በአርሶ አደሮች ከብቶች እና የቤት እንስሳት ላይ ግብር ተጣለ

October 18, 2024 – Konjit Sitotaw  ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት፣ የውስጥ ገቢውን ለማሳደግ ሲል በአርሶ አደሮች እንስሳት ላይ ግብር መጣሉን እንደሰማ ጠቅሶ ሸገር ዘግቧል። የክልሉ መንግሥት አዲሱን ግብር የጣለው፣ የተሻሻለውን ‘’የገጠር መሬት መጠቀሚያ ክፍያና የግብርና ሥራ ገቢ ግብር አዋጅ መሠረት በማድረግ እንደሆነ ዘገባው ጠቅሷል። አዲሱ ግብር የተጣለው፣ አርሶ አደሮች በንብረትነት በያዟቸው የዳልጋ ከብት፣ ጋማ ከብት፣ ፍየል፣ በግ […]

ጎጃም ደቡብ ሜጫ ወረዳ ከ100 በላይ ሰዎች ተገድለዋል

October 18, 2024 – Konjit Sitotaw  በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ ሜጫ ወረዳ የመንግሥት ኃይሎች ከጥቅምት ወር መግቢያ ጀምሮ ፈጸሟቸው በተባሉ ጥቃቶች ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ቢቢሲ ዓይን እማኞችንና ነዋሪዎችን በመጥቀስ ዘግቧል። ጥቅምት 1 እኩለ ቀን ላይ በወረዳው ዋና ከተማ ገርጨጭ መሃል ገነት ጤና ጣቢያ ላይ በተፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች፣ አንድ የዘጠኝ ዓመት ሕጻንንና የጤና ባለሙያን ጨምሮ […]

የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የእርዳታ እህል እንደሚዘረፍ አውቃለሁ አለ

October 18, 2024  የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የእርዳታ እህል እንደሚዘረፍ ለበርካታ ዓመታት ያውቅ እንደነበር በምርመራ ማረጋገጡን ሮይተርስ ዘግቧል። ድርጅቱ ርምጃ ያልወሰደው፣ መንግሥት በጦርነቱ ወቅት ወደ ትግራይ የሚገቡትን የእርዳታ ካሚዮኖች ቁጥር ሊቀንስ ይችላል በሚል ስጋት እንደነበር መረዳቱን ዘገባው ጠቅሷል። የተዘረፈው የእርዳታ እህል ለመንግሥት ወታደሮችና ለሕወሓት ተዋጊዎች እንደሚውል ይታወቅ እንንደነበርም ከአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት የውስጥ ሰነድ መመልከቱን […]

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የ፵፫ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ መደበኛ ጉባኤ የአቋም መግለጫ

October 18, 2024  የአቋም መግለጫ፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የ፵፫ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ መደበኛ ጉባኤ የአቋም መግለጫ “ትውልደ ትውልድ ይንእዱ ምግባሪከ ወይዜንዉ ኃይለከ – የልጅ ልጅ ሥራህን ይናገራሉ፤ ያመሰግናሉ፣ ከሃሊነትህን ይናገራሉ ያስተምራሉ” መዝ 144 ቁ 4 ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊት፣ ዓለምአቀፋዊት የሆነቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሐዋርያዊ ተልዕኮዋ ረጅም ዘመናትን ሰማያዊውን ጥበብንና ምድራዊውን […]

ኢትዮጵያ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነው ህዝብ በድህነት ውስጥ እንደሚገኝ አንድ ጥናት አመላከተ

October 18, 2024 – Konjit Sitotaw  የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ባወጣው ሪፖርት በዓለም ከ1.1 ቢሊዮን የሚበልጡ ሰዎች በአስከፊ ድህነት ውስጥ እንደሚኖሩ አስታውቋል፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ አምስት ሀገራት በከፋ ድህነት ውስጥ የሚገኙ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ያላቸው ሀገራት ሲል ኦክስፎርድ የድህነት እና የሰብአዊ ልማት ኢኒሼቲቭ በሪፖርቱ አስታውቋል፡፡ ከተጠቀሱት አምስት ሀገራት ህንድ፣ ፓኪስታን፣ ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከ1 […]

