዳና ጥቃት ደረሰባቸው

ከ 5 ሰአት በፊት የዴንማርኳ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜቴ ፍሬድሪክሰን በመዲናዋ ኮፐንሃገን ጎዳና ላይ በአንድ ግለሰብ ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ቢሯቸው አስታወቀ። ከጥቃቱ በኋላም ጠቅላይ ሚኒስትሯ “በከፍተኛ ሁኔታ መደናገጣቸውን”ም እንዲሁ ቢሯቸው አክሏል። ጥቃቱ የተፈጸመው በከተማዋ ማዕከል በሚገኝ አደባባይ ላይ ሲሆን አንድ ግለሰብ ወደ እሳቸው በማምራት መትቷቸዋል። የመታቸው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏል። የአውሮፓ ኮሚሽን ኃላፊ ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን […]