“ኢድ ሙባረክ” ከቂሊንጦ እስር ቤት ደጃፍ (ዮናታን ረጋሳ)

  July 17, 2015 –  ዛሬ የኢድ በዓል ነው። የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ፣ ዮናታን ረጋሳ የፖለቲካ እስረኞችን ለመጠየቅ ወደ ቂሊንጦ እር ቤት ሄዶ ነበር። እዚያ ሲደርስ የበር ላይ ዘቦች እንዳይገባ አደረጉት። እናም ውጭ ቁጭ ብሎ የሙስሊም እህቶች እና እናቶች ቤተሰባቸውን ለመጠየቅ መጥተው፤ የሚያደርጉትን ነገር መታዘብ ጀመረ። ከዚያች የእስር ቤት ደጃፍ ላይ ሆኖ፤ ለሁሉም ሙስሊሞች […]

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቴዲ አፍሮ ምክንያት 200 ሺህ ዶላር ከሰረ

July 18, 2015 –  ቴዲበድጋሚ ፓስፖርቱን ተቀምቶ ነበር (ክንፉ አሰፋ፣ ፍራንክፈርት) ባለፈው ሳምንት ወደ ከአዲስ አበባ ናይሮቢ-ኬንያ ይጓዝ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራውን ከጀመረ በኋላ እንዲመለስ መደረጉን የአየር መንገዱ ምንጮች አስታወቁ።  በዚህም ምክንያት አየር መንገዱ የሁለት መቶ ሺህ ዶላር ኪሳራ እንደደረሰበት ምንጮቹ ጠቁመዋል። በተሳፋሪዎች ላይም ከፍተኛ መጉላላት ደርስዋል። አውሮፕላኑ ካኮበኮበ በኋላ እንዲመለስ የተደረገበት ምክንያት ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ከባለቤቱ ከአለምሰት ሙጬ ጋር በአውሮፕላኑ በመሳፈሩ ምክንያት መሆኑ ተረጋግጧል። ይህ አስደንጋጭ ክስተት የተፈጸመው አለምሰት ሙጬ በደረሰባት ድንገተኛ ህመም ለህክምና ወደ ኬንያ እየተጓዘች ባለችበት አውሮፕላን ነው። አውሮፕላኑ ዞሮ ከተመለሰ በኋላም ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ በደህንነቶች ተይዞ ከአውሮፕላኑ እንዲወጣ ተደርጓል።  የህወሃት የደህንነት አባላት የቴዲ አፍሮን ፓስፖርት ቀምተው አሰናብተውት ነበር። ቴዲ አፍሮ በሰሜን አሜሪካ በየዓመቱ የሚደረገው የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫል ላይ ድምጻዊ ጎሳዬ ተስፋዬ ጋር መጋበዙ የሚታወስ ሲሆን ይህንን በመቃወም ሚሚ ስብሃቱ እና ባለቤትዋ ዘሪሁን ተሾመ ዘመቻ ከፍተው እንደነበር የሚታወስ ነው። የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን 33ኛ ዓመት በዓል ላይ እነዚህ ድምጻውያን አልተገኙም። ድምጻውያኑ በበዓሉ ያልተገኙበት ምክንያት የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ በደረሰው የኮምፒውተር  ሽብር ጥቃት- የቪዛ ችግር ያጋጠማቸው መሆኑ ቢገለጽም፤  ቪዛ ቢያገኙ ኖሮ እንኳ በደህንነቶች  አፈና ከሃገር ሊወጡ እንደማይችሉ ግልጽ ነበር። የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌዴሬሽን አሸባሪ ተብሎ በነሚሚ ስብሃቱ መፈረጁን የህወህት መንግስት ተቀብሎ በውስጥ አጽድቆታል። ቴዲ አፍሮ ባለቤቱን ለማሳከም ወደ ኬንያ በመጓዝ ላይ እንዳለ በኬንያ በኩል ወደ አሜሪካ ሊጓዝ ነው ተብሎ በነ ሚሚ ስብሃቱ በደረሰው ጥቆማ ነው አውሮፕላኑ እንዲመለስ የታዘዘው። በዚህ በተሳሳተ መረጃ ምክንያት በተሳፋሪው ላይም ከፍተኛ መጉላላት የደረሰ ሲሆን አየር መንገዱም ለከፋ ኪሳራ ተዳርጓል ሲሉ የአየር መንገዱ ምንጮች ተናግረዋል። ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ከባለቤት ጋር ወደ ኬንያ ይጓዝ የነበረው የሰሜን አሜሪካው የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫል ከተጠናቀቀ በኋላ ነበር። የህወሃት ደህንነት አባላት ይህንን እንኳን ማገናዘብ የማይችሉ ደካሞች እንደሆኑ ምንጮቹ ተቁመዋል። ከብዙ መጉላላት በኋላ ቴዲ አፍሮ ፓስፖርቱን አስመልሶ ወደ ጀርመን – ፍራንክፈርት የበረረ ሲሆን በቅዳሜ ምሽት የአውሮፓ ስፖርትና ባህል ፌስቲቫል ላይ ዝግጅቱን ያቀርባል። ከዚያም የጄኔቭ ስዊዘርላንድ ማዘጋጃ ባሰናዳው ዝግጅት ላይ ልዩ ተጋባዥ በመሆን በመጭው ሳምንት ስራውን ለህዝብ በነጻ ያሳያል። የቴዲ አፍሮ ባለቤት አለምሸት ሙጬ በአሁኑ ሰዓት በአሜሪካ-ቨርጂንያ ህክምናዋን እየተከታተለች ትገኛለች። ድምጻዊ ቴዲ አፍሮን በአካል አግኝቼ ባነጋገርኩበት ግዜ የዚህን ዘገባ ትክክለኝነት አረጋግጫለሁ። ይህንን እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ወደፊት በስፋት…

