ትዊተር በኢላን ከተገዛ በኋላ ከማስታወቂያ የሚያገኘው ገቢ በግማሽ ቀነሰ
ከ 4 ሰአት በፊት ትዊተር የተሰኘውን ማሕበራዊ ሚድያ ባለፈው ጥቅምት ኢላን መስክ ንብረቱ ካደረገው በኋላ ከማስታወቂያ የሚገኘው ገቢ በግማሽ መቀነሱን ባለቤቱ ገለጠ። ትዊተር ባለፈው ሰኔ ምንም ዓይነት የሽያጭ ጭማሪ አላሳየም በያዝነው ሐምሌ ግን “ይሻላል” ብሏል። ኢላን መስክ ባለፈው ዓመት ትዊተርን ሲሸምት ከነበሩት 7500 ሠራተኞች መካከል ግማሹን ማባረሩ አይዘነጋም። በቅርቡ ይፋ የሆነው ትሬድስ የተባለው የትዊተር ተቀናቃኝ […]
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን 9 ኤጲስ ቆጶሳትን ስትሾም፣ የትግራይ አባቶች 10 መረጡ
16 ሀምሌ 2023 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳን ስትሾም በተመሳሳይ ቀን በትግራይ አስር ኤጲስ ቆጶሳት መመረጣቸው ተገለጸ። ቤተክርስቲያኗ የሾመቻቸው አባቶች በቅርቡ ቅዱስ ሲኖዶሱ የመረጣቸው ዘጠኝ የአህጉረ ስብከት ቆሞሳትን ሲሆን፣ ሥነ ሥርዓት መሠረት ሐምሌ 09/2015 ዓ.ም. ተካሂዷል። የዘጠኙ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት በፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ መሪነት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተከናውኗል። […]
ከምዕራባውያን ጋር ፍጥጫ ውስጥ ያለችው ኢራን ከአፍሪካ ጋር ያላት ግንኙነትን በአራት ነጥቦች
16 ሀምሌ 2023 የአፍሪካ እና ኢራን ወዳጅነት አንዴ ጠበቅ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሲላላ አሁን ካለበት ደረጃ ደርሷል። የአፍሪካ እና የባሕረ ሰላጤዋ አገር ግንኙነት ከፖለቲካ እስከ ሃይማኖት፤ ከኪነ ጥበብ እስከ ምጣኔ ሃብት የተገነባ ቢሆንም ግንኙነታቸው ግን ሁሌም ውስብስብ ነው። ፖለቲካ የኢራን እና አፍሪካ ፖለቲካዊ ግንኙነት ለበርካታ አስርት ዓመታት ሲገነባ ቆይቷል። በቀዝቃዛው የዓለም ጦርነት ወቅት በ1970ዎቹ የኢራን […]
የቫግነር ቅጥረኛ ቡድን ተዋጊዎች በከፍተኛ ቁጥር ቤላሩስ መግባታቸውን ዩክሬን ገለጸች
16 ሀምሌ 2023 የዩክሬን ድንበር ጥበቃ አገልግሎት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የቫግነር ቅጠረኛ ቡድን አባላት ከሩስያ ወደ ቤላሩስ መግባታቸውን ገለፁ። የድንበር ጥበቃ ዘቡ አሁን ላይ ምን ያክለ የቫግነር ቡድን አባላት ወደ ቤላሩስ እንደተሻገሩ፣ መገኛቸው እና ለምን ወደ ጎረቤት አገር ቤላሩስ መሄድ እንዳስፈላጋቸው እያጣራሁ ነው ብሏል። አንድ ያልተረጋገጠ ሪፖርት በ60 መኪኖች የተጫኑ የቡድኑ ተዋጊ አባላት ቅዳሜ ጠዋት […]
ሙቀቱ ከ40 ዲግሪ በላይ ይደርሳል በተባለባት አውሮፓ ነዋሪዎች ለፀሐይ እንዳይጋለጡ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው
16 ሀምሌ 2023 በደቡብ አውሮፓ አገራት የተመዘገበው ከፍተኛ ሙቀት በቀጣይ ሳምንትም እንደሚኖር ማስጠንቀቂያ ተሰጠ። ጣልያን፣ ስፔን እና ግሪክ ባለፉት በርካታ ቀናት ከፍተኛ ሙቀት ከተመዘገበባቸው አገራት መካከል ተጠቃሽ ናቸው። የጣሊያ ጤና ሚኒስቴር በቀጣይ ቀናት ሮም፣ ቦሎኛ እና ፍሎረንስን ጨምሮ በ16 ከተሞች ከፍተኛ ሙቀት ይኖራል የሚል ማስጠንቀቂያ አውጥቷል። ሙቀቱ በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚኖር የተተነበየ ሲሆን በጣሊያኗ ሳርዲኒያ ከተማ […]
እናት እና አራት ልጆቿን ጨምሮ 13 ሰዎች የሞቱበት የትራፊክ አደጋ በሰሜን ሸዋ
