አየር ማረፊያ ተውጦ፤ አዞዎች ከተማ መሐል የታዩበት የአውስትራሊያዋ ክዊንስላንድ ጎርፍ

ከ 5 ሰአት በፊት በታሪክ ከፍተኛው በተባለው ዝናብ ምክንያት የአውስትራሊያዋ ክዊንስላንድ ግዛት በጎርፍ ተጥለቅልቃለች። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከሥፍራው እንዲለቁ ሲደረግ በርካቶች አሁንም መንቀሳቀሻ አጥተው ተቀምጠዋል። ትሪፒካል ክሎን በተባለ የአየር ንብረት ክስተት የተከሰተው ዝናብ በአንዳንድ ሥፍራዎች ከፍተኛ ጎርፍ አስከትሏል። ከአካባቢው የሚወጡ ምስሎች በካይርንስ አየር ማረፊያ ያሉ አውሮፕላኖች በከፊል ተውጠው፤ መሐል ከተማ አዞዎች ሲዋኙ እና ነዋሪዎች በታንኳ […]

አብይ አህመድ የተዘፈቀበትን ቀውስ በትርዒት ጋጋታ የሚያመልጥ መስሎት በአየር ሃይል ቀን የኤሜሬትስ የአየር ትርዒት ቀርቧል። መሳይ መኮንን

December 17, 2023  መሳይ መኮንን ፦ በአየር ሃይል ቀን የኤሜሬትስ የአየር ትርዒት ቀርቧል። አብዛኛው ትዕይንት በውጭ ሀገር አየር ሃይል ትርዒት የታየበት ነው። የተወሰኑ ሄሊኮፕተሮች በሰማዩ ላይ ከመብረራቸው በቀር የታየው የኤሜሬትስ ሾው ነው። ለምን እንደዚያ ማድረግ እንዳስፈለገ ግራ የሚያጋባ ነው። ከበዓሉ አከባበር ጀምሮ መላ ቅጡ የጠፋበት ቀን ሆኖ ነው የዋለው። በመሰረቱ 88ዓመት ማክበር ለምን አስፈለገ? 10ኛ፥ 25ኛ፥ […]

‹‹የኢዜማ አባላት ባይለቁ ደስ ይለናል ነገር ግን የትግል ሥልትና የዓላማ ልዩነት ካለ ምን ማድረግ ይቻላል›› የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሙሉዓለም ተገኘወርቅ (ዶ/ር)

EthiopianReporter.com  ዮሐንስ አንበርብር December 17, 2023 ቆይታ የኢትዮጵያ ፖለቲካን ከብሔር ተፅዕኖ የማላቀቅ ትልም ይዞ የፖለቲካ ምኅዳሩን የተቀላቀለው የኢትዮጵያ ዜጎች ማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)፣ ከ2015 ዓ.ም. አጋማሽ ወዲህ ባሉት ጊዜያት ውስጥ በተለየ ሁኔታ የአባላት መልቀቅ እያጋጠመው ይገኛል። የኢዜማ አባላት በተደጋጋሚና ቀላል በማይባል ቁጥር ፓርቲያቸውን ጥለው የሚወጡበት ምክንያት በአሁኑ ወቅት የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኗል። የፓርቲው አባላት የሚለቁት ለምንድነው? በፓርቲው ውስጥ ባለ ውስጣዊ ችግር ነው? የሚለውንና በኢዜማ አጠቃላይ ወቅታዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ዙሪያ የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሙሉዓለም ተገኘወርቅ (ዶ/ር) ከዮሐንስ አንበርብር ጋር ያደረጉት ቆይታ እንደሚከተለው ተጠናቅሯል፡፡ ሪፖርተር፡- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢዜማ አመራሮችን ጨምሮ የፓርቲው አባላት በከፍተኛ ቁጥር እየለቀቁ መሆኑ እየተሰማ ነው። ምንድን ነው ምክንያቱ? ይህ ጉዳይ ፓርቲያችሁ ላይ ሊፈጥር የሚችለው ችግር አይኖርም ወይም አያሳስባችሁም? ዶ/ር ሙሉዓለም፡– የተለያዩ ሚዲያዎችና የተለያዩ አባለት በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻቸው ላይ እንዲህ ዓይነት መልዕክት ሲያስተላልፉ እናያለን። ነገር ግን የኢዜማን አደረጃጀት ካለመረዳት የመነጨ ነው ብለን እናስባለን። ሪፖርተር ጋዜጣም ይህንን የአባላት መልቀቅ በተመለከተ ያወጣው የተሳሳተ ዘገባ አለ፣ መስተካከልም አለበት ብለን እናምናለን። በመሠረታዊነት የኢዜማ አደረጃጀት በምርጫ ክልል ደረጃ ነው። የፓርቲው […]

የመንግሥትና የፓርቲ መዋቅሮች ፅዳት ይሻሉ!

December 17, 2023 – EthiopianReporter.com ከትናንት እስከ ዛሬ የፖለቲካ ክስረቶቻችን ማሳያዎች ብዙ ናቸው፡፡ የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆነ የፖለቲከኞች መስተጋብር በመርህ ላይ ያልተመሠረተ በመሆኑ፣ ልዩነትን ማስተናገጃ በርካታ አዎንታዊ አማራጮች እያሉ አሉታዊ ነገሮች ላይ ማተኮር ይበዛል፡፡ የብዙዎቹ የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጣዊ ግንኙነት በዴሞክራሲ ዓምዶች ላይ ያልተመሠረተ ስለሆነ፣ አለመግባባት ሲያጋጥም በስክነት ጊዜ ወስዶ ከመነጋገር ይልቅ ትርምስ መፍጠር የተለመደ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ኢትዮጵያ […]

ወርቅ – የግለሰቦችና የታጣቂ ቡድኖች ሀብት?

