የኮንስትራክሽን ጥሬ ዕቃዎችን ከቀረጥ ነፃ ለማስገባት የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ሊዘጋጅ ነው

በተመስገን ተጋፋው June 2, 2024 መንግሥት የኮንስትራክሽን ዘርፉን ለመደገፍ ከውጭ የሚገቡ ጥሬ ዕቃዎችን ከቀረጥ ነፃ ለማስገባት የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ሊያዘጋጅ መሆኑን፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት ‹‹ቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ›› የተሰኘ ድርጅት፣ ከግንቦት 22 እስከ 24 ቀን 2016 ዓ.ም. የሚቆይ ዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዓውደ ርዕይና ሲምፖዚየም ላይ ተገኝተው […]

የንግድና መረጃ ማዕከል ለመፍጠር የተጀመረው የኢንዱስትሪዎች ቆጠራ በመስከረም ወር እንደሚጠናቀቅ ተነገረ

በተመስገን ተጋፋው June 2, 2024 በአገር አቀፍ ደረጃ ከአነስተኛ እስከ ከፍተኛ ያሉ የኢንዱስትሪ ተቋማት፣ የራሳቸው የንግድ መረጃ ማዕከል ኖሯቸው በምርትና በግብዓት ትስስር እንዲፈጥሩ ለማድረግ የተጀመረው ቆጠራ፣ በመስከረም ወር 2017 ዓ.ም. እንደሚጠናቀቅ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የኢንዱስትሪዎች ቆጠራ በኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት አማካይነት እየተደረገ መሆኑንና በ2016 ዓ.ም. ሚያዝያ ወር ውስጥ ለሙከራ ያህል በደብረ ብርሃን፣ በወላይታ ሶዶ፣ በአምቦና በአዳማ […]

በግጭት ሳቢያ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ህክምና አያገኙም

Saturday, 01 June 2024 20:44 Written by  Administrator  ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ፣ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ግጭት በማገርሸቱ ሳቢያ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የሕክምና አገልግሎት እያገኙ አለመሆኑን  አስታውቋል። በኢትዮጵያ የኮሚቴው ቡድን መሪ ኒኮላስ ቮን አርክስ እንደተናገሩት፣ ኮሚቴው በግጭቱ ቀጥተኛ ተሳታፊ ከሆኑ ሃይሎች ጋር በመገናኘት ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ሕጎችን እንዲያከብሩ በተደጋጋሚ እየወተወተ  ይገኛል።ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ላይ የተቀሰቀሰው […]

በደቡብ ጎንደር የእናት ፓርቲ ሰብሳቢ ታሰሩ

Addis Admas  Saturday, 01 June 2024 20:44 Written by  Administrator የደቡብ ጎንደር ዞን፣ ታች ጋይንት ወረዳ፣ የእናት ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ዲበኩሉ፣ በጸጥታ ሃይሎች መታሰራቸውን ፓርቲው አስታውቋል።  ”የአባላቱ እስራት የፖለቲካ ስብራታችን አንድ ማሳያ ነው” ብሏል፤ እናት።ፓርቲው ሰሞኑን በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ባሰራጨው መረጃ፤ አቶ ሰለሞን ዲበኩሉ በጸጥታ ሃይሎች ተይዘው የታሰሩት ግንቦት 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ነበር። በአሁኑ […]

ኢትዮጵያ በበርበራ ወደብ ነዳጅ ለማስገባት መስማማቷን የበርበራ ከተማ ከንቲባ ገለጹ

Saturday, 01 June 2024 20:47 Written by  Administrator ኢትዮጵያ በሶማሌላንድ፣ በርበራ ወደብ በኩል ነዳጅ ለማስገባት መስማማቷን የበርበራ ከተማ ከንቲባ አብዲሽኩር መሃሙድ ሃሰን ተናግረዋል። ከንቲባው ይህንን የተናገሩት የሶማሌላንድ የነጻነት በዓል በአዲስ አበባ የሶማሌላንድ ኤምባሲ በተከበረበት ወቅት ነው።አብዲሽኩር፤ ኢትዮጵያ የነዳጅ ምርት የምታስመጣበትን ወደብ ወደ በርበራ እንደምትቀይር ያብራሩ ሲሆን፣ የገቢ ምርቶቿንም ለማስገባት ወደቡ ዝግጁ መሆኑን  ጠቅሰዋል።ከንቲባ አብዲሽኩር መሃሙድ ንግግር […]

የአምናው ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳት ዓላማ ተረሣ? ወይስ ዓላማው ሌላ ነበር?

