ዩክሬን ፕሬዝዳንት ፑቲንን በድሮን ጥቃት ለመግደል ሞክራለች ስትል ሩሲያ ከሰሰች
May 3, 2023 – BBC Amharic 3 ግንቦት 2023, 16:28 EAT ዩክሬን በፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን መኖሪያ ቤተ መንግሥት ላይ ጥቃት በመሰንዘር ልትገድላቸው ሞክራለች ስትል ሩሲያ ከሰሰች። ማክሰኞ ምሽት የፕሬዝዳንት ፑቲን ቤተመንግሥትን ኢላማ ያደረጉ ሁለት ድሮኖችን ጥያለሁ ያለችው ሩሲያ፣ ዩክሬን ፑቲንን ለመግደል እየሞከረች ነው ስትል ከሳለች። የክሬምሊን ቤተመንግሥት ባለሥልጣናት እንዳሉት ለጥቃት የተሰማሩት ድሮኖችን የፕሬዝዳንቱ ጥበቃ ኃይል በኤሌክትሮኒክ ራዳር […]
የአክሱም አውሮፕላን ማረፊያን መልሶ ለመገንባት በመቶ ሚሊዮኖች ወጪ ያስፈልጋል ተባለ
EthiopianReporter.com በአሸናፊ እንዳለ May 3, 2023 በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ከባድ ጉዳት ከደረሰባቸው መሠረተ ልማቶች አንዱ የሆነውና ለሁለት ዓመታት ያለ አገልግሎት የቆየው የአክሱም አውሮፕላን ማረፊያን መልሶ ለመገንባት፣ በብዙ መቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አስታወቀ፡፡ የአውሮፕላን ማረፊያው መንደርደርያ (Ranway) ተቆፍሮ ሙሉ በሙሉ መበላሸቱንና ተርሚናሉም ከባድ ውድመት እንደደረሰበት፣ በተደረገው የመጀመሪያ ደረጃ ፍተሻ (Preliminary […]
“የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት” ቁልፍ በሆኑ የፖለቲከ ጉዳዮች ላይ መግባባት አልታቻለም አለ
May 3, 2023 “የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት” ቁልፍ በሆኑ የፖለቲከ ጉዳዮች ላይ መግባባት አልታቻለም አለ (አዲስ ማለዳ) “የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት” ከመንግሥት ጋር ባደረገው የመጀመሪያው ምዕራፍ ድርድር ቁልፍ በሆኑ የፖለቲካ ጉዳዮች መግባባት ላይ አለመደረሱን አስታወቀ፡፡ ራሱን “የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት” ብሎ የሚጠራውና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪነት የተፈረጀው “ኦነግ ሸኔ” ባወጣውና ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ተመሳሳይነት ባለው መግለጫ ፤ በታንዛኒያ […]
መንግሥት ሲቪል ማኅበራት የዘፈቀደ እሥራትን በተመለከተ ያቀረቡትን ምክረ ሐሳቦች እንዲተገብር ተጠየቀ
May 3, 2023 – EthiopianReporter.com ዜና መንግሥት ሲቪል ማኅበራት የዘፈቀደ እሥራትን በተመለከተ ያቀረቡትን ምክረ ሐሳቦች እንዲተገብር ተጠየቀ ኤልያስ ተገኝ ቀን: May 3, 2023 መንግሥት ከሕግ ውጪ የዘፈቀደ እስራትን በተመለከተ፣ በሲቪል ማኅበራት ተወካዮች ተጣርተው የቀረቡ መረጃዎችንና ምክረ ሐሳቦችን በመቀበል ተግባራዊ እንዲያደርግ ጥያቄ ቀረበለት፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጥያቄውን ያቀረበው በባህር ዳር፣ በጅግጅጋና በሐዋሳ ከተሞች ያካሄደውን ግልጽ የምርመራ […]
አሁን ባለው አገራዊ ሁኔታ ሕገ መንግሥቱን ለማሻሻል ማሰብ አደጋው የከፋ ሊሆን ይችላል ተባለ
May 3, 2023 – EthiopianReporter.com ዜና አሁን ባለው አገራዊ ሁኔታ ሕገ መንግሥቱን ለማሻሻል ማሰብ አደጋው የከፋ ሊሆን ይችላል… ሲሳይ ሳህሉ ቀን: May 3, 2023 በሥራ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አሁን ባለው አገራዊ ሁኔታ ለማሻሻል ወይም ለመቀየር ማሰብ አደጋው የከፋ ስለሚሆን፣ ጠንካራ የአገረ መንግሥት ግንባታና የተሻለ የሰላም ሁኔታ ማስፈን የሚለው ቀዳሚ ሥራ መቅደም አለበት የሚለው ጉዳይ ምሁራንን […]
