ራሱን (IS) የሚለው ቡድን በሱማሊያ እየተጠናከረ መሆኑ ተገለጸ

September 19, 2024 – DW Amharic  ራሱን እስላማዊ መንግሥት በማለት የሚጠራው ቡድን፤ በእንግሊዝኛ ምህጻሩ (IS) ቀድሞ ከነበረባቸው ስፍራዎች ተሸንፎ ቢባረርም በሶማሊያ ግን እየተጠናከረ መምጣቱ ተገልጧል ። የሱማሌና ሌሎች መንግስታት በጋራና በተቀናጀ ርምጃ እንቅስቃሴውን እንዲገድቡም ዓለማቀፉ ጥሪ ተላልፏል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

ዶናልድ ትራምፕ ላይ የመግደል ሙከራ አድራጊው ምን ሆነ?

September 19, 2024 – DW Amharic  የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከዳግመኛ የመግደል ሙከራ ከተረፉ በኋላ የወደፊት የደሕንነታቸው ሁኔታ አነጋጋሪ ሁኗል ። የድያ ሙከራ በተደረገበት የጎልፍ መጫወቻ ሥፍራቸው ያለው ደሕንነት ምን ያህል ጥብቅ መሆኑን ጠባቂዎቻቸውን ጠይቀዋል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የሉሲ ወይም ድንቅነሽ ቅሪተ-አካል ግኝት 50ኛ ዓመት

September 19, 2024 – DW Amharic  በጎርጎሪያኑ ህዳር 1974 ዓ.ም. በአፋር የአዋሽ ስምጥ ሸለቆ የተገኘው የሉሲ ወይም የድንቅነሽ ቅሪተ አካል እነሆ 50 ዓመቱን ይዟል። 3.2 ሚሊዮን ዓመት ዕድሜ ያለው የሉሲ ቅሪተ-አካል ስለ ሰው ልጆች አመጣጥ ለማጥናት ዓለም አቀፋዊ ፍላጎት የቀሰቀሰ እና ቀደም ሲል ስለሰው ልጆች አመጣጥ የነበረውን ታሪክ እና አመለካከት የለወጠ ሆኗል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ […]

ግጭትና ጦርነቶች፡ የርዳታ ድርጅቶች ላይ ብርቱ ፈተና መደቀናቸው

September 19, 2024 – DW Amharic  ኢትዮጵያ ውስጥ ግጭት ባለባቸው አከባቢዎች የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦቶችን ማከናወን ፈታኝ እንደሆነበት የዓለማቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) ዐሳወቀ፡፡ ኢትዮጵያ ጦር መሣሪያ ላላነገቡ ሰላማዊ ሰዎች የርዳታ ተደራሽነት ብርቱ ፈተና ውስጥ ከሚገኙባቸው አከባቢዎች አንዱ መሆኑኗም ተገልጧል ።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

ጎንደር ከትናንቱ ውጊያ ማግስት

September 19, 2024 – DW Amharic  ትናንትና በመከላከያ እና ፋኖ መካከል ውጊያ ሲካሄድባት ነበር የተባለችው የጎንደር ከተማ ዛሬ የተኩስ ድምፅ እንደማይሰማባት ተገለጠ ። ሆኖም መደበኛ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ወደ ቀድሞው ሁኔታቸው እንዳልተመለሱ ነዋሪዎች ተናግረዋል ።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

«ሰዎች በርሐብ እየሞቱ ነው»የተፈናቃዮች አቤቱታ

September 19, 2024 – DW Amharic  በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የሚገኙ ነዋዎች ለከፋ የምግብ እህል እጥረት መጋለጣቸውን ዐሳወቁ ። መንግስት የአቅርቦት ችግር እንዳለበት አመልክቷል ። ሰዎች በርሐብ እየሞቱ ነው፣ ለልመናም የወጡ ተፈናቃዮች እንዳሉም ተነግሯል፡፡… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የደብረፅዮን ቡድን መፈንቅለ መንግስት ሊያደርግብኝ ነው ሲል የአቶ ጌታቸው ረዳ ቡድን አስታወቀ

September 19, 2024 – Konjit Sitotaw  የደብረፅዮን ቡድን ለስልጣኑ ሲል የትግራይ ህዝብ ላይ ተደጋጋሚ ክህደት እየፈፀመ ይገኛል ሲል የጌታቸው ረዳ ቡድን ባወጡት መግለጫ ገልጸዋል። አባላቱ አክለውም የትግራይ ህዝብ ላይ የተፈፀመውን ጄኖሳይድ ለስልጣኑ ሲል ወደ መካድ ደርሷል ሲል ከሰዋል። የጌታቸው ቡድን መግለጫው የደብረፅዮን(ዶ/ር) ቡድን ማንኛውም አካል ላይ ውሳኔ የማሳለፍ ሆነ እርምጃ የመውሰድ ፖለቲካዊ፣ ሞራላዊ እና ህጋዊ ስልጣን እንደሌለው […]

በአማራ ክልል 5 ነጥብ 5 ሚሊዮን ተማሪዎች ለዘንድሮው የትምህርት ዘመን አልተመዘገቡም

Bywazemaradio  Sep 19, 2024 ዋዜማ- በአማራ ክልል ለ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ይመዘገባሉ ተብሎ ከታቀደው 7 ሚሊዮን ተማሪዎች ውስጥ እስካሁን የተመዘገቡት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ተማሪዎች ብቻ ናቸው።  ክልሉ የ2017 የትምህርት ዘመንን መስከረም 7 ቀን አስጀምሯል። ሆኖም ለዘንድሮው የትምህርት ዘመን እስካሁን የተመዘገቡት 21 በመቶ ገደማ ያህሉ ብቻ መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል። ዋዜማ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች […]