እስራኤል እና ሐማስ ከስምምነት ለመድረስ ተቃርበዋል፤ የተኩስ አቁም ምንድን ነው? ጦርነትን ያስቆማል?
25 ነሐሴ 2024 ተሻሽሏል 15 ጥር 2025 የባሕረ ሰላጤዋ አገር ኳታር አደራዳራዳሪዎች እንደሚሉት እስራኤል እና ሐማስ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ ከጫፍ ደርሰዋል። እስራኤል በሐማስ የተፈጸመባትን ድንገተኛ ጥቃት ተከትሎ በጋዛ ላይ እያካሄደችው ያለው መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ 15 ወራትን ሊያስቆጥር በተቃረበበት ጊዜ ነው ሁለቱ ወገኖች ከስምምነት ለመድረስ መቃረባቸው የተነገረው። እስራኤል ሐማስን አጠፋለሁ ብላ በጋዛ ላይ […]
የግብፅ ባለሥልጣናት የቀይ ባሕር የጀልባ አደጋን ለመሸፋፈን ሞክረዋል ሲሉ ከአደጋው የተረፉ ሰዎች ከሰሱ
ከ 6 ሰአት በፊት ወደ ባሕር ለመጥለቅ ጥቅም ላይ የሚውል ጀልባ በግብፅ መገልበጡን ተከትሎ ከአደጋው የተረፉ ሰዎች ባለሥልጣናትን ከሰዋል። ጀልባው የተገለበጠው ቀይ ባሕር ላይ ነበር። ከአደጋው የተረፉ ሰዎች እንዳሉት አረብኛ ማንበብ ባይችሉም በአረብኛ የተጻፈ የዓይን እማኞች ሰነድ ላይ እንዲፈርሙ ተገደዋል። ጀልባውን ያከራየው ድርጅት “ተጠያቂ አይደለም” የሚል ጽሑፍ ላይም ያለዕውቅናቸው እንዲፈርሙ መደረጋቸውን ተናግረዋል። ከአደጋው የተረፉ 11 […]
የአዲስ አበባ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ‘መስፈርት አላሟሉም’ ያላቸውን 400 የሚሆኑ ሠራተኞችን ከሥራ አባረረ
ከ 9 ሰአት በፊት የአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት “በድልድል እና ምደባ” 400 የሚሆኑ ሠራተኞችን ከጥር ጀምሮ ከሥራ ማሰናበቱን ሠራተኞች እና ድርጅቱ ተናገሩ። በ2015 ዓ.ም. “የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት” በሚል ከ70 ዓመታት በላይ ለአዲስ አበባ የትራንስፖርት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው አንበሳ ባስ እና ሸገር ብዙኃን ትራንስፖርት ተዋህደው የልማት ድርጅት ተመሥርቷል። ይህን ተከትሎ “ሪፎርም” ማድረግ የጀመረው ድርጅቱ፤ባከናወነው […]
ናይጄሪያውያን በዘማሪ ጓደኛዋ ተቀልታ ለተገደለችው ሴት ሐዘናቸውን እየገለጹ ነው
15 ጥር 2025, 09:43 EAT ናይጄሪያውያን የፍቅር ጓደኛዋ ነው በተባለ ዘማሪ አንገቶ ተቀልቶ ለተገደለችው ሴት ሐዘናቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ እየገለጹ ነው። ፖሊስ ዘማሪውን ቲሚሌይ አጃይን በአንድ ቤተ ክርስቲያን አቅራቢያ በቁጥጥር ስር ሲያውለው የ24 ዓመቷን ሳሎሜ አዳይዱ ጭንቅላት ይዞ ነው። ወጣቷ አንገቷ ተቀልቶ የተገደለችው ናሳራዋ በተሰኘችው ግዛት ነው። ግለሰቡ ጭንቅላቷን በከረጢት ይዞ በሚንቀሳቀስበት ወቅት የአካባቢው ነዋሪዎችን ትኩረት […]
አሜሪካ ኩባን ከሽብር ፍረጃ ዝርዝሯ ልታስወግድ ነው
15 ጥር 2025, 08:01 EAT ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ሽብርተኝነትን በመንግሥት ደረጃ ስፖንሰር ታደርጋለች በሚል የተፈረጀችውን ኩባ ከዝርዝሩ ሊያስወጧት እንደሆነ ተናገሩ። ኩባን ከዚህ የሽብር ዝርዝር የሚያስወግዷት እስረኞችን ለመፍታት በተደረገ የስምምነት አካል እንደሆነ ዋይት ሃውስ አስታውቋል። የባይደንን ውሳኔ ተከትሎ ብዙም ሳይቆይ ኩባ “በተለያዩ ወንጀሎች” ያሰረቻቸውን 553 እስረኞች እንደምትፈታ አስታውቃል። ከሚፈቱት መካከል ከአራት ዓመታት በፊት በነበረው የኩባ […]
የዩኬ የግምጃ ቤት ሚኒስትር በባንግላዴሽ በቀረበባቸው የሙስና ክስ ከሥልጣናቸው ለቀቁ
