የቻይና እግር ኳስ ማኅበር ፕሬዝዳንት በሙስና ወንጀል በዕድሜ ልክ እስራት ተቀጡ

ከ 3 ሰአት በፊት የቀደሞው የቻይና እግር ኳስ ማኅበር ፕሬዝዳንት ቼን ዡዩዋን በሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው የዕድሜ ልክ አስራት ተፈረደባቸው። ባለፈው ጥር ፕሬዝዳንቱ 81 ሚሊዮን ዩዋን (11.2 ሚሊዮን ዶላር) በጉቦ መልክ መውሰዳቸውን አምነው ነበር። የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ የሚመሩት ፀረ-ሙስና እንቅስቃሴ በስፖርት፣ በባንክ እና በወታደራዊ ዘርፎች በሙስና ውስጥ እጃቸው ያለበት ሰዎችን ዘብጥያ እያወረዱ ነው። […]

አይኤስ ሩሲያን እንደ ጠላት የሚያያት ለምንድን ነው? እንዴትስ ሞስኮ ውስጥ ጥቃት ሊፈጽም ቻለ?

ከ 9 ሰአት በፊት አርብ ምሽት መጋቢት 13/2016 ዓ.ም. በሩሲያዋ መዲና ሞስኮ በሚገኘው የሙዚቃ አዳራሽ ላይ ጥቃት በደረሰ በሰዓታት ጊዜ ውስጥ ኢስላሚክ ስቴት (አይኤስ) በቴሌግራም ገፁ ኃላፊነት የወሰደው። ጽንፈኛው የሱኒ ቡድን አይኤስ እንደ ማረጋገጫ ጥቃቱ ሲደርስ የሚያሳይ ቪድዮ አብሮ የለቀቀ ሲሆን፣ ዩናይትድ ስቴትስ ደግሞ ትክክለኛ ነው የሚል ማረጋገጫ ሰጥታለች። አሜሪካ ጥቃቱ ከመፈጸሙ ከቀናት በፊት በሩሲያ […]

የአሜሪካ ፌዴራል ፖሊስ የራፐር “ዲዲ” መኖሪያ ቤቶች ላይ ድንገተኛ ፍተሻ አደረገ

ከ 8 ሰአት በፊት ሾን “ዲዲ” ኮምብስ የተሰኘው ጉምቱው ራፐር መኖሪያ ቤት ሰኞ ዕለት በአሜሪካ ፌዴራል ፖሊስ ፍተሻ እንደተደረገበት ተዘገበ። ሆምላንድ ሴኪዩሪቲ የተሰኘው የሀገር ውስጥ ፀጥታ መሥሪያ ቤት እንደገለጠው “እያደረገው ባለው ምርመራ መሠረት” ኒው ዮርክ፣ ሎስ አንጀለስ እና ማያሚ ያሉ ንብረቶች ላይ ፍተሻ አድርጓል። ሎስ አንጀለስ እና ማያሚ የሚገኙ የራፐሩ ሁለት መኖሪያ ቤቶች ፍተሻ ተደርጎባቸዋል። […]

በሚሊዮን የሚቆጠሩ አሜሪካውያን በቻይና የመረጃ መንታፊዎች ወጥመድ መያዛቸው ተነገረ

ከ 8 ሰአት በፊት በሚሊዮን የሚቆጠሩ አሜሪካውያን የኢንተርኔት ‘አካውንቶች’ የቻይና ዜግነት ባላቸው መረጃ መንታፊዎች በዘረጉት እና እጅግ አደገኛ በሆነ ወጥመድ መያዛቸውን የአሜሪካ ባለስልጣናት፣ የፍትህ ቢሮ እና ኤፍ ቢ አይ ገልጸዋል። በዚህ መጠነ ሰፊ የመረጃ ምንተፋ ወይም ‘ሳይበር አታክ’ ዘመቻ ላይ እንደተሳተፉ የተጠረጠሩ 7 ቻይናውያን ክስ ተመስርቶባቸዋል። ተከሳሾቹ 14 ዓመታት አስቆጥሯል በተባለው የዚህ የመረጃ ምንተፋ ስራ […]

የሩሲያ የመንግሥት ሚዲያዎች ለጥቃቱ ዩክሬን እና ምዕራባውያንን ተጠያቂ አደረጉ

ከ 7 ሰአት በፊት የሩሲያ የመንግሥት መገናና ብዙኃን የ137 ሰዎችን ሕይወት ለቀጠፈው ጥቃት ዩክሬን እና ምዕራባውያንን ተጠያቂ አደረጉ። በሞስኮ አቅራቢያ በሚገኘው ክሮከስ አዳራሽ የሮክ ሙዚቃ ለመታደም በተገኙ ሰዎች ላይ የተከፈተውን ተኩስም በምዕራባውያኑ እንደተቀነባበረ በክሬምሊን የተነገረውን መገናኛ ብዙኃኑ አጽንኦት ሰጥተው ዘግበዋል። ዩክሬን በጥቃቱ ላይ ምንም ተሳትፎ የለኝም ስትል አስተባብላለች። ኤንቲቪ የተሰኘው የሩሲያ የመንግሥት ሚዲያ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ […]

የፀጥታው ምክር ቤት በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ውሳኔ አሳለፈ

ከ 8 ሰአት በፊት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በጋዛ አስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ውሳኔ አስተላለፈ። በውሳኔው ላይ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብቷን ያልተጠቀመችው አሜሪካ በቀደመ አቋሟ አለመቀጠሏ ታይቷል። ውሳኔው ታጋቾች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እና በፍጥነት እንዲለቀቁም ጠይቋል። መስከረም ማብቂያ ላይ ከተጀመረው ጦርነት በኋላ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ሲወሰን ይህ የመጀመሪያው ነው። አሜሪካ ያሳየችው አቋም ከእስራኤል […]