የማህሙድ አህመድ የስልሳ ዓመታት የሙዚቃ ሕይወት ጉዞ

November 29, 2024 – VOA Amharic  ገና በአፍላ ዕድሜው ያደረበትን የሙዚቃ ፍቅር ይዞ አደባባይ የወጣው አንጋፋው ድምጻዊ ማህሙድ አህመድ ትውልድ ተሻግረው ዛሬም ድረስ እንደ አዲስ የሚሰሙ ሙዚቃዎችን እየተጫወተ እዚኽ ደርሷል። የኢትዮጵያን የሙዚቃ ባህል በዓለም አቀፍ የሙዚቃ መድረኮች ማስተዋወቅ ብቻ ሳይሆን፤ ሙዚቃውን የሚጫወቱ ቁጥራቸው የበዙ አውሮፓውያን እና አሜሪካውያን ሙዚቀኞችም አፍርቷል። ዩናይትድ ስቴትስን እና ካናዳን … … ሙሉውን ለማየት […]

ጁባላንድ ከሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ጋራ ያላትን ግንኙነት ማቋረጧን አስታወቀች

November 29, 2024 – VOA Amharic  በሶማሊያ አንድ የፌዴራሉ ዓባል የሆነ ግዛት ከማዕከላዊ መንግሥት ጋራ ያለውን ግንኙነት ማቋረጡን ተከትሎ በሃገሪቱ የሚታየው የፖለቲካ ቀውስ ተባብሷል። በሶማሊያ ከሚገኙ ስድስት የፌዴራሉ ዓባል ግዛቶች ውስጥ አንዷ የሆነችው በደቡብ የምትገኘው ጁባላንድ ከፌዴራል መንግሥቱ ጋራ ያላትን ግንኙነት ማቋረጧን በይፋ አስታውቃለች፡፡  ይላል የግዛቲቱ ካቢኔ ስብሰባን ተከትሎ ዛሬ ከኪሲማዮ የወጣው መግለጫ… … ሙሉውን ለማየት ወይም […]

አማራ ክልል ከ4.7 ሚሊዮን ተማሪዎች አይማሩም

November 28, 2024 – DW Amharic  አማራ ክልል በፌደራሉ መንግሥት ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በሚደረገዉ ዉጊያ4.7 ሚልየን ህፃንት መማር አለመቻላቸዉን የአማራ ክልል የከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት መድረክ ወይም ፎረም አስታወቀ።መድረኩ እንደሚለዉ በክልሉ 969 የጤና ተቋማት ውድመት።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የሶማሊያዋ ጁባላንድ ክልል ከፌደራሉ መንግሥት ጋር ያለኝን ግንኙነት አቋርጫለሁ አለች

ከ 2 ሰአት በፊት ከምርጫ ጋር በተያያዘ በማካሄዷ ከሶማሊያ የፌደራል መንግሥት ጋር ውዝግብ ውስጥ የገባችው ከፊል ራስ ገዟ የጁባላንድ ክልል ከፌደራሉ መንግሥት ጋር ያላትን ግንኙነትም ሆነ ትብብር ማቋረጧን አስታወቀች። ጁባላንድን ከአውሮፓውያኑ 2013 ጀምሮ የመሩት የፕሬዚዳንት አህመድ መሐመድ ኢስላም ወይም ማዶቤ አስተዳደር የሶማሊያ መንግሥት ሕገ መንግሥቱን እየጣሰ እንዲሁም የሕዝቡን አንድነት እያናጋ ነው ሲልም ወንጅሏል። ኬንያ እና […]

መንግሥት እያደረጋቸው ያሉ የሕግ ማሻሻያዎች እና የፈጠሩት ስጋት

ከ 6 ሰአት በፊት ባለፈው ሳምንት አጋማሽ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካሉት መሰብሰቢያዎች መካከል አንዱ የሆነው 52 ቁጥር አዳራሽ በሰዎች ተሞልቶ ነበር። በስብሰባ አዳራሹ የሕግ እና የሚዲያ ባለሙያዎች እንዲሁም የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች ተገኝተዋል። እነዚህ ሰዎች በአዳራሹ የተገኙት የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ረቂቅ ማሻሻያ ላይ ሕዝባዊ ውይይት ለማድርግ ነው። ከአንድ ወር ገደማ በፊት ለምክር ቤቱ የቀረበው […]

