ዶናልድ ትራምፕ ከካማላ ሃሪስ ጋር ሁለተኛ ዙር የምርጫ ክርክር አላደርግም አሉ

ከ 7 ሰአት በፊት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ ጋር ሁለተኛ ዙር የቴሌቪዥን የምርጫ ክርክር ለማድረግ የቀረበላቸውን ጥያቄ ውድቅ አደረጉ። ጥቅምት አጋማሽ ላይ ሲኤንኤን ቴሌቪዥን ሊያካሂድ ያቀደውን የፕሬዝዳንታዊ ዕጩዎች ሁለተኛ ዙር ክርክር ካማላ ሃሪስ ሲቀበሉት፣ ትራምፕ ግን ክርክር ለማድረግ “ጊዜው በጣም ረፍዷል” በማለት በክርክሩ እንደማይሳታፉ ለደጋፊዎቻቸው ገልጸዋል። ትራምፕ ከጥቂት ሳምንታት በፊት […]

የዓለማችን ቁጥር አንዱ ‘ዩቲዩበር’ ሚስተር ቢስት በአምስት ሴቶች የተከሰሰው ለምንድነው?

ከ 7 ሰአት በፊት ግማሽ ቢሊዮን ተከታዮች ያሉት ሚስተር ቢስት በኢንተርኔት ዓለም ‘እጅግ መልካም’ ከሚባሉ ሰዎች መካከል ነው። ጂሚ ዶናልድሰን በተባለ የመዝገብ ስሙ የሚታወቀው ሚስተር ቢስት ፕራይም ቪድዮ በተሰኘው የቪድዮ ማሠራጫ ላይ በቅርቡ በሚተላለፈው ‘ጌም ሾው’ ምክንያት ነው ክስ የቀረበበት። የዚህ ‘ጌም ሾው’ ተሳታፊ የሆኑ አምስት ሴቶች ናቸው የሚስተር ቢስትን ኩባንያ እና የፕራይም ቪድዮ ባለቤት […]

ፓኔንካ – የጀርመኖችን ልብ የሰበረው አነጋጋሪው የፍፁም ቅጣት ምት አመታት

ከ 8 ሰአት በፊት የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ሽርሽር ለመሄድ ጓጉተዋል። በአውሮፓውያኑ 1976 የተደረገው የአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ወደ ፍፁም ቅጣት ምት ይሄዳል ብሎ ማንም አልጠበቀም። የቀድሞው የአውሮፓ ዋንጫ እንዲሁም በወቅቱ የዓለም ዋንጫ ባለቤት የነበረችው ምዕራብ ጀርመን ቼኮዝሎቫኪያን እንደምትረታ የተጠራጠረ አልነበረም። የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ያሳሰባቸው ዋንጫውን ካነሱ በኋላ የሚያደርጉት ሽርሽር ነው። መጀመሪያ ዕቅዱ የነበረው ግጥሚያው […]

የእስራኤል ወታደሮች የቀጥታ ሥርጭት እያስተላለፈ የነበረው የአል ጀዚራ ቢሮን በመውረር ዘጉ

ከ 8 ሰአት በፊት የእስራኤል ወታደሮች በወረራ ስር ባለው ዌስት ባንክ ውስጥ የሚገኘውን የአል ጀዚራ ቢሮን በመውረር ለቀጣዮቹ 45 ቀናት የቴሌቪዥን ጣቢያው ቢሮ እንዲዘጋ አዘዙ። የታጠቁ እና ፊታቸውን በጭምብል የሸፈኑ የእስራኤል ወታደሮች በቀጥታ ሥርጭት ላይ የነበረውን የአል ጀዚራ የራማላ ቢሮን የወረሩት እሁድ ማለዳ ላይ ነው። ወታደሮቹ በዌስት ባንክ የሚገኘው የቴሌቪዥን ጣቢያው ቢሮ እንዲዘጋ የሚያዘውን ደብዳቤ […]

ወደ ሰሜን ኮሪያ በመሸሽ እስር ተፈርዶበት የነበረው የአሜሪካ ወታደር ተለቀቀ

21 መስከረም 2024, 13:57 EAT ባለፈው ዓመት ከደቡብ ወደ ሰሜን ኮርያ በሕገ ወጥ መንገድ አቋርጦ የተያዘው ትሬቪስ ኪንግ፣ በትናንትናው ዕለት የአንድ ዓመት እስር ተፈርደበት። ትሬቪስ ኪንግ የተባለው የአሜሪካ ወታደር ወደ ሰሜን ኮርያ ከሸሸ በኋላ ወደ አሜሪካ እንዲመለስ ተደርጎ ክስ የተመሰረተበት ባለፈው ሐምሌ ወር ነበር። በትናንትናው ዕለት ከሥራ ገበታው ላይ በመጥፋት እና ባልደረባው ላይ ጥቃት በመፈጸም […]

ከሄዝቦላህ የመገናኛ መሳርያዎች ፍንዳታ ጋር ተያይዞ እስካሁን ምላሽ ያላገኙ ጥያቄዎች

21 መስከረም 2024, 08:40 EAT በሊባኖስ በሁለት የተለያዩ ሥፍራዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ፔጀሮች እና የሬድዮ መገናኛ መሳርያዎች ፈንድተው ቢያንስ 37 ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። እስካሁን ድረስ እንዲህ ዓይነት ጥቃት እንዴት ሊደርስ እንደቻለ ለማወቅ ጥረት እየተደረገ ነው። ሊባኖስ እና የመገናኛ መሳርያዎቹ ዒላማ የተደረጉበት ሄዝቦላህ እስራኤል ላይ ጣታቸውን ቀስረዋል።በእርግጥ እስራኤል ያለችው ነገር የለም። […]