ኢትዮጵያን ጨምሮ ታዳጊ አገሮች ለውጭ ብድር የሚከፍሉት ዕዳ እንደሚጨምር ዓለም ባንክ ተነበየ
December 17, 2023 – EthiopianReporter.com በዮናስ አማረ December 17, 2023 ዓለም አቀፉን የአገሮች የውጭ ብድር ዕዳ ዓመታዊ ሪፖርት (International Dept Report) ዓርብ ታኅሳስ 5 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ያደረገው የዓለም ባንክ (WB) ኢትዮጵያን ጨምሮ ታዳጊ አገሮች ለውጭ ብድር ዕዳ ማቅለያ የሚከፍሉት ገንዘብ እየጨመረ እንደሚሄድ ገለጸ፡፡ ወደ 122 አገሮች የተበደሩትን 3,000 አዳዲስ ብድሮችን ጨምሮ ከ45 ሺሕ ያላነሱ የብድር […]
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሠራተኞቹ የብቃት ምዘና ፈተና ሊሰጥ ነው
Saturday, 16 December 2023 19:42 Written by Administrator ፈተናውን ማለፍ ያልቻሉ መቋቋሚያ ተሰጥቷቸው ከስራ ይሰናበታሉ ተብሏል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በስሩ ለሚገኙትና አዲስ የመዋቅራዊ ማሻሻያ አደረጃጀት ጥናት ባደረጉ ተቋማት ውስጥ ለሚገኙ ሁሉም ሠራተኞችና የስራ ኃላፊዎች የብቃት መመዘኛ ፈተና ሊሰጥ ነው ተባለ። ፈተናውን ያላለፉ ሰራተኞች መቋቋሚያ ተሰጥቷቸው ከስራ ይሰናበታሉ ተብሏል።ከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ዘርፎች ለሰራኞቹ የብቃት ምዘና ፈተናውን […]
የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ድሮን ለኢትዮጵያ ማቅረቧን ባስቸኳይ እንድታቆም ተጠየቀ
December 17, 2023 – Addis Admas የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ድሮን ለኢትዮጵያ ማቅረቧን ባስቸኳይ እንድታቆም ተጠየቀ Written by መታሰቢያ ካሳዬ ድሮኖቹ በሠላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እየወሰዱ ነው ተብሏል የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ለኢትዮጵያ መንግስት እያደረገች ያለው የሰው አልባ አውሮፕላን ‘የድሮን’ አቅርቦት በአስቸኳይ እንድታቆም በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የኢትዮጵያ ሲቪክ ድርጅች ጠየቁ። ድርጅቶቹ ድሮኖቹ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እየወሰዱ […]
በገጠር መሬት አስተዳደር ዙሪያ የሚወጡ ሕጎች ለፌዴራል መንግሥት ብቻ እንዲተው ተጠየቀ
December 17, 2023 – EthiopianReporter.com ዜና በገጠር መሬት አስተዳደር ዙሪያ የሚወጡ ሕጎች ለፌዴራል መንግሥት ብቻ እንዲተው ተጠየቀ ሔለን ተስፋዬ ቀን: December 17, 2023 የገጠር መሬት አስተዳዳደርና አጠቃቀም ዙሪያ የሚወጡ ሕጎች ለፌዴራል መንግሥት ብቻ እንዲተው ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቀ፡፡ ምክር ቤቱ ይህንን ያለው ታኅሳስ 4 ቀን 2016 ዓ.ም. የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ […]
የንግሥቲቱን ከፍተኛ ሽልማት አልቀበልም ያለው እንግሊዛዊው ገጣሚ ቤንጃሚን
