የሶማሊያው ፕሬዝዳንት በሁለት ወራት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ለጉብኝት አሥመራ ገቡ

ከ 8 ሰአት በፊት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በሁለት ወራት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ከልዑካን ቡድናቸው ጋር ለሥራ ጉብኝት ወደ ኤርትራ ዋና ከተማ አሥመራ መግባታቸው ተገለጸ። የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በኤክስ ገጻቸው ላይ እንደገለጹት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ዛሬ እሁድ መጋቢት 8/2016 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ አሥመራ ገብተዋል። የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ጉብኝት በኤርትራው ፕሬዝዳንት […]

ማሊያዊ- ፈረንሳዊቷ አያ በፓሪስ ኦሊምፒክ መክፈቻ ላይ ትዘፍናለች መባሉ ያስነሳው ውዝግብ

ከ 7 ሰአት በፊት በዓለም ላይ ስማቸው ከገነነ ሙዚቀኞች መካከል አንዷ ናት – አያ ናካሙራ። አያ በፈረንሳይኛ በመዝፈን ከቋንቋው ተናጋሪዎች ባሻገር በዓለማችን ተደማጭ ከሆኑ ጥቂት ሙዚቀኞች መካከል አንዷ ናት። ጃጃ (Djada) የሚለው ሙዚቃዋ በዩቲዩብ 954 ሚሊዮን ተመልካቾችን አግኝቷል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ነው በሐምሌ ወር በሚከፈተው የፓሪስ ኦሊምፒክስ ላይ የ28 ዓመቷ አያ እንድትዘፍን በአገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል […]

የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዋን ወደ ትልቅ ቢዝነስ ያሸጋገረችው ኢትዮጵያዊት

ከ 6 ሰአት በፊት ካባና ዲዛይን ከመደበኛ ሥራ ውጪ በትርፍ ጊዜ ከሚሠራ የጊዜ ማሳለፊያ ‘ሆቢ’ የተወለደ እና ጥቂት ለማይባሉ ሰዎችም ሥራ እና ተስፋን ያስገኘ የሥራ ፈጠራ ሙከራ ነው። የሰመሃል ጉዕሽ የትርፍ ጊዜ ሥራ የነበረው ካባና ዲዛይን አሁን ከ100 በላይ ሠራተኞች ያሉት ሲሆን፣ ተፈላጊ የቆዳ ውጤቶችን በማምረት ለውጭ ገበያ ከማቅረቡ በተጨማሪ፣ ጥቂት ለማይባሉ ሴት ባለሙያዎች ዕድልን […]

አሜሪካ በአመጽ እየታመሰች ካለችው ሄይቲ ዜጎቿን በልዩ በረራ ልታስወጣ ነው

ከ 6 ሰአት በፊት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በወንበዴ ቡድኖች እየታመሰች ካለችው ሄይቲ ዜጎችን በልዩ በረራ እንደሚያስወጣ አስታወቀ። የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ መውጫ አጥተው በሄይቲ ለሚገኙ አሜሪካውያን ከመዲናዋ 200 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቃ ከምትገኘው ካፕ-ሄይሺየን ከተማ በረራ እንደሚደረግ ለዜጎቹ መልዕክት አስተላልፏል። ሚኒስቴሩ በመልዕክቱ በረራው የሚደረገው በካፕ-ሄይሺየን ያለው የጸጥታ ሁኔታ የተረጋጋ ከሆነ ብቻ መሆኑን እና አውሮፕላኑን […]

ቮውን ገተን የመጀመሪያው ጥቁር የዌልስ መሪ ሊሆኑ ነው

ከ 5 ሰአት በፊት ከጥቁር ዛምቢያዊት እናት እና ከነጭ የዌልስ አባት የተወለዱት ቮውን ገተን የመጀመሪያው ጥቁር የዌልስ መሪ ሊሆኑ ነው። ቮውን ገተን በዌልስ ሠራተኞች ፓርቲ የአመራር ምርጫ 51.7 በመቶ ድምጽ በማግኘት ተቀናቃኛቸውን በጠባብ ድምጽ አሸንፈዋል። የገተን ተፎካካሪ የነበሩት ጄሬሚ ማይልስ 48.3 በመቶ ድምጽ አግኝተዋል። ቮውን ገተን በአሁኑ ወቅት የዌልስ ተቀዳሚ ሚኒስትር የሆኑትን ማርክ ደሬክፎርድን በመተካት […]

የዩናይትድ አየር መንገድ ቦይንግ አውሮፕላን አንድ አካሉ ጠፍቶበት ምንም ጉዳት ሳይደርስበት አረፈ

ከ 5 ሰአት በፊት በአሜሪካዋ ኦሬገን ግዛት አንድ የዩናይትድ አየር መንገድ ንብረት የሆነ ቦይንግ አውሮፕላን የአውሮፕላን አካል ጠፍቶ ሳለ ያለምንም ጉዳት ማረፉ ተሰምቷል። የበረራ ቁጥሩ 433 የሆነው አውሮፕላን ከሳን ፍራንሲስኮ ተነስቶ ሮግ ቫሊ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሥፍራው ሰዓት አቆጣጠር 5፡30 አርፏል። 25 ዓመት የሞላው ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን 139 መንገደኞች እና 6 የበረራ ሠራተኞችን ጭኖ […]