በመስቀል ላይ የሚፈጸም ስቅላት እንዴት እና የት ተጀመረ?

14 ሚያዚያ 2023 ተሻሽሏል ከ 5 ሰአት በፊት በክርስትና እምነት ተከታዮች ከትንሳኤ ዕለት የምትቀድመዋን ዕለተ አርብ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት ቀን በማለት በየዓመቱ ያስቧታል። ይህች ዕለትም ከብዙ እንግልት እና ስቃይ በኋላ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጅ ከተዘፈቀበት ሃጥያት ለማንጻት ሲል በመስቀል ላይ የከፈለው የመስዋዕትነት የሚዘከርባት ናት። የእምነቱ ተከታዮችም ዕለቱን ኢየሱስ ለሰው ልጆች ፍቅር ሲል ራሱን አሳልፎ የሰጠበት […]

በጋዛ እየተፈጸመ ባለው ጥቃት ምክንያት ቱርክ ከእስራኤል ጋር ያላትን የንግድ ግንኙነት አቋረጠች

3 ግንቦት 2024, 08:03 EAT ተሻሽሏል ከ 4 ሰአት በፊት እስራኤል በጋዛ እየፈጸመችው ያለው የማያባራ ጥቃት “እጅግ እየከፋ እና የሰብአዊ ሰቆቃ ማስከተሉን” በመጥቀስ ቱርክ ከእስራኤል ጋር ያላትን ሁሉን የንግድ ግንኙነቶች አቋረጠች። እስራኤል “ያልተስተጓጎለ እና በቂ የእርዳታ ፍሰትን” ወደ ጋዛ እንዲገባ ካልፈቀደች በስተቀር ይህ ውሳኔ ጸንቶ እንደሚቆይ የቱርክ የንግድ ሚኒስትር አስታውቋል። በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የንግድ […]

የ75 ሺህ ዓመቷ ኒያንደርታል ሴት ፊት ይፋ ሆነ

ከ 5 ሰአት በፊት ከዛሬ 75 ሺህ ዓመታት በፊት ከነበሩ የቅርብ ዘመዶቻችን አንዱን በአካለ ሥጋ ብናገኘው ምን ይመስል ይሆን? የሳይንስ ሊቃውንት የኒያንደርታል ሴት በህይወት እያለች ምን እንደምትመስል የሚያሳይ አስደናቂ ምስል አዘጋጅተዋል። መሠረት ያደረጉት ደግሞ በቁፋሮ የተገኘ ለስላሳ አጥንት ላይ ነው። ተመራማሪዎች አጥንቶቹን እንደገና ከመገጣጠማቸው በፊት ማጠናከር ነበረባቸው። በኋላም ባለሙያዎች ልዩ የ3ዲ ሞዴል ለማዘጋጀት በቁ። ሞዴሌ […]

44 ቢሊዮን ዶላር አጭበርብራለች ተብላ ሞት የተፈረደባት ቬትናማዊት ሴት ማን ነች?

ከ 5 ሰአት በፊት በቅርቡ ከቬትናም የተሰማው የወንጀል ታሪክ ብዙዎችን ያነጋገረ ነው። ቬትናማዊት ቢሊየነር ቾንግ ሚ ላን ተሰምቶ በማይታቅ ሁኔታ በ44 ቢሊዮን ዶላር የማጭበርበር ወንጀል ጥፋተኛ ተባለ ሞት ተፈርዶባታል። ብዙዎችን ያስደነቀው የተላለፈባት የሞት ፍርድ ሳይሆን፣ እንዴት 44 ቢሊዮን ዶላር ማጭበርበር ይቻላል የሚለው ነበር። ቼንግ ሚላን ይህ የኢትዮጵያን የሦስት ዓመት በጀት ሊሆን የሚችል ገንዘብ ማጭበርበር የቻለችው […]

የጸጥታ ኃይሎቿ ታዳጊዋን ወሲባዊ ጥቃት አድርሰው ገድለዋታል በሚለው የቢቢሲ ዘገባ የተነሳ ኢራን ጋዜጠኞችን ከሰሰች

ከ 3 ሰአት በፊት የኢራን የጸጥታ ኃይል አባላት የሆኑ ግለሰቦች የ16 ዓመቷን የመንግሥት ተቃዋሚ ታዳጊ ወሲባዊ ጥቃት ፈጽመው እንደገደሏት ቢቢሲ በምርመራ ዘገባ ማውጣቱን ተከትሎ ኢራን በጋዜጠኞች እና ተሟጋቾች ላይ ክስ መሰረተች። ክስ የተመሰረተባቸው ግለሰቦች ቢቢሲ በአውሮፓውያኑ 2022 ህይወቷ ባለፈው ኒካ ሻካራሚ ግድያን አስመልክቶ ለሰራው ዘገባ ያናገራቸው ጋዜጠኞች ተካትተውበታል። በኢራን የፍትህ አካል የሚተዳደረው ሚዛን የተሰኘው የዜና […]

በኬንያ እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ የተነሳ በግድብ አቅራቢያ የሚገኙ ሰዎች አካባቢያቸውን እንዲለቁ ታዘዙ

ከ 2 ሰአት በፊት የኬንያ መንግሥት እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ በ178 ግድቦች እና የውሃ ማቆሪያዎች (reservoirs) አቅራቢያ የሚኖሩ ሰዎች አካባቢያቸውን እንዲለቁ ትዕዛዝ አስተላልፏል። በኬንያ የውሃ አካላት ከመጠን በላይ ስለሞሉ ወይም ሊሞሉ በመቃረባቸው ጎርፍ ሊከሰት እንደሚችል የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር ገልጿል። በዚህም ሳቢያ በነዚህ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደሆኑ አስጠንቅቋል። ከውሃ አካላት አቅራቢያ […]