መተው፤ ነገሬን ላይከተው

Friday, October 19, 2018 ታዋቂው የሥነ ልቡና ምሁር ሮልፍ ዶብሊ ‹አጥርቶ የማሰብ ጥበብ› በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ እንዲህ ይላሉ፡፡ እንበልና አንተ የመድኃኒት አስተዳደር ኃላፊ ነህ፡፡ ለረዥም ግዜ ታምሞ የአልጋ ቁራኛ ለሆነ ሰው የሚሰጥን መድኃኒት በተመለከተ እንድትወስን ቀረበልህ፡፡ መድኃኒቱ ከባድ የሆነ የጎንዮሽ ችግር አለው፡፡ ከሚወስዱት መካከል 20 በመቶዎቹ ሊሞቱ ይችላሉ፡፡ 80 በመቶዎቹን ደግሞ የማዳን ዕድል አለው፡፡ ይህን […]

በኢሕአዴግ አመራሮች ፊርማ ለሱዳን በምስጢር የተሰጡት የእርሻ መሬቶችን ለማስመለስ መንግስት ኮሚቴ አቋቋመ።

October 19, 2018  በኢትዮጵያ እና ሱዳን የወሰን ድንበሮች የሚገኙ የኢትዮጵያ የእርሻ መሬቶች ፓርላማ ተወያይቶ ሳያጸድቅ ስልጣን ላይ በነበሩ የኢሕአዴግአመራር ፊርማ ለሱዳን ተላልፈው መሰጠታቸው ስህተት እንደነበር በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ልዩ ረዳት እና የኮምኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አብይ ኤፍሬም አስታወቁ ። https://youtu.be/cYjWKxiW69I

የኢትዮ-ኤርትራ የንግድ ግንኙነት በርካቶችን እየሳበ ነው።

October 19, 2018  ቢቢሲ የኤርትራ ነፃነቷን ካወጀች በኋላ የሁለቱን ሃገራት የንግድ ግንኙነት ምን መልክ ሊኖረው እንደሚገባ በውል ውይይት ተደርጎበት መልክ እንዲይዝ አልተደረገም። ሁለቱም ራሳቸውን የቻሉ ሃገራት ከሆኑ ከዓመታት በኋላም የሚኖራቸው የገንዘብ ልውውጥ በምን መልኩ መካሄድ እንደለበት ምንም ዓይነት ስምምነት ላይ አልተደረሰም ነበር። በወቅቱ የሁለቱ ሃገራት ምጣኔ ኃብታዊና የንግድ ግንኙነት በተጠናና ግልጽ በሆነ መንገድ አለመመራቱ ደግሞ […]

አብይን በመደገፌ አላዝንም፤ አልጸጸትም! (ፋሲል የኔአለም)

10/19/2018 አብይን በመደገፌ አላዝንም፤ አልጸጸትም! ፋሲል የኔአለም   * ሲያዩት ትንሽ የሚመስለው ብርጭቆ ሲሰበር ይበዛል፤ አገርም እንደ ብርጭቆ ነው። አንዴ ከተሰበረ  ስብርባሪውን ለቅሞ እንደነበረው ለማድረግ ፈታኝ ነው! አብይ ስሜቱ በከፍተኛ ሁኔታ እንደተጎዳ ከዛሬው የፓርላማ ንግግሩ ታዝቤአለሁ።  ህዝብ ካልደገፈው በስተቀር ወንበሩ ላይ መቀጠል እንደማይፈልግም ተናግሯል። ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ በማንኛውም ጊዜ “በቃኝ” ሊል የሚችልበት እድል ሰፊ ነው። […]

ቀን የጎደለ ለት፤ ይደረጋል ሁሉም!(በእውቀቱ ስዩም)

10/19/2018 ቀን የጎደለ ለት፤ ይደረጋል ሁሉም! በእውቀቱ ስዩም ምሽቴን ማን ወሸማት፤ ኣይሉም ኣይሉም በሬየን ማን ነዳው፤ ኣይሉም ኣይሉም ቤቴን ማን ወረሰው፤ ኣይሉም ኣይሉም ቀን የጎደለ ቀን፤ ይደረጋል ሁሉም ብሎ ኣንጎራጎረ ደጃዝማች ብሩ የተባለ መስፍን ፡፡ ይህ ሰው ባንድ ወቅት ራሱ ባለስልጣን ስለነበረ የስልጣን ባህርይ በደንብ ገብቶታል፡፡ በዘመናችን ይደረጋሉ ተብለው የማይታሰቡ ግፎች ሲፈጸሙ በተመለከትኩ ቁጥር ወደ […]