December 17, 2023 – EthiopianReporter.com  ከቡና ቀጥሎ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ትልቁን የውጭ ምንዛሪ ገቢ ከሚያስገኙት የኤክስፖርት (ወጪ ንግድ) ምርቶች መካከል አንዱ የወርቅ ማዕድን ነው። ይህ የወርቅ ሀብት አጠቃላይ ኢኮኖሚው በከፍተኛ ደረጃ በውጭ ምንዛሪ እጥረት በተመታበት በአሁኑ ወቅት ለኢኮኖሚው ምርኩዝ መሆን አልቻለም። ኢትዮጵያ ከፍተኛና ጠቃሚ የውጭ ምንዛሪ ገቢ ልታገኝ የምትችልበት ይህ የወርቅ ሀብቷ፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከእጇ እያመለጣትና ከኤክስፖርት […]

የማስታወቂያ ሰሌዳዎች በዲጂታል ስክሪኖች ሲተኩ የአፈጻጸም ችግር ማጋጠሙ ተገለጸ

EthiopianReporter.com  በሰላማዊት መንገሻ December 17, 2023 በውይይት መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማስታወቂያዎችን ለማዘመን የቢልቦርድ ማስታወቂያዎች ተነስተው በዲጂታል ስክሪን እንዲተኩ ትዕዛዝ ካስተላለፈ በኋላ፣ የአፈጻጸም ችግር ማጋጠሙን፣ የኢትዮጵያ ማስታወቂያ ሥራ ማኅበር አስታወቀ፡፡ ማኅበሩ ይህንን የገለጸው ታኀሳስ 4 ቀን 2016 ዓ.ም. ባካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ሲሆን፣ በውይይት መድረኩ ላይ ከተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት የተወከሉ ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል፡፡ የቢልቦርድ […]

ከኦሮሚያ ንብረታቸውን ጥለው የተፈናቀሉ ዜጎች ተገቢውን ካሳ ለመጠየቅ እየተመዘገቡ መሆኑ ተገለጸ

 EthiopianReporter.com  ማኅበራዊ ከኦሮሚያ ንብረታቸውን ጥለው የተፈናቀሉ ዜጎች ተገቢውን ካሳ ለመጠየቅ እየተመዘገቡ መሆኑ ተገለጸ አበበ ፍቅር ቀን: December 17, 2023 ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው በአማራ ክልል ደብረ ብርሃን ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች፣ ይኖሩበት ከነበረው አካባቢ ጥለውት የመጡትን ንብረት የመመዝገብና መረጃን የማሰባሰብ ሥራን እየሠራ መሆኑን የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡ የጠፋባቸውን ንብረት ለማወቅና ንብረታቸው ካልተገኘ ተገቢውን ካሳ ለመጠየቅ ተፈናቃዮች […]

ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባዔ እንዲያካሂዱ ትዕዛዝ ተላለፈ

EthiopianReporter.com  በዳዊት ታዬ December 17, 2023 ከመተዳደሪያ ደንባቸውና ከተቋቋሙበት አዋጅ ውጪ የጠቅላላ ጉባዔ ምርጫ ሳያካሂዱ የቆዩት ሁሉም የንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች ጠቅላላ ጉባዔያቸውን እንዲያካሂዱ ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ትዕዛዝ መስተላለፉ ተገለጸ፡፡ ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ማሳሰቢያ የተሰጠው ኅዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ሲሆን፣ ጠቅላላ ጉባዔያቸውንም እስከ ታኅሳስ 30 ቀን 2016 ዓ.ም. መጨረሻ ድረስ ማጠናቀቅ […]

ከከተማ አስተዳደር እስከ ወረዳ ያሉ ሠራተኞች ፈተና ወስደው እንደ አዲስ ሊመደቡ ነው

EthiopianReporter.com  ማኅበራዊ ከከተማ አስተዳደር እስከ ወረዳ ያሉ ሠራተኞች ፈተና ወስደው እንደ አዲስ ሊመደቡ ነው ዮናስ አማረ ቀን: December 17, 2023 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቢሮዎች ሥር የሚገኙ ሠራተኞች በብቃት መመዘኛ ፈተና ሊለዩ እንደሆነ ተነገረ፡፡ በመጀመርያ ዙር ፈተናውን የሚወስዱ ተቋማት የተለዩ ሲሆን፣ እስከ ጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም. የተለዩት ቢሮዎች ሁሉም ሠራተኞች ለፈተናው ዝግጁ ይሆናሉ ተብሏል፡፡ […]

በአንድነት ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት ውዝግብ ላይ ትምህርት ሚኒስቴር ‹‹አስገዳጅ ትዕዛዝ›› እንዲሰጥ ተጠየቀ

EthiopianReporter.com  ማኅበራዊ በአንድነት ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት ውዝግብ ላይ ትምህርት ሚኒስቴር ‹‹አስገዳጅ ትዕዛዝ›› እንዲሰጥ ተጠየቀ ሰላማዊት መንገሻ ቀን: December 17, 2023 የአንድነት ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት የወላጆችና የመምህራን ኅብረት፣ ከትምህርት ቤቱ አስተዳደር ጋር የተደረገው ስምምነት ተፈጻሚ እንዲሆን ‹‹አስገዳጅ ትዕዛዝ›› እንዲሰጥለት ለትምህርት ሚኒስቴር ጥያቄ አቀረበ፡፡ በኅብረቱ ሰብሳቢ ፍፁም ዳግማዊ (ዶ/ር) ተፈርሞ ታኅሳስ 2 ቀን 2016 ዓ.ም ለትምህርት ሚኒስቴር […]