መድረክና ሰማያዊ፤ በአባሎቻችን ላይ ግድያና እስር እየተፈፀመ ነው ሲሉ አማረሩ

Saturday, 18 July 2015 10:19     ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከግንቦቱ ምርጫ በኋላ አባሎቻቸውና ደጋፊዎቻቸው ላይ ግድያ፣ እስራትና እንግልት እየተፈፀመባቸው መሆኑን የገለፁ ሲሆን መድረክ 5 አባሎቹ እንደተገደሉበት ስታውቋል። ሰማያዊ ፓርቲም በአባላቱ ላይ እየተፈፀመ ነው ያለው ግድያ፣ እስርና እንግልት በአስቸኳይ እንዲቆም ሰሞኑን ጠይቋል፡፡ ድረክ በሰጠው በመግለጫ፤ በደቡብና በኦሮሚያ ክልሎች በአባላቱ ላይ የሚፈፀሙት እስራቶችና ንግልቶች ተጠናክረው እንደቀጠሉ አመልክቷል፡፡ ከምርጫው […]

የውጭ ብድር እዳ ኢትዮጵያን ያሰጋታል ተባለ

• ስጋት ከተጋረጠባቸው 14 ሀገራት ውስጥ ተካታለች • ሴኔጋል፣ ታንዛኒያ፣ ኡጋንዳ፣ሞዛምቢክ በዕዳ ተዘፍቀዋል የውጪ ብድር እዳ ኢኮኖሚያቸውን ሊፈታተን ይችላል የሚል ስጋት ከተጋረጠባቸው 14 የአለም አገራት ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ዘ ጋርዲያን የአለም ባንክን ሪፖርት ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ በአሁን ወቅት ኢትዮጵያ ከፍተኛ የብድር እዳ እንዳለባት የጠቀሰው ሪፖርቱ፤ ከአጠቃላይ አገራዊ ምርቷ 45 በመቶ የሚሆነው ከብድር የተገኘ ገንዘብ እንደሆነ ጠቁሞ፤ […]

