የሱዳን ጦር መሪ መሣሪያ ታጥቀው በአንድ ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ ታዩ

ከ 1 ሰአት በፊት የሱዳን ጦር ሠራዊት ዋና አዛዡ ሌተናንት ጄኔራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን ከወታደሮቻቸው ጋር ሆነው የሚታዩበትን ምስል ለቋል። የጦሩ መሪ አል-ቡርሃን አድራሻው ባልታወቀ አንድ የኻርቱም አካባቢ ወታደሮቻቸው በደስታ ከበዋቸው ታይተዋል። ረቡዕ ዕለት የተለቀቀው የ23 ሰከንድ ምስል እንደሚያሳየው ጀኔራል ቡርሃን የጦር መሣሪያ ታጥቀዋል። ወታደራዊ መለዮ የለበሱት ጄኔራሉ በደስታ ያጀቧቸውን ወታደሮች እየዞሩ ሲጨብጡ ይታያሉ። ጦር […]

ሩሲያ የዩክሬንን መዲና ለዘጠነኛ ጊዜ በሚሳኤል አጠቃች

ከ 5 ሰአት በፊት ሩሲያ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ዘጠነኛ የተባለውን የሚሳኤል ጥቃት በዩክሬን መዲና ኪዬቭ ላይ ፈጸመች። የኪዬቭ ከንቲባ ቪታሊ ክሊችኮ የሚሳኤል ጥቃቱ መቀጠሉን ገልጸው በአንድ አካባቢም የወዳደቁ ሚሳኤሎች የእሳት ቃጠሎ ማስነሳታቸውን ነው። ከመዲናዋ በተጨማሪ በማዕከላዊ ዩክሬን በሚገኙት ቪኒትሳ፣ ክሜልኒትስኪ እና ዚሂቶሚር ግዛቶች ውስጥ ፍንዳታዎች ተሰምተዋል። የኪዬቭ ወታደራዊ አስተዳደር መረጃ እንደሚያመለክተው በከተሞቹ ላይ የተቃጡ […]

ኬንያ የአገልግሎት ጊዜው ባለፈበት የስኳር ንግድ ምክንያት 27 ባለስልጣናትን አገደች

ከ 3 ሰአት በፊት ኬንያ የአገልግሎት ጊዜው ያለፈበት ስኳር ለገበያ መቅረቡን ተከትሎ 27 ባለስልጣናትን ከስራ አገደች። የኬንያ የጥራትና ደረጃ ተቆጣጣሪ 1 ሺህ ቶን የሚሆን የአገልግሎት ጊዜው ያለፈበት ስኳር ወደ ገበያ መውጣቱን ጠቁሞ ይህንን ባደረጉ ባለስልጣናትም እርምጃ ተወስዷል ብሏል። የህዝብ አገልግሎት ኃላፊው ፊሊክስ ኮስኬይ በሰጡት መግለጫ በአውሮፓውያኑ 2018 ወደ አገር ውስጥ የገባ 20 ሺህ ከረጢት ስኳር […]

የአሜሪካዋ ሞንታና ግዛት ቲክቶክን ግለሰቦች እንዳይጠቀሙ ልታገድ ነው

ከ 4 ሰአት በፊት የአሜሪካዋ ሞንታና ግዛት ነዋሪዎቿ በግል የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ቲክቶክን እንዳይጠቀሙ ለማገድ የተዘጋጀች ሲሆን ይህን እርምጃ የምትወስድ የመጀመሪያዋ የሀገሪቱ ግዛት ትሆናለች። የግዛቲቱ ገዢ ግሬግ ጃንፎቴ ይህንን እገዳ የያዘው ህግ ላይ ትላንት ረቡዕ ፈርመዋል። ይህ ህግ ከቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል። እገዳውን ተከትሎ ቲክቶክ በሰጠው አስተያየት እርምጃው የሞንታና ነዋሪዎችን መሰራታዊ መብት የሚጥስ ነው […]

የፌደራል መንግስት “ደመወዝ የመክፈል ጫና ውስጥ ለገቡ” ክልሎች፤ ከሰባት ቢሊዮን ብር በላይ ማበደሩን የገንዘብ ሚኒስትሩ ተናገሩ

May 18, 2023 – Konjit Sitotaw  የፌደራል መንግስት “ደመወዝ የመክፈል ጫና ውስጥ ለገቡ” ክልሎች፤ ከሰባት ቢሊዮን ብር በላይ ማበደሩን የገንዘብ ሚኒስትሩ ተናገሩ የክልል መንግስታት ላጋጠማቸው የበጀት እጥረት፤ የፌደራል መንግስት ብድር መስጠት እንጂ ቀጥታ ድጋፍ ማድረግ እንደማይችል የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተናገሩ። የፌደራል መንግስት “ደመወዝ የመክፈል ጫና ውስጥ ለገቡ” ክልሎች፤ ከሰባት ቢሊዮን ብር በላይ ማበደሩንም ሚኒስትሩ ገልጸዋል። […]

