‘ረሃብ በረታብን’ – ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በልመና ያጨናነቋት የጂቡቲ ከተማ
ከ 6 ሰአት በፊት “እንዴት ናችሁ?”. . . . . . “Akkam jirtu?” በጎናችን እያለፉ ለነበሩት ስደተኞች ያቀረብነው ሰላምታ ነበር። በጂቡቲ በረሃ በየጥጋ ጥጉ ተስፋ ቆርጠው ለተቀመጡ እና ነገ የሚያመጣውን ለማይገምቱ፣ ቀጣዩ ምግባቸውን ማን እንደሚመጸውታቸው ለማያውቁ ኢትዮጵያውያን ይህ ሰላምታ ያልጠበቁት ነበር። በቀይ ባሕር ዳርቻዋ የጂቡቲ ከተማ ኦቦክ ነው የምንገኘው። ይህቺ ከተማ የመንን አሻግረው ለሚያልሙ ኢትዮጵያውያን […]
እስራኤል ተኩሳ የገደለቻቸው ታጋቾች እርዳታ የሚማጸኑ ጽሁፎች በጨርቅ ላይ አስፍረው ነበር ተባለ
ከ 5 ሰአት በፊት የእስራኤል መከላከያ ተኩሶ የገደላቸው እስራኤላዊ ታጋቾች እርዳታን የሚማጸኑ ጽሁፎች በጨርቅ ላይ ጽፈው ነው ተባለ። ጽሁፎቹንም ለማስፈር የተራረፈ ምግብ መጠቀማቸውን የእስራኤል ጦር አስታውቋል። አርብ እለት የተገደሉት ሶስቱ እስራኤላዊ ታጋቾች በነጭ ጨርቅ ላይ እርዳታን የሚጠይቅ ጽሁፎች አስፍረው እንዲሁም እያውለበለቡ ነበር ተብሏል። ሶስቱ ታጋቾች ተተኩሰው በተገደሉበት ህንጻ ለተወሰነ ጊዜ ቆይተው ሊሆን እንደሚችል ባለስልጣናቱ ያምናሉ። […]
ከስድስት ዓመታት በፊት በሊቢያ የታገተው ደቡብ አፍሪካዊ በአል-ቃኢዳ ታጣቂዎች ነጻ ወጣ
ከ 5 ሰአት በፊት ከአል- ቃኢዳ ጋር ግንኙነት ያላቸው እስላማዊ ታጣቂዎች ከስድስት ዓመታት በፊት በሊቢያ ታግቶ የነበረውን ደቡብ አፍሪካዊ የድንገተኛ አደጋ የህክምና ባለሙያ ማስፈታታቸውን አንድ ግብረ ሰናይ ድርጅት አስታወቀ። ጊፍት ኦፍ ዘ ጊቨርስ የተሰኘው ግብረ ሰናይ ድርጅት ለረዥም ጊዜ ታግቶ ቆይቷል ያለውን፤ ታጋቹን ጌርኮ ቫን ዴቨንተር “ያለ ቅድመ ሁኔታ” እንዲለቀቅ ማመቻቸቱን አስታውቋል። እ.ኤ.አ. በ 2017 […]
አየር ማረፊያ ተውጦ፤ አዞዎች ከተማ መሐል የታዩበት የአውስትራሊያዋ ክዊንስላንድ ጎርፍ
ከ 5 ሰአት በፊት በታሪክ ከፍተኛው በተባለው ዝናብ ምክንያት የአውስትራሊያዋ ክዊንስላንድ ግዛት በጎርፍ ተጥለቅልቃለች። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከሥፍራው እንዲለቁ ሲደረግ በርካቶች አሁንም መንቀሳቀሻ አጥተው ተቀምጠዋል። ትሪፒካል ክሎን በተባለ የአየር ንብረት ክስተት የተከሰተው ዝናብ በአንዳንድ ሥፍራዎች ከፍተኛ ጎርፍ አስከትሏል። ከአካባቢው የሚወጡ ምስሎች በካይርንስ አየር ማረፊያ ያሉ አውሮፕላኖች በከፊል ተውጠው፤ መሐል ከተማ አዞዎች ሲዋኙ እና ነዋሪዎች በታንኳ […]
አብይ አህመድ የተዘፈቀበትን ቀውስ በትርዒት ጋጋታ የሚያመልጥ መስሎት በአየር ሃይል ቀን የኤሜሬትስ የአየር ትርዒት ቀርቧል። መሳይ መኮንን
