በአብይ አገዛዝ 50 የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ላልተገባ እስር መዳረጋቸው ታወቀ

December 11, 2023 – Konjit Sitotaw  በመገባደድ ላይ ባለው የፈረንጆቹ 2023 ዓመት ብቻ 50 የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች “ላልተገባ እስር መዳረጋቸውን” የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል አስታወቀ። ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑት አሁንም በእስር ላይ የሚገኙ እንዳሉበት የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ኃይለ ማርያም ተናግረዋል። አቶ ያሬድ ይህን ያሉት “በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶችን ለማስጠበቅ ያሉ ወቅታዊ ተግዳሮቶች እና የመፍትሔ አማራጮችን” በተመለከተ፤ […]

“በቤተ ክርስቲያኗ እና በምዕመኖቿ ላይ የሚፈጸመው በምድርም ሆነ በሰማይ የሚያስጠይቅ ነው” ፡ ሲኖዶስ

11 ታህሳስ 2023, 17:35 EAT የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በአገልግጋዮች፣ በምዕመናን እና በአብያተ ክርስቲያናት ላይ እየተፈጸመ ያለው ድርጊት በምድርም በሰማይም የሚያስጠይቅ ነው አለ። ሲኖዶሱ ዛሬ ሰኞ ታኅሣሥ 01/2016 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ ላይ በቅርቡ በተለያዩ ስፍራዎች በምዕመናን እና በቤተክርስቲያኗ አባቶች ላይ በተፈጸሙ ጥቃቶች ከ60 በላይ ሰዎች መገደላቸውን በዝርዝር አመልክቷል። “ግድያና፣ […]

በአጣዬ ከተማ ከትላንት ረፋድ ጀምሮ በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ የሰዎች ሕይወት አለፈ

11 ታህሳስ 2023, 16:32 EAT በአማራ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ አጣዬ ከተማ ከትናንት እሁድ ረፋድ ጀምሮ በመከላከያ ሠራዊት እና በታጣዊዎች መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ የሰው ሕይወት ማለፉን ነዋሪዎች ተናገሩ። እሁድ ኅዳር 30/2016 ዓ. ም. የመከላከያ ሠራዊት ከፋኖ እና መንግሥት “ሸኔ” ከሚላቸው ታጣቂዎች ጋር በአካባቢው የተኩስ ለውውጥ ማድረጉን አራት የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ […]

“ልንበላው የዘራነውን እህል አፈር በላው፤ በረሃብ ልንሞት ነው” የትግራይ አርሶ አደሮች

11 ታህሳስ 2023, 12:50 EAT የአሁኑን አያደርገው እና በትግራይ ክልል ምሥራቃዊ ዞን የሚገኘው የአጽበደራ ወረዳ ቀድሞ እህል የተትረፈረፈበት፣ እንስሳት በስፋት የሚታዩበት ለም አካባቢ ነበር። ስንዴ እና በቆሎ በብዛት የሚበቅልበት ይህ አካባቢ በማር ምርቱም ታዋቂ ነበር። አሁን መሬቱ ጦም ካደረ ሰነባበተ። ለሁለት ዓመት የዘለቀውን ደም አፋሳሽ ጦርነት ማክተሙን ተከትሎ አርሶ አደሮች ወደ እርሻቸው ቢመለሱም በድርቅ ምክንያት […]

የታንዛኒያ ምክትል ፕሬዝዳንት ሞተዋል የሚል ወሬ ያሰራጩ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ምርመራ ሊደረግባቸው ነው

11 ታህሳስ 2023, 15:14 EAT ስለ ታንዛኒያ ምክንትል ፕሬዝዳንት ፊሊፕ ምፓንጎ የጤና ሁኔታ ሐሰተኛ መረጃ በማሰራጨት የተጠረጠሩ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ላይ በአገሪቱ መሪዎች ምርመራ እየተደረገ እንደሆነ ተገለጸ። ምክትል ፕሬዝዳንቱ ከአንድ ወር በላይ በሕዝብ አደባባይ ሳይታዩ ከቀሩ በኋላ ትላንት በይፋ ታይተዋል። በይፋ መታየታቸው በርካቶችን እፎይታ ሰጥቷል። ሞተዋል የሚል ጭምጭምታ ተሰምቶ ነበር። የማስታወቂያ ሚኒስትር የሆኑት ኔፕ ናኙይ […]

ኢትዮጵያዊው ሙላቱ ለማ (ፕ/ር) በዓለም አቀፉ ከፍተኛ ባለሙያዎች ማህበር የ2023 ምርጥ ፕሮፌሰር በመሆን ተመረጡ።

December 11, 2023 – Konjit Sitotaw  በጆርጂያ ሳቫና ግዛት ዩኒቨርሲቲ የሂሳብ መምህር የሆኑት ኢትዮጵያዊው ሙላቱ ለማ (ፕ/ር) የ2023 ምርጥ ፕሮፌሰር በመሆን ተመረጡ። ሙላቱ ለማ (ፕ/ር) በዘርፍ የተመረጡት በዓለም አቀፉ ከፍተኛ ባለሙያዎች ማህበር መሆኑን የአሜሪካ ኤምባሲ አስታውቋል። ማህበሩ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሙያዊ ስኬት፣ በአካዳሚክ ውጤት፣ በአመራር ችሎታ፣ በመስኩ ረጅም ጊዜ በማገልገል እና ለማህበረሰብ ባደረጉት አስተዋፅዖ በመመርኮዝ ለባለሙያዎች እውቅና […]

የሱዳን ተዋጊ ኃይሎች ያለቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም ለማድረግ ተስማሙ

ከ 3 ሰአት በፊት በሱዳን እየተፋለሙ ያሉት ኃይሎች የተኩስ አቁም ስምምነቱን እንደሚያከብሩ መስማማታቸውን ኢጋድ ገለጸ። የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (IGAD) እሑድ እንዳስታወቀው እዚህ ስምምነት ላይ የተደረሰው በጂቡቲ በተደረገ የአባላት አገራት ስብሰባ ነው። ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን የሚመሩት ኃይል የፈጥኖ ደራሽ ኃይልን ካለፈው ዓመት ታኅሣሥ ጀምሮ ሲፋለም ቆይቷል። በዚህ ጂቡቲ በተደረገው ጉባኤ አብዱልፈታህ አልቡርሃን ተገኝተዋል። የኢጋድ […]

የጋዛ ተኩስ አቁም ስምምነት ተስፋው እየተመናመነ ነው- ኳታር

ከ 4 ሰአት በፊት እስራኤል በጋዛ ላይ አጠናክራ የቀጠለችው የማያባራ የቦምብ ጥቃት የተኩስ አቁም ስምምነት ዕድሉን እያጠበበው ነው ሲሉ የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ። ሼክ መሀመድ ቢን አብዱልራህማን አል ታኒ በዶሃ ጉባኤ ላይ እንደተናገሩት ኳታር ሁለቱ ወገኖች የተኩስ አቁም እንዲያደርጉ ግፊት ማድረጓን ትቀጥላለች። ኳታር በሁለቱ ወገኖች ዘንድ ለአንድ ሳምንት የቆየ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ቁልፍ […]

ፊቱ የማይታየው እና በእስራኤል ከሚፈለጉት አንዱ የሆነው የሐማስ አፈ ቀላጤ – አቡ ኡቤይዳ

ከ 6 ሰአት በፊት የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ የሆነው የአል-ቃሳም ብርጌድ ቃል አቀባይ በእስራኤል-ጋዛ ጦርነት ጎልተው ከወጡት መካከል አንዱ ነው። “አቡ ኡቤይዳ” በመባል የሚታወቀው ግለሰብ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የቡድኑን መልዕክት በበይነ መረብ ሲያሰራጭ ደጋግሞ ይታያል። ቅጽል ስሙን ያገኘው ከቀደምት የሙስሊም የጦር አዛዦች አንዱ ከሆነው ከአቡ ኡቤይዳ ኢብን አል-ጃራህ ነው። ሐማስ በደቡባዊ እስራኤል ላይ መስከረም ወር መጨረሻ […]

ከዩኬ ጎን ተሰልፈው ታሊባንን የተዋጉ የአፍጋኒስታን ልዩ ኃይል ወታደሮች ‘ተክደናል’ አሉ

ከ 5 ሰአት በፊት በቁጥር 200 የሚሆኑና ከዩኬ ጎን ተሰልፈው ታሊባንን ሲፋለሙ የነበሩ የአፍጋኒስታን ልዩ ኃይል ወታደሮች ‘ዩኬ ክህደት ፈጸመችብን’ ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ። እነዚህ ወታደሮች ታሊባን መልሶ አፍጋኒስታንን ሲቆጣጠር በዩኬ ጥገኝነት ለማግኘት ከሁለተኛ አገር ሆነው ሲጠባበቁ የነበሩ ቢሆንም ማመልከቻቸው ውድቅ ተደርጎባቸዋል። የቀድሞ የዩኬ ጄኔራልና በአፍጋኒስታን ለ12 ዓመት የገለገሉት ሰር ሲቻርድ ባሮንስ ድርጊቱን ‘’የለየለት ክህደት’’ ሲሉ […]