ከ 1 ሰአት በፊት ከአዲስ አበባ በስተሰሜን በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ውስጥ በደረሰ የትራፊክ አደጋ አንዲት እና አራት ልጆቿን ጨምሮ 13 ሰዎች ሞቱ። እሁድ ሐምሌ 9/2015 ዓ.ም. ንጋት ላይ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደገም ወረዳ ወረቢ ተብላ በምትጠራ ስፍራ ነው ይህ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ የደረሰው። ለአስራ ሦስት ሰዎች ህልፈት ለሆነው ለዚህ የትራፊክ አደጋ ምክንያቱ […]
በቻይና የወጣቶች የሥራ አጥነት ቁጥር እያሻቀበ ነው ተባለ
ከ 27 ደቂቃዎች በፊት ቻይና ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ በምጣኔ ሃብት ለማገገም እየጣረች ባለችበት ወቅት ከፍተኛ የወጣቶች የሥራ አጥነት ቁጥር መጨመር ገጥሟታል ተባለ። የመንግሥት መረጃ እንደሚያሳየው ከ16 እስከ 24 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል የሚገኙ ወጣቶች የሥራ አጥነት ቁጥር ባለፈው ወር በ21.3 በመቶ ከፍ ብሏል። የዓለም ሁለተኛዋ ግዙፍ ኢኮኖሚ የሆነችው ቻይና እስከ ሰኔ መጨረሻ ድረስ ባሉት ሦስት […]
የቫግነር ተዋጊዎች ወደ መካከለኛ አፍሪካ ሪፐብሊክ መግባታቸው ተገለጸ
ከ 37 ደቂቃዎች በፊት በመቶዎች የሚቆጠሩ የሩሲያው ቫግነር ቅጠረኛ ቡደን ተዋጊዎች ወደ መካከለኛ አፍሪካ ሪፐብሊክ መግባታቸው ተሰማ። ከቫግነር ጋር ግንኙነት ያለው መልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቡድኑ ተዋጊዎች ትናንት ዕሁድ ወደ መካከለኛ አፍሪካ ሪፐብሊክ መግባታቸውን ገልጿል። የቡድኑ አባላት በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ በሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ የጥበቃ አገልግሎት ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሕዝበ ውሳኔው ሥልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝዳንት […]
በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ችግኝ ለመትከል ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል
ከ 4 ሰአት በፊት ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም. ከንጋት ጀምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ችግኝ ለመትከል ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። የአገሪቱ ባለስልጣናት ዛሬ ለ12 ሰዓታት በሚቆየው ዘመቻ ግማሽ ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል እቅድ ተይዟል ይላሉ። የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ንጋት በሰጠው መግለጫ በአንድ ጀምበር 500 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል ሁነት ከማለዳው 12 ሠዓት ጀምሮ በመላ […]
የኢራን የሞራል ፖሊስ ሂጃብ በማይለብሱ ሴቶች ላይ ቁጥጥር ማድረግ መልሶ ሊጀምር ነው
ከ 3 ሰአት በፊት የኢራን ፖሊስ ከአሁን በፊት አቁሞት የነበረውን በሴቶች ላይ የሚያደርገውን የሂጃብ አለባበስ ቁጥጥር እንደገና ሊጀምር መሆኑን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ። እሁድ የአገሪቱ መንግሥት ቃል አቀባይ በሰጡት መግለጫ መሠረት ሴቶች ፀጉራቸውን የሚሸፍን ሂጃብ ማድረጋቸውን ለመቆጣጠር “የሥነ ምግባር ፖሊሶች” እንደገና ወደ ጎዳናዎች ይሰማራሉ ብለዋል። ይህ የሆነው አንዲት ወጣት ሂጃብ አልለበስችም በሚል በፖሊስ እስራት ላይ […]