December 17, 2023 መሳይ መኮንን ፦ በአየር ሃይል ቀን የኤሜሬትስ የአየር ትርዒት ቀርቧል። አብዛኛው ትዕይንት በውጭ ሀገር አየር ሃይል ትርዒት የታየበት ነው። የተወሰኑ ሄሊኮፕተሮች በሰማዩ ላይ ከመብረራቸው በቀር የታየው የኤሜሬትስ ሾው ነው። ለምን እንደዚያ ማድረግ እንዳስፈለገ ግራ የሚያጋባ ነው። ከበዓሉ አከባበር ጀምሮ መላ ቅጡ የጠፋበት ቀን ሆኖ ነው የዋለው። በመሰረቱ 88ዓመት ማክበር ለምን አስፈለገ? 10ኛ፥ 25ኛ፥ […]
‹‹የኢዜማ አባላት ባይለቁ ደስ ይለናል ነገር ግን የትግል ሥልትና የዓላማ ልዩነት ካለ ምን ማድረግ ይቻላል›› የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሙሉዓለም ተገኘወርቅ (ዶ/ር)
EthiopianReporter.com ዮሐንስ አንበርብር December 17, 2023 ቆይታ የኢትዮጵያ ፖለቲካን ከብሔር ተፅዕኖ የማላቀቅ ትልም ይዞ የፖለቲካ ምኅዳሩን የተቀላቀለው የኢትዮጵያ ዜጎች ማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)፣ ከ2015 ዓ.ም. አጋማሽ ወዲህ ባሉት ጊዜያት ውስጥ በተለየ ሁኔታ የአባላት መልቀቅ እያጋጠመው ይገኛል። የኢዜማ አባላት በተደጋጋሚና ቀላል በማይባል ቁጥር ፓርቲያቸውን ጥለው የሚወጡበት ምክንያት በአሁኑ ወቅት የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኗል። የፓርቲው አባላት የሚለቁት ለምንድነው? በፓርቲው ውስጥ ባለ ውስጣዊ ችግር ነው? የሚለውንና በኢዜማ አጠቃላይ ወቅታዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ዙሪያ የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሙሉዓለም ተገኘወርቅ (ዶ/ር) ከዮሐንስ አንበርብር ጋር ያደረጉት ቆይታ እንደሚከተለው ተጠናቅሯል፡፡ ሪፖርተር፡- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢዜማ አመራሮችን ጨምሮ የፓርቲው አባላት በከፍተኛ ቁጥር እየለቀቁ መሆኑ እየተሰማ ነው። ምንድን ነው ምክንያቱ? ይህ ጉዳይ ፓርቲያችሁ ላይ ሊፈጥር የሚችለው ችግር አይኖርም ወይም አያሳስባችሁም? ዶ/ር ሙሉዓለም፡– የተለያዩ ሚዲያዎችና የተለያዩ አባለት በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻቸው ላይ እንዲህ ዓይነት መልዕክት ሲያስተላልፉ እናያለን። ነገር ግን የኢዜማን አደረጃጀት ካለመረዳት የመነጨ ነው ብለን እናስባለን። ሪፖርተር ጋዜጣም ይህንን የአባላት መልቀቅ በተመለከተ ያወጣው የተሳሳተ ዘገባ አለ፣ መስተካከልም አለበት ብለን እናምናለን። በመሠረታዊነት የኢዜማ አደረጃጀት በምርጫ ክልል ደረጃ ነው። የፓርቲው […]
የመንግሥትና የፓርቲ መዋቅሮች ፅዳት ይሻሉ!
