ፔንታገን በስህተት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢሜሎች የሩሲያ አጋር ወደሆነችው ማሊ ላከ
ከ 9 ሰአት በፊት ፔንታገን በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአሜሪካ ወታደራዊ የኢሜል መልዕክቶች በስህተት የሩሲያ አጋር ወደሆነችው ማሊ መላኩ ተገለጠ። መልዕክቶቹ መጨረሻው ‘. mil’ ወደተሰኘ ኢሜል መላክ ሲገባቸው በስህተት ‘.ml’ ወደሚል አድራሻ በመሄዳቸው ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሃገር ለዓመታት የአሜሪካን ወታደራዊ ኢሜል ስትቀብል ከርማለች። አንዳንዶቹ ኢሜሎች የይለፍ ቃል፣ የሕክምና ታሪክ እና የከፍተኛ ወታደሮች የጉዞ ዝርዝር መረጃ የተካተተባቸው ናቸው። ፔንታገን […]
የአውሮፓ ህብረት ስደትን ለመከላከል ከቱኒዝያ ጋር የ118 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ላይ ደረሰ
ከ 9 ሰአት በፊት በርካታ አፍሪካውያን ስደተኞችን አውሮፓ ለመድረስ የሚያቋርጧት ሰሜናዊቷ አፍሪካዊት አገር፣ ቱኒዝያ ስደትን ለመከላከል ከአውሮፓ ህብረት ጋር ስምምነት ላይ ደርሳለች። የአውሮፓ ህብረትና ቱኒዝያ የስደተኞች ዝውውርን ለመግታትና እንዲሁም መደበኛ ያልሆኑ ስደተኞችንም ለመመለስ የሚውል የ118 ዶላር የመግባቢያ ሰነድም ተፈራርመዋል። ቱኒዝያ የሜዲትራንያንን ባህር አቋርጠው ወደ አውሮፓ ለመግባት ለሚሞክሩ ስደተኞች ዋነኛ መሸጋገሪያም በመሆን እያገለገለች ይገኛል። በዘንድሮው የአውሮፓውያኑ […]
1999 የተመረተ አይፎን ስልክ 10.4 ሚሊዮን ብር ተሸጠ
18 ሀምሌ 2023, 07:33 EAT ለወትሮው አንድ ስልክ ከሱቅ ከወጣ ያለው ዋጋ ያሽቆለቁላል። ነገር ግን በአሜሪካው ጨረታ የታየው ሌላ ነው። የመጀመሪያው የአይፎን ዘር የሆነው ከሰገባው ያልወጣ ስልክ 190 ሺህ 372 ዶላር ከ80 ሳንቲም ተሽጧል። ይህ ገንዘብ አሁን ባለው የውጭ ምንዛሪ ተመን ብንመታው ከ10.4 ሚሊዮን በላይ ብር ነው። 4ጂቢ የተባለው የአይፎን ምርት ለገበያ ሲበቃ በገፍ አልነበረም። […]
ጥቃት የደረሰበት የክሪሚያ ድልድይ በከፊል መከፈቱን ሩስያ አስታወቀች
18 ሀምሌ 2023, 07:43 EAT ሩስያን ከክሪሚያ ጋር የሚያገናኘው ድልድይ ጥቃት ከደረሰበት ከአንድ ቀን በኋላ በከፊል መከፈቱን ሩስያ አስታወቀች። ለተሽከርካሪዎች በተወሰነ መልኩ አገልግሎት መስጠት መጀመሩንም ነው ባለስልጣናቱ ያስረዱት። ተሽከርካሪዎች የድልድዩን አንደኛውን ክፍል እየተጠቀሙ መሆናቸውንም ቪዲዮዎችን ያጋሩ አንድ ባለስልጣን ተናግረዋል። በድልድዩ ላይ በተፈጸመው ጥቃት በመዝናናት ላይ የነበሩ ሁለት ባልና ሚስት ሲገደሉ እንዲሁም ሴት ልጃቸው ቆስላለች። ጥቃቱ […]
በአውሮፓ እና በአሜሪካ አገራት የተከሰተው ከባድ የሙቀት ማዕበል እና ኢትዮጵያውያን
ከ 1 ሰአት በፊት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በማጋጠሙ ነዋሪዎች ከመደበኛ እንቅስቃሴያቸው ከመገታታቸው በተጨማሪ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ታዘዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪነታቸው በጣልያን የሆኑ ኢትዮጵያውያንም በአውሮፓ እየተመዘገበ ያለው ከፍተኛ የሙቀት ማዕበል በጣም በነዋሪው ላይ አስቸጋሪ ሁኔታ እየፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያውያኑ እንደሚሉት አሁን የተከሰተው ከባድ ሙቀት ቀዝቃዛ የአየር ንብረት ለተላመደው ሕዝብ ሕይወቱን […]
በአንድ ቀን 500 ሚሊየን ችግኝ ተከላ ???
July 18, 2023 – DW Amharic በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 500 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ያለመ ዘመቻ ዛሬ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ሲካሄድ ውሏል። … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
ለትግራይ ቤተክህነት ኤጲስቆጶሳት ምርጫ የሲኖዶስ ምላሽ
July 18, 2023 – DW Amharic ትናንት በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ የተከናወነው የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቤተ-ክህነት የኤጲስ ቆጶሳት መረጣ «ለቤተ ክርስትያንም፣ ለሀገርም ሆነ ለሰላም የማይበጅ ፣ ይልቁንም ቤተክርስትያንን እና ሀገርን የሚጎዳ ነው» ተባለ።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
በሱዳን ውጊያው ተፋፍሞ ቀጥሏል
ጁላይ 17, 2023 · ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የጦር ወንጀል ክሡን አስተባብሏል በሱዳን፣ ለሦስት ወራት የቆየው ጦርነት ተፋፍሞ፣ ትላንት እሑድ፣ መዲናዋ ካርቱም ውሎዋን በአየር ስትደበደብ፣ በምዕራብ ዳርፉር ደግሞ ከባድ ውጊያ እንደነበር ተገልጿል። የጦር ሠራዊቱ የውጊያ ጄቶች፣ በምሥራቃዊ እና ሰሜናዊ ምዕራብ ካርቱም የሚገኙ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን መደቦች ሲደበድቡ ውለዋል። ፈጥኖ ደራሽ ኀይሉ በበኩሉ፣ የአየር መቃወሚያ መተኮሱን፣ የዐይን […]
ሊቢያ በበረሓ ላይ የተጣሉ ፍልሰተኞችን ማግኘቷን አስታወቀች
July 18, 2023 – VOA Amharic የሊቢያ ድንበር ጠባቂዎች በደርዘን የሚቆጠሩ እና፣ በቱኒዚያ ባልሥልጣናት በረሃ ላይ ተጥለናል ያሉ የአፍሪካ ፍልሰተኞችን መታደጋቸውን አስታውቀዋል። ሴቶች እና ሕጻናትም እንደሚገኙበት ታውቋል። የቱኒዚያ ባለሥልጣናት ካለ ውሃ ምግብ እና መጠለያ በረሃ ላይ አምጥተው እንደጣሏቸው ፍልሰተኞቹ ለዜና ሰዎች ተናግረዋል። ሙሳ ካሊድ የተባለ ፍልሰተኛ ለአሶስዬትድ ፕረስ እንደተናገረው፣ የቱኒዚያ የጸ… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ […]
የትግራይ ክልል አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት የዕጩ ኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ አካሔዱ
ጁላይ 17, 2023 የትግራይ ክልል አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት የዕጩ ኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ አካሔዱ – ከተመረጡት አንዱ ቆሞስ አባ ሠረቀ ብርሃን ከአገር በግዳጅ መባረራቸውን ጊዜያዊ አስተዳደሩ ተቃወመ፤ በትግራይ ክልል የሚገኙ አራት ሊቃነ ጳጳሳት እና አህጉረ ስብከት፣ ትላንት በአኵስም ከተማ፣ የ10 ዕጩ ኤጲስ ቆጶሳትን ምርጫ አካሒደዋል፡፡ ራሱን፣ “የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን […]