የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ወቅታዊ ሁኔታ

September 20, 2024 – DW Amharic  የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ጋር በቀጣናዊ ሰላም እና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ሰሞኑን ተወያይተዋል። ኢጋድ በሶማሊያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት መከበር ላይ ግልጽ አቋም እንዳለውና ይህም የድርጅቱ አባል ሃገራት እና መንግሥታት መሪዎች ያረጋገጡት መሆኑን ዋና ጸሐፊው ተናግረዋል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

በህወሃት መሪዎች መካከል የቀጠለው ውዝግብ

September 20, 2024 – DW Amharic  ህወሃት ውስጥ የተፈጠረው ውዝግብ እያደር እየጋለ መሄዱ እየታየ ነው። ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በተቃራኒ በቅርቡ ስብሰባ ያካሄደው ህወሃት አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የተወሰኑ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ማገዱን ይፋ አድርጓል። አቶ ጌታቸውም ህወሃት የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር ከሥልጣን ለማውረድ እየሠራ ነው በማለት ከሰዋል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

ለታጋቾች ማስለቀቂያ ብር ለመክፈል የሄዱ ግለሰቦች እራሳቸው በታጣቂዎች መታገታቸው ተሰማ

September 20, 2024  ከሳምንት በፊት በአርሲ ዞን ሲርካ ወረዳ 38 ሰዎች በጉዞ ላይ እያሉ በሸኔ ታጣቂዎች ታግተው መወሰዳቸው ይታወሳል፡፡ ታጣቂዎቹ ታጋቾችን ለመልቀቅ ከ250ሺህ እስከ 1 ሚሊየን ብር ድረስ የማስለቀቂያ ገንዘብ እንዲከፈላቸው መጠየቃቸውን ተከትሎም አንዳንድ የታጋች ቤተሰቦች ገንዘቡን ለመክፈል ወደ ተባሉበት ቦታ ማቅናታቸውን የሚገልጹት የመረጃ ምንጮች ገንዘብ አቀባዮቹ በቦታው ሲደርሱ ግን እራሳቸው በታጣቂዎቹ መታገታቸውን ነው የገለጹት […]

የቤት እድሳት ለማድረግ ለግንባታ ፈቃድ እስከ 100 ሺህ ብር ጉቦ እየተጠየቁ እንደሆነ የለሚ ኩራ ነዋሪዎች ተናገሩ

September 20, 2024  (መሠረት ሚድያ)- በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች ቤታቸውን ወይም የንግድ ሱቆቻቸውን ለማደስ ፈልገው የግንባታ ፈቃድ ሲጠይቁ እስከ 100 ሺህ ብር ጉቦ አምጡ እየተባሉ እንደሆነ ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል። “እኔ ለምሳሌ ሰሚት ፍየል ቤት አካባቢ ነዋሪ ነኝ፣ የንግድ ቤቴን ትንሽ ለማደስ ፈቃድ ጠይቄ 80 ሺህ ብር ስጠን ተብያለሁ” ያሉ አንድ […]

ኢትዮጵያን ዲጂታል የማድረግ ውጥን፡ ኢትዮ ቴሌኮም

September 20, 2024 – DW Amharic  በ2017 ዓ.ም. በኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚን መሰረተ ልማት ለመዘርጋት ከአንድ ቢሊየን በላይ የአሜሪካ ዶላር መመደቡን የኢትዮ-ቴሌኮም አስታወቀ። ኩባንያው የኔተዎርክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት ጥራት ላይም በዚህ ዓመት አተኩሮ እንደሚሠራ አሳውቋል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

በሊባኖስ በመልዕክት መቀበያ ስልኮች የደረሱ ፍዳታዎች ያደረሱት ጉዳት

September 19, 2024 – DW Amharic  በሊባኖስ ባለፈው ማክሰኞ በአነስተኛ የኤሌክትሮኒክስ መልክት ማስተላለፊያ መሳሪይዎች ወይም ፔጀርስ፤ በትናንትናው ዕለት ደግሞ በመገናኛ የእጅ ሬዲዮኖችና ኮምፕዩተሮችና መኪናዎች ጭምር በደረሱ ፍንዳታዎች እስካሁን 32 ሰዎች ሞተዋል፤ 3,500 የሚሆኑ ደግሞ ቆስለዋል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