ለውጭ ገበያ ሳይላክ ለቀረ ቡና ላኪዎች ታክስ እስከ ወለዱ እንዲከፍሉ ተወሰነ
May 31, 2023 – EthiopianReporter.com በኤልያስ ተገኝ May 31, 2023 ገቢ ሰብሳቢ ተቋማት ቡና ላኪዎች የሚያቀርቧቸውን ሰነዶች መርምረው ወደ ውጭ ሳይላክ የቀረ ቡና መኖሩን ካረጋገጡ፣ ሊከፈል የሚገባውን የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ገዥው ወይም ላኪው ከእነ ወለዱ እንዲከፍሉ እንዲያደርጉ መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሪፖርተር የተመለከተውና በገንዘብ ሚኒስትር ደኤታው ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ተፈርሞ ለገቢዎች ሚኒስቴርና ግልባጩ ለኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን […]
አርሶ አደሮች የቲማቲም ማሳቸውን ወደ በጋ ስንዴ እንዲቀይሩ መገደዳቸውን ተናገሩ
May 31, 2023 – EthiopianReporter.com በሔለን ተስፋዬ የቲማቲም ገበያ ‹‹የአመለካከት ችግር ተፈጥሮ ካልሆነ በስተቀር ስንዴ በሌሎች ምርቶች ላይ ተፅዕኖ አላሳደረም›› የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ አርሶ አደሮች፣ የቲማቲምና የአትክልት ማሳቸውን ወደ በጋ መስኖ ስንዴ እንዲቀይሩ መገደዳቸውን ተናገሩ፡፡ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አንድ አርሶ አደር ለሪፖርተር እንደተናገሩት በወረዳው ቲማቲም፣ ሽንኩርትና ፍራፍሬ ማምረት ተከልክሏል፡፡ […]
የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ከዛሬ ረቡዕ ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ጉዞ ሊያደርጉ ነው
30 ግንቦት 2023 የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር ከዛሬ ረቡዕ ጀምሮ ለሰባት ቀናት የሚቆይ ጉዞ ወደ ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ እንደሚያደርጉ ተገለጸ። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ፣ ልዩ መልዕክተኛው ከግንቦት 23 አስከ 29/2015 ዓ.ም. ድረስ በሚኖራቸው ቆይታ፣ በአገራት እና በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ከከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር እንደሚወያዩ አስታውቋል። አምባሳደር ማይክ ሐመር […]
ከትምህርት ለራቁ የዳውሮ ህጻናት እና ጎልማሶች የተስፋ ብርሃንን የፈነጠቀው መምህር
ከ 6 ሰአት በፊት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን ውስጥ በሚገኘው ጉኖ ቀበሌ የሚገኘው የሻመና አካባቢ በሁሉም ወራት ለምለም ነው። ከዓመት ዓመት አረንጓዴ ነው። የሻመና አብዛኛው ነዋሪ ገበሬ ነው። ከእርሻው ቀለቡን አዘጋጀቶ የተረፈውን ወደ ገበያ ይዞ ይወጣል። የዚህ አካባቢ ነዋሪዎች ዋነኛ ችግር ግን መንገድ ነው። በተለይ በዝናብ ወራት መንገድ አይታሰብም። ለነገሩ፣ መንገድ የሻመና ብቻ ሳይሆን […]
19 መምህራን ከሞቱበት የመኪና አደጋ ምንም ሳይሆን የተረፈው መምህር የአደጋው የመጨረሻ ቅጽበት ትውስታ
ከ 6 ሰአት በፊት ከሳምንት በፊት በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ አርሲ ዞን የደረሰው አስከፊ የትራፊክ አደጋ የ19 የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞችን ሕይወት ሲቀጥፍ በ18 ሰዎች ላይ ደግሞ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳትን አደርሷል። የብዙዎችን ሕይወት ከቀጠፈው እና የአካል ጉዳትን ካስከተለው ከዚህ አደጋ ታዲያ ሁለት መምህራን ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስባቸው በሕይወት መትረፍ ችለዋል። ከእነዚህ መምህራን አንዱ ደግሞ ደስታ […]
