በኤርትራውያን መካከል ኔዘርላንድስ ውስጥ በተከሰተ ግጭት የፖሊስ መኪኖች ተቃጠሉ

18 የካቲት 2024, 14:14 EAT ኔዘርላንድስ ሄግ ከተማ ውስጥ በሚገኙ በሁለት ኤርትራውያን ቡድኖች መካከል ቅዳሜ ምሽት በተከሰተ ግጭት የፖሊስ ተሽከርካሪዎች በእሳት መጋየታቸው ተነገረ። የኤርትራ መንግሥት ደጋፊ እና ተቃዋሚ በሆኑት ቡድኖች መካከል የተፈጠረውን ግጭት ለመቆጣጠር የኔዘርላንድስ ፖሊስ አስለቃሽ ጋዝ መጠቀሙን እና መኪኖች መቃጠላቸውን የዐይን እማኞች ለቢቢሲ ትግርኛ ገልጸዋል። ግጭቱ በተካሄደበት ስፍራ በርካታ ሰዎች በጎዳና ላይ የታዩ […]

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት የአዲስ አበባ ቆይታቸውን አቋርጠው ወደ ሞቃዲሾ ተመለሱ

18 የካቲት 2024, 10:47 EAT የሶማሊያው ፕሬዝዳንት የኢትዮጵያ መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ላይ እንዳይገኙ እንቅፋት ሆነውባቸው እንደነበር ከከሰሱ በኋላ የአዲስ አበባ ቆይታቸውን አቋርጠው ወደ አገራቸው መመለሳቸው ተዘገበ። ኢትዮጵያ ነጻ አገርነቷን ካወጀችው ሶማሊላንድ ጋር የመግባቢያ ሰነድ መፈራረሟን ተከትሎ ሶማሊያ ተቃውሞዋን በማሰማት በሁለቱ አገራት መካከል ውዝግብ መፈጠሩ ይታወቃል። በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት ከሻከረ […]

‘ንቦችን ለማገዝ’ የማር እንጀራን በ3ዲ የሚያትመው ኢትዮጵያዊ ወጣት

18 የካቲት 2024 ናትናኤል በኃይሉ ተወልዶ ያደገው በነጭ ማር ምርት በምትታወቀው አዲግራት፣ ትግራይ ክልል ውስጥ ነው። ከአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ በኤሌክትሮ ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ተመርቋል። የተማረበትን ሙያ እና የልጅነት ህልሙን ማገናኘት ሲፈልግ ወደ አእምሮው ብቅ ያሉት ‘ትጉሆቹ ንቦች’ ናቸው። የንቦች ነገር ሁሌም ይመስጠዋል፤ በኅብረት ይሠራሉ፤ በሕብረት ያመርታሉ። ታታሪነታቸው ከየትኛውም ነፍሳት የተለየ ነው። እናም የመጀመሪያ […]

ከዩኒቨርስቲ ትምህርት ብስክሌትን የመረጠው ኢትዮጵያዊ ብስክሌተኛ በዓለም አቀፍ ውድድር ላይ

18 የካቲት 2024 ኢትዮጵያዊው ኪያ ጀማል ሮጎራ የዓለም አቀፉ የብስክሌት ማዕከል ተወዳዳሪ ሆኖ በቱር ደ ሩዋንዳ ለመሳተፍ ኪጋሊ ተገኝቷል። ቱር ደ ሩዋንዳ በየዓመቱ የሚደረግ በአፍሪካ አሉ ከሚባሉ የብስክሌት ውድድሮች ቁንጮው ሲሆን፣ ዓለም ያወቃቸው ብስክሌተኞች ይሳተፉበታል። በቱር ደ ፍራንስ 10 ጊዜ ተወዳድሮ 4 ጊዜ ያሸነፈው እንግሊዛዊው ክሪስ ፍሩም ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት ለመሳተፍ ሩዳንዳ መጥቷል። ፍሩም የፈረንሳዩን […]

ዶናልድ ትራምፕ በስማቸው የሚጠራውን አዲስ የስኒከር ጫማ ምርትን አስተዋወቁ

18 የካቲት 2024, 09:30 EAT የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በራሳቸው ድርጅት የተመረተ እና በስማቸው የሚጠራ የስኒከር ጫማ ምርትን ይፋ በማድረግ ለገበያ አስተዋወቁ። በሚቀጥለው ዓመት በሚደረገው ምርጫ ላይ በድጋሚ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ለመሆን ለዕጩነት እየተፎካከሩ ያሉት ትራምፕ፣ ፊላዴልፊያ የስኒከር ጫማ ወዳጆች በተሰበሰቡበት ማዕከል ውስጥ ተገኝተው ነው አዲሱን ምርት ያስተዋወቁት። “ትራምፕ” የሚል ስያሜ ያለው እና 399 ዶላር […]

የምልምል ወታደሮች እጥረት የገጠማት ጃፓን ወጣቶችን ለማበረታታት ለውጥ እያደረገች ነው

18 የካቲት 2024, 09:04 EAT ጃፓን በርካታ ወጣቶች ጦር ሠራዊቷን እንዲቀላቀሉ ለማበረታታት በሚል በወታደሮቿ የፀጉር ቁርጥ ደንብ ላይ ለውጥ ማድረጓን አስታወቀች። በዚህም ጃፓንን ጨምሮ በበርካታ የዓለም አገራት ጦር ሠራዊቶች ውስጥ ወታደሮች ፀጉራቸውን በአጭር እንዲከረከሙ የሚያዘውን ደንብ በመለወጥ አዳዲስ ምልምሎች ፀጉራቸውን እንዲያሳድጉ ተፈቅዶላቸዋል። ጃፓን ይህንን ለውጥ ያደረገችው በዙሪያዋ ካሉት ቻይና እና ሰሜን ኮሪያ በኩል ወታደራዊ ስጋት […]

ለ35 ዓመታት የኬጂቢ ሰላይ የነበረው የፈረንሳዩ ታዋቂ መጽሄት ዋና አዘጋጅ

18 የካቲት 2024, 08:10 EAT የታዋቂው የፈረንሳይ መጽሄት ‘ኤል ኤክስፕረስ’ ስመጥር የቀድሞ ዋና አዘጋጅ ፊሊፕ ግሩምባች ለ35 ዓመታት ያህል ለሶቭየት ኅብረት ሲሰልል እንደነበር በመጨረሻ ይፋ አድረጓል። ግሩምባች ለበርካታ አስርት ዓመታት በሥራው በፈረንሳይ ሕዝብ ዘንድ ከፍ ያለ ስም ያለው ሰው ነበር። የአገሪቱ ፕሬዝዳንቶች፣ ተዋናዮች እንዲሁም ታላላቅ የሥነ ጽሑፍ ባለሙያዎች ቅርብ ጓደኞቹ ነበሩ። በጋዜጠኝነት ሙያው የአንቱታ ስፍራ […]