ፑቲን የዩክሬን ውሳኔ ሰጪ ማዕከላትን በአዲሱ ባለስቲክ ሚሳኤል እንደሚመቱ አስጠነቀቁ

ከ 5 ሰአት በፊት የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን መዲና ኪዬቭ የሚገኙ ውሳኔ ሰጪ ማዕከላት ላይ ኦሬሽኒክ በተሰኘው አዲሱ የአገሪቱ የባለስቲክ ሚሳኤል እንደሚመቱ አስጠነቀቀቁ። ዩክሬን ከአሜሪካ የተለገሰችውን አታካምስ ሚሳኤል በመጠቀም ሩሲያን ላይ እየፈጸመችው ያለውን ተከታታተይ ጥቃት ተከትሎ ፑቲን የተቀናጀ ነው ያሉትን አጸፋዊ ምላሽ መስጠት መጀመራቸውን ተናግረዋል። ሩሲያ በትናንትናው ሌሊት የዩክሬን የኃይል አቅርቦትን ከመታች በኋላ ነው […]

ከ60 በላይ ሴት ልጆችን የደፈረው የሕጻናት እንክብካቤ ሠራተኛ እድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት

ከ 4 ሰአት በፊት በአውስትራሊያ የሕጻናት እንክብካቤ ሠራተኛ የነበረ እና የከፋው የህጻናት ደፋሪ የሚል ስያሜ የተሰጠው ግለሰብ ወደ 70 የሚጠጉ ህጻናት ሴቶች ላይ የመድፈር እና ወሲባዊ ጥቃቶችን በመፈጸሙ የዕድሜ ልክ እስራት ተበየነበት። የ47 ዓመቱ አሽሊ ፖል ግሪፊት እአአ ከ2003 እስከ 2022 ባሉት ጊዜያት በአውስትራሊያዋ ኩዊንስላንድ ግዛት እና ጣሊያን ውስጥ በሚገኙ የህጻናት ማቆያ ማዕከላት 307 ወንጀሎችን […]

በአፍሪካ የሩሲያ ፕሮፖጋንዳ መሪ የሆነው ግለሰብ ለምን በቁጥጥር ሥር ዋለ?

ከ 6 ሰአት በፊት ከጥይት እና ከፍንዳታ ሲያመልጥ እንዲሁም የሀገራትን ብርቱ ምሥጢር ሲጠብቅ ይታያል። ቦምባስቲክ በቅርቡ የሠራው የፕሮፖጋንዳ ፊልም ማክሲም ሹጋሌይ የተባለውን ገፀ-ባህሪ ጀግና የሩሲያ የፖለቲካ ሰው አድርጎ ይስላል። ሰውዬው በውጭ ሀገራት ሀገሩን ለማስተዋወቅ የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። ምንም እንኳ ለፊልም ተብሎ ግነት ቢታከልበትም በእውነተኛው ዓለምም ቢሆን ይህ ሰው በአፍሪካ የሩሲያ ተፅዕኖ እንዲበረታ ብዙ አበርክቷል። በተለይ […]

የዚምባብዌ ፓርላማ ስለበጀት እየመከረ ሳለ መብራት ጠፋ

ከ 5 ሰአት በፊት በዚምባብዌ ፓርላማ የፋይናንስ ሚኒስትሩ ምቱሊ ንኩቤ ስለበጀት ንግግር እያደረጉ ሳለ መብራት ሙሉ በሙሉ ጠፍቶ በጨለማ ተውጦ እንደነበር ተዘገበ። በፓርላማው ይህ ክስተት ያጋጠመው መብራቱ ብልጭ ድርግም የማለት ምልክት ካሳየ በኋላ ነው የጠፋው። በዚህም ምክንያት ፕሬዝደንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ፣ ምክትል ፕሬዝደንት ኮንስታንቲኖ ቺዌንጋ እና ሌሎች የፓርላማ አባላት ጨለማ ውስጥ ለመቀመጥ ተገደዋል። መብራት በፈረቃ እያደለች […]