በቢሾፍቱ ስለተገደሉ የፖሊስ አባላት ጉዳይ ምርመራ መጀመሩን የከተማው ከንቲባ አስታወቁ

May 18, 2023 – EthiopianReporter.com  በቢሾፍቱ ስለተገደሉ የፖሊስ አባላት ጉዳይ ምርመራ መጀመሩን የከተማው ከንቲባ አስታወቁ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ቢሾፍቱ ከተማ በታጣቂዎች ስለተገደሉት አራት የፖሊስ አባላት ጉዳይ ምርመራ መጀመሩን፣ የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ በታጠቁ ኃይሎች ስለተገደሉት የፖሊስ አባላት ምርመራ እየተደረገ መሆኑን፣ የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አቶ ዓለማሁ አሰፋ ተናግረዋል፡፡ በታጣቂዎች…

‹‹የኢትዮጵያ ሚና ለሱዳን መንግሥት አዎንታዊና ደጋፊ ነው›› የሱዳን የሽግግር መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ አገሮች ልዩ መልዕክተኛ

May 18, 2023 – EthiopianReporter.com  ‹‹የኢትዮጵያ ሚና ለሱዳን መንግሥት አዎንታዊና ደጋፊ ነው›› የሱዳን የሽግግር መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ አገሮች ልዩ መልዕክተኛ ከተጀመረ አንደኛ ወሩን ላስቆጠረው የሱዳን ጦርነት ‹‹የኢትዮጵያ ሚና ለሱዳን መንግሥት አዎንታዊና ደጋፊ ነው፤›› ሲሉ፣ የሱዳን የሽግግር መንግሥት ምክር ቤት የአፍሪካ ኅብረትና የአፍሪካ ቀንድ አገሮች ልዩ መልዕክተኛ አስታወቁ፡፡ የሱዳን የሽግግር መንግሥት ምክር ቤት የአፍሪካ ኅብረትና የአፍሪካ…

ለፓርላማ በቀረበ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለብልፅግና አባላት ሥልጠና ተሰጠ መባሉ ጥያቄ አስነሳ

May 18, 2023 – EthiopianReporter.com  ለፓርላማ በቀረበ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለብልፅግና አባላት ሥልጠና ተሰጠ መባሉ ጥያቄ አስነሳ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር በ2015 ዓ.ም. የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ውስጥ፣ ለብልፅግና የክልል ፓርቲ ጽሕፈት ቤት አባላት የአቅም ግንባታ ሥልጠና ድጋፍ መሰጠቱ ተጠቅሶ መቅረቡ በፓርላማ ጥያቄ አስነሳ፡፡  የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማክሰኞ ሚያዝያ 8 ቀን…

የአፍሪካ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ አኅጉራዊ ሁነት በአዲስ አበባ ሊዘጋጅ ነው

May 18, 2023 – EthiopianReporter.com  የአፍሪካ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ አኅጉራዊ ሁነት በአዲስ አበባ ሊዘጋጅ ነው የአፍሪካ ኅብረት 60ኛ ዓመት የምሥረታን በዓል መሠረት በማድረግ ተገማች ባልሆነው ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ የአፍሪካን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እንዴት ማረጋገጥ ይቻላል? በሚለው ላይ የሚመክር ዓለም አቀፍ ኤክስፖና የምክክር ሁነት መዘጋጀቱን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ ይኼን ያስታወቀው…

የኢጋድ አባል አገሮች ሐዋላ ላይ የሚሠራ አገራዊ ተቋም እንዲያቋቁሙ ተጠየቀ

May 18, 2023 – EthiopianReporter.com  የኢጋድ አባል አገሮች ሐዋላ ላይ የሚሠራ አገራዊ ተቋም እንዲያቋቁሙ ተጠየቀ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) አባል አገሮች፣ በሐዋላ ላይ አፅንኦት ሰጥቶ የሚሠራ አገራዊ ተቋም ማቋቋም እንደሚገባቸው ተገለጸ፡፡ የሐዋላ ፖሊሲዎችን (Remittance Policies) በቀጣናው እንዲስማሙ የማድረግ ፕሮጀክት በሚል በተዘጋጀ የማዕከላዊ ባንኮች ስብሰባ ነበር፣ የተቋማቱን ማቋቋም…