በዓለም ባንክ ድጋፍ በሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ላይ ሙስናና ብልሹ አሠራሮች እንደሚፈጸሙ ተገለጸ
May 3, 2023 – EthiopianReporter.com ዜና በዓለም ባንክ ድጋፍ በሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ላይ ሙስናና ብልሹ አሠራሮች እንደሚፈጸሙ ተገለጸ ሔለን ተስፋዬ ቀን: May 3, 2023 በዓለም ባንክ ድጋፍ በሚከናወኑ ሰባት ፕሮጀክቶች ላይ ሙስናና ብልሹ አሠራሮች የሚፈጸሙ ቢሆንም በሪፖርት ውስጥ እንደማይካተቱ፣ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ ይህንን ያስታወቀው ሚያዝያ 21 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዳማ ከተማ በዓለም ባንክ […]
‹‹የሚጠና የፖሊሲ ጉዳይ የለንም›› የሚሉ የመንግሥት ተቋማት መኖራቸው ተገለጸ
May 3, 2023 – EthiopianReporter.com ዜና ‹‹የሚጠና የፖሊሲ ጉዳይ የለንም›› የሚሉ የመንግሥት ተቋማት መኖራቸው ተገለጸ ኤልያስ ተገኝ ቀን: May 3, 2023 ትምህርት ሚኒስቴር አንደኛው መሆኑ ተጠቁሟል የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት መንግሥታዊ ተቋማት እንዲጠኑላቸው የሚፈልጉትን የፖሊሲ ጉዳይ እንዲያሳውቁት በሰርኩላር ቢጠይቅም፣ አንዳንዶቹ ‹‹የሚጠና ጉዳይ የለንም›› የሚል ምላሽ እንደሚሰጡ አስታወቀ፡፡ ኢንስቲትዩቱ እያንዳንዱ መንግሥታዊ ተቋም ለምርምር የሚበቁና የሚነሱ ጉዳዮችን፣ እንዲሁም በግልጽ መረጃ […]
የመንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የመጀመሪያው ዙር ንግግር ያለ ስምምነት ተጠናቀቀ
May 3, 2023 – BBC Amharic 3 ግንቦት 2023, 13:53 EAT በኦሮሚያ ክልል ለዓመታት የዘለቀውን ጦርነት በሰላም ለመቋጨት በፌደራሉ መንግሥትና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል ሲካሄድ የቆየው የመጀመሪያ ዙር ንግግር ያለስምምነት ተጠናቀቀ። ካለፈው ሳምንት ማክሰኞ ጀምሮ ለዘጠኝ ቀናት ሲካሄድ የቆየው ንግግር በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ መድረስ እንዳልተቻለ ሁለቱም ወገኖች ገልጸዋል። በሰሜናዊ ምሥራቅ ዛንዚባር በምትገኘው ሙዩኒ የባሕር ዳርቻ […]
የታንዛንያው የመጀመሪያ ዙር ድርድር አለመሳካቱ ተሰማ
May 3, 2023 የጠቅላይ ሚኒስትር የብሔራዊ ጸጥታ አማካሪ፣ አቶ ሬድዋን ሁሴን የታንዛኒያው የሰላም ውይይት “በአመዛኙ ገንቢ” እንደነበርና “እንደ አለመታደል ሆኖ በዚህ የውይይት ዙር ወቅት በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ መድረስ አልተቻለም” ብለዋል
በኢትዮጵያ ያለው የሲቪክና የሚዲያ ምኅዳር አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
May 3, 2023 – EthiopianReporter.com ዜና በኢትዮጵያ ያለው የሲቪክና የሚዲያ ምኅዳር አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ አሸናፊ እንዳለ ቀን: May 3, 2023 30ኛው የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ዛሬ እየተከበረ ነው ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት፣ የሲቪክና የሚዲያ ምኅዳር ውስጥ እየተፈጠሩ ያሉ ክስተቶች አሳሳቢ እየሆኑ መምጣታቸውን የተመድ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጽሕፈት ቤተ ገለጸ፡፡ ባለፉት ሁለት ቀናት በኢትዮጵያ ጉብኝት […]