በአማራ ክልል በዳኞች ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘፈቀደ እስር በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል›› የክልሉ ዳኞች ማህበር

October 18, 2024 – Konjit Sitotaw በአማራ ክልል በዳኞች ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘፈቀደ እስር በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል›› የክልሉ ዳኞች ማህበር በአማራ ክልል እየተፈጸመ ያለው የዳኞች አስር፣ ማዋከብና መሰል ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች ካለፈው አንድ አመት ወዲህ ተባብሶ ቀጥሏል ያለው የአማራ ክልል ዳኞች ማህበር ድርጊቱን ባወጣው መግለጫ አውግዟል፡፡ የዳኞችን ነጻነት መጠበቅ ህገ-መንግስታዊ መብት ሆኖ የተደነገገ ቢሆንም ይህንን አክብሮ ከመንቀሳቀስ አኳያ […]

ሐማስ መሪው ያህያ ሲንዋር መገደሉን አረጋግጦ ትግሉን እንደሚቀጥል አስታወቀ

18 ጥቅምት 2024, 17:57 EAT የሐማስ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሆኑት ኻሊል አል-ሃያ የቡድኑ የፖለቲካ እና ወታደራዊ አዛዥ የነበረው ያህያ ሲንዋር ጋዛ ውስጥ መገደሉን አረጋገጡ። ሐሙስ እስራኤል ያህያ ሲንዋርን መግደሏን ይፋ ካደረገች በኋላ የሐማስ ምክትል መሪ በቪዲዮ በተላለፈ መልዕክት መሪያቸው መገደሉን ነገር ግን የእርሱ ሞት ቡድኑን የበለጠ ያጠናክረዋል ብለዋል። ባለሥልጣኑ ጨምረውም ሐማስ የፍልስጤማውያንን ምኞት እውን ለማድረግ የጀመረውን […]

በጫሞ ሐይቅ ላይ ጀልባ ተገልብጦ 13 ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁን ፖሊስ ገለጸ

ከ 9 ሰአት በፊት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ በሚገኘው ጫሞ ሐይቅ ላይ ሲጓዝ የነበረ ጀልባ ተገልብጦ ከአስር በላይ ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁ ተገለጸ። ሐሙስ ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም. ከቀኑ 10 ሰዓት አካባቢ ከአርባ ምንጭ በጫሞ ሐይቅ ላይ ሙዝ እና 16 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረው ጀልባ ተገልብጦ 13 ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁን የጋሞ ዞን ፖሊስ ለቢቢሲ ገለጸ። ሰዎች እና […]

በሰሜን ጎጃም ዞን ድሮንን ጨምሮ በተፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የዓይን እማኞች ተናገሩ

18 ጥቅምት 2024, 13:41 EAT በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ ሜጫ ወረዳ “የመንግሥት ኃይሎች” ከጥቅምት ወር መጀመሪያ አንስቶ ፈጸሟቸው በተባሉ ጥቃቶች ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የዓይን እማኞች እና ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ። በወረዳው ዋና ከተማ ገርጨጭ ከጥቅምት 01 እስከ ጥቅምት 04/2017 ዓ.ም. በድሮን ጥቃት እና በዘፈቀደ በተፈጸሙ ጥቃቶች ህጻናትን ጨምሮ ሽማግሌዎች እንዲሁም ወጣቶች መገደላቸውን የሟች […]

በሁለት ሳምንት ውስጥ በአማራ ክልል 11 ዳኞች መታሰራቸው ተነገረ

18 ጥቅምት 2024, 15:42 EAT የአማራ ክልል ዳኞች ማኅበር ከመስከረም ወር መጨረሻ ወዲህ ባሉት ሁለት ሳምንታት 11 ዳኞች ያለ አግባብ ታስረዋል ሲል ገለጸ። ባለመረጋጋት ውስጥ በሚገኘው የአማራ ክልል ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ የሚገኙ ዳኞች “ያለ አግባብ ሲታሰሩ እና ሲዋከቡ” እንደነበር ማኅበሩ ገልጿል። ባለፈው ዓመት ከ35 በላይ ዳኞች ያለ አግባብ ታስረው እንደነበር የጠቀሰው ማኅበሩ፤ “በወንጀል ምርመራ […]