December 17, 2023 – EthiopianReporter.com ከትናንት እስከ ዛሬ የፖለቲካ ክስረቶቻችን ማሳያዎች ብዙ ናቸው፡፡ የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆነ የፖለቲከኞች መስተጋብር በመርህ ላይ ያልተመሠረተ በመሆኑ፣ ልዩነትን ማስተናገጃ በርካታ አዎንታዊ አማራጮች እያሉ አሉታዊ ነገሮች ላይ ማተኮር ይበዛል፡፡ የብዙዎቹ የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጣዊ ግንኙነት በዴሞክራሲ ዓምዶች ላይ ያልተመሠረተ ስለሆነ፣ አለመግባባት ሲያጋጥም በስክነት ጊዜ ወስዶ ከመነጋገር ይልቅ ትርምስ መፍጠር የተለመደ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ኢትዮጵያ […]
ወርቅ – የግለሰቦችና የታጣቂ ቡድኖች ሀብት?
December 17, 2023 – EthiopianReporter.com ከቡና ቀጥሎ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ትልቁን የውጭ ምንዛሪ ገቢ ከሚያስገኙት የኤክስፖርት (ወጪ ንግድ) ምርቶች መካከል አንዱ የወርቅ ማዕድን ነው። ይህ የወርቅ ሀብት አጠቃላይ ኢኮኖሚው በከፍተኛ ደረጃ በውጭ ምንዛሪ እጥረት በተመታበት በአሁኑ ወቅት ለኢኮኖሚው ምርኩዝ መሆን አልቻለም። ኢትዮጵያ ከፍተኛና ጠቃሚ የውጭ ምንዛሪ ገቢ ልታገኝ የምትችልበት ይህ የወርቅ ሀብቷ፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከእጇ እያመለጣትና ከኤክስፖርት […]
የማስታወቂያ ሰሌዳዎች በዲጂታል ስክሪኖች ሲተኩ የአፈጻጸም ችግር ማጋጠሙ ተገለጸ
EthiopianReporter.com በሰላማዊት መንገሻ December 17, 2023 በውይይት መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማስታወቂያዎችን ለማዘመን የቢልቦርድ ማስታወቂያዎች ተነስተው በዲጂታል ስክሪን እንዲተኩ ትዕዛዝ ካስተላለፈ በኋላ፣ የአፈጻጸም ችግር ማጋጠሙን፣ የኢትዮጵያ ማስታወቂያ ሥራ ማኅበር አስታወቀ፡፡ ማኅበሩ ይህንን የገለጸው ታኀሳስ 4 ቀን 2016 ዓ.ም. ባካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ሲሆን፣ በውይይት መድረኩ ላይ ከተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት የተወከሉ ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል፡፡ የቢልቦርድ […]
ከኦሮሚያ ንብረታቸውን ጥለው የተፈናቀሉ ዜጎች ተገቢውን ካሳ ለመጠየቅ እየተመዘገቡ መሆኑ ተገለጸ
EthiopianReporter.com ማኅበራዊ ከኦሮሚያ ንብረታቸውን ጥለው የተፈናቀሉ ዜጎች ተገቢውን ካሳ ለመጠየቅ እየተመዘገቡ መሆኑ ተገለጸ አበበ ፍቅር ቀን: December 17, 2023 ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው በአማራ ክልል ደብረ ብርሃን ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች፣ ይኖሩበት ከነበረው አካባቢ ጥለውት የመጡትን ንብረት የመመዝገብና መረጃን የማሰባሰብ ሥራን እየሠራ መሆኑን የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡ የጠፋባቸውን ንብረት ለማወቅና ንብረታቸው ካልተገኘ ተገቢውን ካሳ ለመጠየቅ ተፈናቃዮች […]