15 ጥር 2025, 09:06 EAT የዩናይትድ ኪንግደም የግምጃ ቤት ሚኒስትር ቱሊፕ ሲዲቅ በባንግላዴሽ እየተካሄደባቸው ካለው የሙስና ምርመራ ጋር በተያያዘ በደረሰባቸው ጫና ከሥልጣናቸው ለቀቁ። ሚኒስትሯ ባለፈው ዓመት ከሥልጣናቸው ከተወገዱት አክስታቸው ጋር ባላቸው ግንኙነት ላይ ጥያቄ ከተነሳባቸው በኋላ ጉዳዩን ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ሲር ላውሪ ማንጉሰ ጋር ወስደውት ነበር። ሰር ላውሪም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ትክክለኛ […]
የነዳጅ መኪኖችን አስቀርታ የኤሌክትሪክ መኪኖችን በመጠቀም ቀዳሚ የሆነችው ኖርዌይ
15 ጥር 2025 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በመጠቀም ኖርዌይ በዓለማችን ቁንጮ ስፍራ ላይ ተቀምጣለች። ባለፈው ዓመት በኖርዌይ ካሉ አስር መኪኖች መካከል ዘጠኙ የኤሌክትሪክ መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ። ሌሎች አገራት ከኖርዌይ ምን መማር ይችላሉ? በኦስሎ መቀመጫውን ያደረገው የመኪና አምራቹ እና አስመጪው ሃራልድ ኤ ሞለር ባለፉት 75 ዓመታት ቮልስዋገን መኪኖችን ያስገባ ነበር። ባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ ግን በነዳጅ የሚሠሩ […]
የደቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት ለሰዓታት ከቆየ ፍጥጫ በኋላ በቁጥጥር ስር ዋሉ
15 ጥር 2025, 08:21 EAT የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣናት ወታደራዊ አገዛዝን ካወጁ በኋላ አመጽ አነሳስተዋል የተባሉትን ፕሬዚዳንት ዮን ሱክ ዮልን ከጠባቂዎቻቸው ጋር ለሰዓታት ከቆየ አስገራሚ ፍጥጫ በኋላ በቁጥጥር ስር አዋሉ። በዚህም በስልጣን ላይ እያሉ በቁጥጥር ስር የዋሉ የመጀመሪያው የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንት ለመሆን በቅተዋል። ዮን ወደ ሙስና ምርመራ ቢሮ መወሰዳቸው ታውቋል። “ምርመራውን ህገወጥ” ሲሉ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ “ያልተፈለገ […]
በቻይና የተከተሰው አዲሱ ቫይረስ እንዴት ይተላለፋል? ለምንስ ልጆች እና አዛውንቶችን ያጠቃል?
15 ጥር 2025 በቅርቡ በሰሜን ቻይና የኤችኤምፒቪ ቫይረስ መስፋፋት ስጋት ፈጥሯል። Human Metapneumovirus ወይም HMPV የሚባለው ቫይረስ የመጣው ዓለም በኮኖናቫይረስ ከተወረረች ከአምስት ዓመታት በኋላ ነው። በቻይና ሰባት ሚሊዮን ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሞተዋል። የቻይና ባለሥልጣናት እንዳሉት ዕድሜያቸው ከ14 ዓመት በታች ያሉ እና በኤችኤምፒቪ ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው። ሆኖም ግን ሆስፒታሎች በህሙማን ተጨናንቀዋል የሚለውን አስተባብለዋል። በቫይረሱ […]
በውጭ ምንዛሬ ለውጡ ሳቢያ የግል የቴሌቭዥን ጣቢያዎች እየተዘጉ ናቸው
January 14, 2025 – VOA Amharic የኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ምንዛሬ ፖሊሲ ለውጥ ማድረጉን ተከትሎ፣ የሳተላይት ስርጭት ኪራዩ በእጥፍ በመጨመሩ ለመክፈል መቸገራቸውንና ስርጭታቸውን አቋርጠው ለመውረድ መገደዳቸውን፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡ የቴሌቭዥን ሓላፊዎች ተናግረዋል፡፡ የአሜሪካ ድምፅ ባገኘው መረጃም መሠረት፣ በሳተላይት ስርጭታቸውን ከሚያስተላልፉ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች መካከል እስከ አሁን 13 የሚኾኑቱ ከሳተላይት… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