ልብ ይሰብራል!!! (ሀብታሙ አያሌው)

10/19/2018 ልብ ይሰብራል!!! ሀብታሙ አያሌው ስለ ጠበቃ ሄኖክና ስለ ማይክ የእስር ሁኔታ ምንም ማለት እስከማልችል ድረስ ግራ ገብቶኛል:: ማይክን ባለፈው ሳምንት አግኝቼዋለሁ:: ማይክ ሙሉ ሰው የምንለው አይነት ምርጥ ሰው ነው:: ደግነቱ…. የሚገለፀው በመስጠቱ ሳይሆን ከልቡ በመስጠቱ ነው:: መስጠቱ…. በአይን የሚታይንና የእለት ችግርን በሚያቃልል መልኩ ብቻ አይደለም:: ቅን..ሩህሩህ… አዛኝ… የመሆኑ ቀመር የመጣው ከመኖር እና ከማንበብ ነው:: […]

“አዲስ አበባ በአዲስ አበባውያን ትተዳደር ማለት ወንጀል አይደለም” (ጠበቃ አለልኝ ምህረቱ)

10/19/2018 “አዲስ አበባ በአዲስ አበባውያን ትተዳደር ማለት ወንጀል አይደለም”  ጠበቃ አለልኝ ምህረቱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አለም አቀፉ ድርጅት አምነስቲ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹንና ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉና ጓደኛው ሚካኤል መላክ ሐሳባቸውን በነፃ በመግለፃቸው ሊታሰሩ አይገባም፤ እንዲለቀቁም በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። ሔኖክ አክሊሉና ጓደኛው ሚካኤል መላክ “አዲስ አበባ እንደ ሌሎች ክልሎች በራሷ አስተዳደር ልትተዳደር ይገባል ማለታቸውና ከፍልስጥኤም […]

የኢሳቱ ጋዜጠኛ የሲሳይ አጌና ኦነጋዊ አስተሳሰብ!-ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

አቶ ሲሳይ አጌና ቀንደኛ የዐቢይ አስተዳደር ደጋፊ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በተለይም ዐቢይ አሜሪካንን በጎበኘበት ወቅት ስሙን ጠርቶ ካመሰገነውና ካደነቀው ወዲህ ብሶበታል፡፡ ሚዛናዊ የሆነ ዕይታውን ጨርሶ ትቶታል፡፡ የማገናዘብና የማሰብ ብቃቱ ከድቶታል፡፡ ባልደረቦቹና ለውይይት የሚጋብዛቸው ሰዎች ዐቢይን የተቹ እንደሆነ ለንቦጩን መጣልና ሐሳባቸውን እንዳይገልጹ ለማቀብ መጣር የዕለት ተዕለት ተግባሩ አድርጎታል፡፡ ከዚህ ትዝብት ላይ ከሚጥለው፣ ታሪኩን ከሚያበላሸውና ስሙን ከሚያጎድፈው ጭፍን […]

ዐቢይን ለመግደል ቤተመንግሥት የመጣው የአግአዚ ሠራዊት! -ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

የሆነውስ ሆነና ዐቢይ ትናንትና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተብየው ላይ “ሊገሉኝ ቤተመንግሥት ድረስ ሠራዊት ልከው የነበሩ ሰዎች ሴራቸው ከሽፎ ሊገሉኝ ባለመቻላቸው ተናደዋል ተበሳጭተዋል!” ያሏቸውን 240 የአግአዚ ሠራዊት ልከው ሊገሏቸው የሞከሩትን የወያኔ ወንጀለኛ ባለሥልጣናትን በቁጥጥር ስር አውለዋቸዋል ወይ??? መቸም የላኳቸው እነሱ መሆናቸውን ሳያረጋግጡ ወይም በቂ መረጃ ሳይኖራቸው እንደዚህ የዓለምአቀፍ የዜና አውታሮች ሳይቀር እየተቀባበሉ ያራገቡትን ክስ በማንሣት […]