ሰው ሰራሽ አስተውሎት የሰው ልጆችን ከምድር ሊያጠፋ ይችላል ሲሉ ባለሙያዎች አስጠነቀቁ
ከ 4 ሰአት በፊት በኦፕንኤአይ እና ዲፕማይንድ የተባሉ ስመ ጥር የቴክኖሎጂ ተቋማት መሪዎችን ጨምሮ በርካታ ባለሙያዎች ሰው ሰራሽ አስተውሎት (አርተፊሻል ኢንተለጀንስ) የሰው ልጆችን ከምድር ሊያጠፋ ይችላል ሲሉ አስጠነቀቁ። ባለሙያዎቹ ስጋታቸውን በመግለጽ ያወጡት ጽሑፍ በዘርፉ በተሰማሩ በርካታ ባለሙያዎች ድጋፍ ቢያገኝም ስጋቱ የተጋነነ ነው ያሉ ባለሙያዎችም አልጠፉም። የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስጋትን እንደ ዓለም አቀፍ የበሽታ ወረርሽኝ እና […]
የቀድሞው የሩሲያ ሰላይ ነው ተብሎ የተጠረጠረው አሳ ነባሪ በስዊድን የባህር ዳርቻ ላይ ታየ
ከ 4 ሰአት በፊት የቀድሞ የሩሲያ ሰላይ ነው ተብሎ የተጠረጠረው አሳ ነባሪ (ዌል) በስዊድን የባህር ዳርቻ ላይ መታየቱን ቤሉጋ አሳነባሪን ለመከታተል የሚሰራው ድርጅት አስታወቀ። በአካባቢው ‘ሃቫልድሚር’ የሚል ስም የተሰጠው ይህ አሳ ነባሪ፣ መጀመሪያ ላይ ሩሲያ ሰራሽ ቀበቶ ተጠልቆለት በኖርዌይ የባህርዳርቻ ላይ የታየው እንደ አውሮፓውያኑ 2019 ነበር። ከኖርዌይ ሰሜናዊ ክፍል ወደ ደቡብ አቅጣጫ ቀስ እያለ በመጓዝ […]
ደብረ ማርቆስ ሱቆቿን ዘግታ ትግሉን ተቀላቀለች
May 31, 2023 – Konjit Sitotaw ደብረ ማርቆስ ሱቆቿን ዘግታ ትግሉን ተቀላቀለች የደብረ ማርቆስ ህዝብ በደብረኤልያ የሚደረገው የሥላሳሴ ገዳም የከባድ መሳሪያ ድብደባ፣የመነኮሳት እና የፀበልተኞች ጭፍጨፈ ባስቸኳይ እንዲቆም ትግሉን ተቀላቅሏል። ዕምነት የለሹ የዐብይ አህመድ ጨፍጫፊ የኦነግ ሠራዊት ከተቀደሰው የጎጃም ገደማት እና አካባቢዎች ባስቸኳይ ለቆ እንዲወጣ ህዝቡ በቁጣ እየጠየቀ ነው።የማይወጣ ከሆነ ግን ትግሉ አድማሱን አስፍቶ አቅጣጫውን ይቀይራል ብለዋል። በተመሳሳይ […]
በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ከሦስት ሺሕ በላይ መምህራንና ተማሪዎች መሞታቸው ተገለጸ
May 31, 2023 በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት፣ በትግራይ ክልል ውስጥ፣ ከ3ሺሕ800 በላይ መምህራንና ተማሪዎች ሕይወት ማለፉን፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ፡፡ ተቋሙ፣ ጦርነቱ በክልሉ ስላደረሰው ጉዳት በአካሔደው የዳሰሳ ጥናት፣ በትምህርት ሥርዐቱም ላይ ከፍተኛ ውድመት መድረሱን አመልክቷል፡፡ የጉዳት መጠኑ፣ በቅርቡ በተጀመረው የመማር ማስተማር ሒደት ላይ ከፍተኛ እክል እንደፈጠረ በተቋሙ የተገለጸ ሲኾን፣ የክልሉ የትምህርት ቢሮ በበኩሉ፣ የሚመለከታቸው […]
በመንግሥት የቀረበው የ28 ቢሊዮን ዶላር የጦርነት ኪሳራ ተኣማኒነት እና ገለልተኝነት የጎደለው፣ ተጠያቂነትንም አያመለክትም
May 31, 2023 – VOA Amharic የኢትዮጵያ መንግሥት፣ መነሻውን በትግራይ ክልል ባደረገው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት፣ የ28 ቢሊዮን ዶላር ወይም በወቅቱ ምንዛሪ ከ1ነጥብ5 ትሪሊዮን ብር በላይ ጉዳት መድረሱን፣ ግንቦት 9 ቀን 2015 ዓ.ም. በይፋ ባወጣው ዳሰሳዊ ጥናቱ አስታውቋል፡፡ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ምሁራንና የምጣኔ ሀብት ባለሞያዎች፥ ዶ/ር አክሎግ ቢራራ፣ ዶ/ር ጉቱ ቴሶ እና አቶ እምነት ነጋሽ፣ ይፋ የተደረገው ጥናት፥ […]