ስበር ዜና ! የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትሩ አማካሪ ከሀገር ኮበለሉ

Wednesday, 08 July 2015 14:50 በ  ፋኑኤል ክንፉ  ስንደቅ        የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን አማካሪ የነበሩት አቶ አንዱዓለም አዱኛ አሞኘ ከሀገር መኮብለላቸው ተሰማ። አቶ አንዱዓለም ባለፈው ሀገር ዓቀፍ ምርጫ በኢሕአዴግ ጽ/ቤት ለቅስቀሳ የሚሆኑ ሰነዶችን እንዲያዘጋጁ ከመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ተመድበው ይሰሩ ነበር። ሆኖም ምክንያቱ ለጊዜው ባልታወቀ ሁኔታ ከስራገበታቸው በመሰወራቸው፣ በተደረገው ማጣራት ከአሜሪካ […]

መድረክ የምርጫ ታዛቢ አባሉ መገደሉን አስታወቀ

Wednesday, 15 July 2015 13:36 በ  ጋዜጣው ሪፖርተር – ሰማያዊ ፓርቲ እስርና ግድያ እንዲቆም ጠየቀ በግንቦት ወር 2007 በተካሄደው ምርጫ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በካፋ ዞን በግንቦ ወረዳበአድዮ ካካ ምርጫ ክልል በጎጀብ ምርጫ ጣቢያ የመድረክ ምርጫ ታዛቢ/ወኪል ሆነው የሠሩት አቶ አሥራት ኃይሌ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ቅዳሜ ሰኔ 27 ቀን በተፈጸመባቸው አሰቃቂ ድብደባ ምክንያት ሕይወታቸው […]

ከሰላሙም ከጉልበቱም የተራራቀው የኤርትራ መንግሥት

15 JULY 2015 ተጻፈ በ  የማነ ናግሽ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ሕልፈት ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትርነቱን የተረከቡት አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ የኤርትራን ጉዳይ በተመለከተ በወቅቱ ከአልጄዚራ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ ‹‹አስመራም ድረስ በመሄድ ዕርቅ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ›› ብለው ነበር፡፡ ቀደም ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት የኢትዮጵያ መንግሥት በኤርትራ ላይ የሚከተለው ፖሊሲ ከመከላከል ወደ ማጥቃት ለመሸጋገር ሊገደድ […]

ሃዲያ ሞሃመድ! ያልተዘመረላት ጀግና

July 2015 ያልተዘመረላት፣ ያልተነገረላት ጀግና ኢትዮጵያዊት ሴት ናት። እንደሌሎች “እኔ ምን አገባኝ? አርፌ ልቀመጥ” ብላ፣ ባርነትንና ዉርደትን አሜን ብላ ተቀብላ፣ ሕሊናዋን ሸጣ፣ የገዢው ፓርቲ አዉደልዳይ ሆዳም ካድሬና አገልጋይ ሆና፣ በዘረኝንትና በጠባብነት በሽታ ተለክፋ መኖር ትችል ነበር። ግን አላደረገችውም። ከደቡብ ክልል ከወላይታ ሶዶ ናት። የወያኔ ቡችላው ሃይለማሪያም ደሳለኝ መጣሁበት ካለው። እንደ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የሌሎች አሽከር አልሆነችም። […]

የሸገር ወላጆች ምሬት Vs የግል ት/ቤቶች ቅሬታ

July 14, 2015 ·  እንደ አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አህዛዊ መረጃ በመዲናዋ ውስጥ 1671 የሚሆኑ የግል ትምህርት ቤቶች አሉ፡፡ መረጃው ከቅድመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ኮሌጅ መሰናዶ ድረስ ያሉትን የግል ትምህርት ቤቶች የሚያጠቃልል ሲሆን ፤ ትምህርት ቢሮው በ2006 የትምህርት ዘመን መጨረሻ ወራት ላይ ባወጣው ሪፖርት መሰረት ፣ በግል ትምህርት ቤቶች ውስጥ 200,000 (ሁለት መቶ […]