June 2, 2024 የአምናው ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳት ዓላማ ተረሣ? ወይስ ዓላማው ሌላ ነበር?++++++++(ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ)ቅዱስ ሲኖዶስ አሁን እንደወሰነው ከሆነ ሰፊ የጳጳሳት ዝውውር ተፈጽሟል። ከአንዱ ሀገረ ስብከት ወደሌላው የተደረገው ይህ ዝውውር ትኩረትን የሚስበው ጳጳሳትን ማዘዋወር አዲስ ነገር ሆኖ ሳይሆን የተዘዋወሩት አባቶች እና ይዘዋቸው የነበሩት አህጉረ ስብከቶች ባለፉት ዓመታት ትልቅ መነጋገሪያ የነበሩ መሆናቸው ነው። በ2015 ዓ/ም በነበረው […]

የተመድ ‘ሰላም አስከባሪዎች ቀን’

June 2, 2024 – DW Amharic  ዓለም አቀፉ የተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪዎች ቀን ለሰላም ሲሉ ሕይወታቸውን ላጡ ከ4,000 የሚበልጡ የሰላም አስከባሪዎ ጓዶችን አስቦ ዉሏል። የተባበሩት መንግሥት የሰላም አስከባሪ ጓዶች ላለፉት 75 ዓመታት በአፍሪቃ፣ በእስያ፣ በአውሮጳና በመካከለኛው ምሥራቅ በግጭት በተጠቁ አካባቢዎች ሠላምን በማስከበር ሲያገለግሉ ዘልቀዋል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የደቡብ አፍሪቃ ምርጫ: ጥምር መንግሥት ያስፈለገዉ ANC

June 2, 2024 – DW Amharic  በፕሬዝዳንት ሲረል ራማፎሳ የሚመራው የደቡብ አፍሪቃ ገዥ ANC ፓርቲ አብላጫ ድምፅ ሳያጣ አይቀርም፤ ጥምር መንግሥት መመስረት ይኖርበታል፤ የሚል የሕዝብ አስተያየቶች የተሰሙበት ምርጫ፤ የድምፅ ቆጠራዉ እየተካሄደ ነዉ። ባለስልጣናት ከፍተኛ መራጮች የታዩበት ምርጫ ሲሉ አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

ሪያል ማድሪድ ዌምብሌይ ላይ ዶርትሙንድን በማሸነፍ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን አነሳ

ከ 6 ሰአት በፊት ሪያል ማድሪድ ቦሪስያ ዶርትሙንድን 2 ለምንም በማሸነፍ የአውሮፓ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን አነሳ። ዶርትሙንድ በተለይም በመጀመሪያው አጋማሽ ያባካናቸውን ዕድሎች ተጽዕኖ ያልፈፈጠሩበት ማድሪድ ለ15ኛ ጊዜ የአውሮፓ ትልቁን ዋንጫ ለማንሳት ችሏል። አሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲም አምስተኛ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫቸውን በማንሳት ታሪክ ለመጻፍ በቅተዋል። የዶርትሞንዶቹ ካሪም አድዬሚ እና ኒክላስ ፉልከርግ ያገኟቸውን ዕድሎች ሳይጠቀሙባቸው ቀርተዋል። ማድሪድ በሁለተኛው […]

የእስራኤል ሚኒስትሮች አገራቸው የተኩስ አቁም ለማድረግ ከተስማማች ጥምር መንግሥቱን እናፈርሳለን ሲሉ ዛቱ

ከ 6 ሰአት በፊት ሁለት ቀኝ ዘመም የእስራኤል ሚኒስትሮች አገራቸው የተኩስ አቁም ለማድረግ ከተስማማች ጥምር መንግሥቱን አፍርሰን ስልጣን እንለቃለን ሲሉ ዛቱ። ሁለቱ ሚኒስትሮች ይህን ያሉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በጋዛ ያለውን ጦርነት ለማስቆም አማራጭ ያሉትን መፍትሄ ማቅረባቸውን ተከትሎ ነው። የፋይናንስ ሚኒስትር ቤዛሌል ስሞትሪች እና የብሔራዊ ደኅንነት ሚኒስትር አታማር ቤን-ጋቪር ሐማስ ሙሉ በሙሉ ሳይወገድ እስራኤል ወታደራዊ […]