17 ታህሳስ 2023 ቃላቶች ይታዘዙለታል የሚባለው እንግሊዛዊው ገጣሚ እና ፀሐፊ ቤንጃሚን ዘፋኒያህ በቅርቡ ሕይወቱ አልፏል። በ65 ዓመቱ ያረፈው ቤንጃሚን ከፀሐፊነቱ በተጨማሪ ሙዚቀኛ፣ ተዋናይ እንዲሁም በግጥም እና በጽሁፍም የዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር ነበር። ቤንጃሚን ዘረኝነትን አጥብቆ የሚጠየፍ ታጋይ ነበር። ለሚታገልለት ዓላማ ያለው ቁርጠኝነትም ሽልማትን አልቀበልም እስከሚል ጽናት ድረስ ዘልቋል። ወቅቱ በአውሮፓውያኑ 2003 ነበር። በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ በሁለተኛነት ለተቀመጠው […]
ጦርነት እንዲቆም በሚጠይቅ አጭር ፊልም ታዋቂ ሽልማትን ያገኘው ወጣት ኢትዮጵያዊ
17 ታህሳስ 2023 አንዲት ወጣት መምህርት ወደ ማስተማሪያ ክፍል ስትገባ ፊልሙ ይጀምራል። “እንደምን አደራችሁ ተማሪዎች?” በማለት መምህርቷ ለተማሪዎቿ ሰላምታ ታቀርባለች። ዘለግ ያለው “ደህና እግዚአብሔር ይመስገን!” የሚለው የተለመደ የተማሪዎች ምላሽ ግን እዚህ ክፍል ውስጥ አይሰማም። ከዚያም መምህርቷ ቁጭ ብላ የተማሪዎቿን ስም መጥራት ትጀምራለች። ሄለን ተስፋዬ፣ ጋዲሳ ፍራኦል፣ ዊንታና ሐጎስ. . . እያለች ጥሪው ይቀጥላል፤ ምላሽ ግን […]
ከ60 በላይ ስደተኞች በሊቢያ የባህር ዳርቻ ሰጥመው ሞቱ
17 ታህሳስ 2023, 10:01 EAT በሊቢያ የባህር ዳርቻ በደረሰ የጀልባ አደጋ ከ60 በላይ የሚሆኑ ስደተኞች ሰጥመው መሞታቸውን የተባበበሩት መንግሥታት ኤጀንሲ አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) አስታወቀ። ጀልባዋ 86 የሚጠጉ ስደተኞችን አሳፍራ ከዙዋራ ከተማ ቅዳሜ ዕለት መውጣቷንም ከአደጋው የተረፉ ሰዎችን ዋቢ አድርጎ ድርጅቱ ጠቅሷል። ከፍተኛ ማዕበል ጀልባዋን ማናወጡን ተከትሎ በደረሰው አደጋ ህጻናትን ጨምሮ 61 ስደተኞች በውሃ […]
የዩኬ ባሕር ኃይል በቀይ ባሕር አካባቢ የሁቲ ድሮን ተኩሶ ጣለ
17 ታህሳስ 2023, 12:59 EAT ኤችኤምኤስ ዳይመንድ የሚል ስም ያለው የዩኬ የጦር መርከብ ቅዳሜ ዕለት አንድ ሰው አልባ የጦር አውሮፕላን (ድሮን) ቀይ ባሕር አካባቢ መትቶ መጣሉን አስታወቀ። የዩኬ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የሮያል ባሕር ኃይል አንድ ዒላማ ከአየር ተኩሶ ሲጥል ምናልባትም ከ10 ዓመት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ነው። መከላከያ ሚኒስቴር ሰው አልባ አውሮፕላኑ ከማን እንደተተኮሰ ያለው ነገር […]
የአልጀዚራ የካሜራ ባለሙያ በእስራኤል የድሮን ጥቃት ተገደለ
17 ታህሳስ 2023, 09:19 EAT በእስራኤል የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃት የተገደለው የአልጀዚራ የካሜራ ባለሙያ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈጸመ። ሳመር አቡዳቃ እስራኤል በደቡባዊቷ ጋዛ ኻን ዩኒስ ትምህርት ቤት አርብ ዕለት በፈጸመችው የድሮን ጥቃት ነው ጉዳት ከደረሰበት በኋላ ህይወቱ አልፏል። እስራኤል በአካባቢው እያደረሰችው በነበረው ከፍተኛ የቦምብ ጥቃት ምክንያት የህክምና ባለሙያዎች መድረስ ባለመቻላቸውም ሳመር ከፍተኛ ደም ፈሶት […]
የእስራኤል ጦር ታጋቾችን ተኩሶ በገደለበት ወቅት ነጭ ጨርቅ እያውለበለቡ እንደነበር አስታወቀ
17 ታህሳስ 2023, 08:29 EAT የእስራኤል ጦር በጋዛ ታግተው የነበሩ ሶስት ዜጎቹን ተኩሶ በገደለበት ወቅት ነጭ ጨርቅ እያውለበለቡ እንደነበር አስታወቀ። እስራኤል ሶስት የታገቱ ዜጎቿን ተኩሳ የገደለችው በስህተት መሆኑንም አስታውቃለች። የእስራኤል መከላከያ ከፍተኛ ባለስልጣን “ከጦሩ አሰራር ጋር የሚቃረን ነው” እንዲሁም በከፍተኛ ደረጃም ምርመራ መከፈቱንም ተናግረዋል። በእስራኤል ጦር አርብ ዕለት የተገደሉት ታጋቾች የ28 አመቱ ዮታም ሃይም፣ የ22 […]
