የሩሲያን ድንበር ጥሰው የገቡት ሽምቅ ተዋጊዎች ተመሳሳይ ጥቃት እንደሚፈጽሙ ዛቱ

ከ 4 ሰአት በፊት ባሳለፍነው ሰኞ የሩሲያን ድንበር ሰብረው እንደገቡ የተነገረላቸው ሽምቅ ተዋጊዎች ተመሳሳይ እርምጃ እንፈጽማለን ሲሉ ዛቱ። ከነዚህ ሸማቂ ቡድኖች አንዱ የሆነው የሩሲያ ወዶ ዘማቾች ቡድን መሪ ዴኒስ ካፑስቲን በዩክሬን መሬት ላይ ሆኖ እንደተናገረው ‘በቅርቡ በሩሲያ በኩል ገብተን የምታዩን ይመስለኛል’ ሲል እሱ የሚመራው የአርዲኬ (RDK) ቡድን ለሌላ ዙር ጥቃት መሰናዳቱን ጠቁሟል። ይህ ቡድን የሩሲያን […]

ቻይና የኬንያ የመንግሥት ተቋማት ላይ የመረጃ መረብ ጥቃት አድርሳለች መባሏን አስተባበለች

ከ 3 ሰአት በፊት የቻይና የኢንተርኔት መረጃ መንታፊዎች በኬንያ ቁልፍ የሚባሉ የመንግሥት ተቋማት ላይ የመረጃ መረብ ጥቃት አድርሰዋል መባሉን ቻይና አስተባበለች። በዚህ የመረጃ መረብ ጥቃት የፕሬዚዳንቱን ቢሮ ጨምሮ ሌሎች ቁልፍ የመንግሥት ተቋማት ኢላማ ተደርገዋል። ጥቃቱ ያነጣጠረው ኬንያ ከቻይና የተበደረችውን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላሮችን ለመክፈል ያስችል ለመገምገም እንደሆነም ሮይተርስ የዜና ወኪል የዘገበ ሲሆን በኬንያ የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ […]

ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ የዋሽንግተን ቡድን አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋራ ጥላቻ ውስጥ እንድትገባ ሠርተዋል ሲሉ ከሠሡ

May 25, 2023 – Konjit Sitotaw  የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈ ወርቂ፣ “የዋሽንግተን ዲሲ ቡድን” ሲሉ በጠሩት አካል ላይ ክሥ አሰሙ። ፕሬዚዳንቱ ወቀሳውን ያሰሙት፣ ዛሬ በተከበረው 32ኛ ዓመት “የነፃነት በዓል” ላይ ነው። ፕሬዚዳንቱ፣ የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር፣ በኤርትራ እና በሌሎች ሀገራት ላይ ያካሒደዋል ያሉት ፖሊሲ፣ “ለትውልድ የዘለቀ ጠበኛነትን አትርፏል፤” ሲሉ ከሠዋል፡፡ ዝርዝሩን ከዚህ ያገኙታል https://minilik-salsawi.blogspot.com/2023/05/eritrea-president-accused-washington.html

የሸገር ከተማ አስተዳደር በሚያፈናቅላቸው ዜጎች ዙሪያ ከሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ጋር ያደረገላቸውን ውይይቶች ካደ

May 25, 2023 – VOA Amharic የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ በሸገር ከተማ “ሕገ ወጥ ግንባታ” በሚል እየተካሔደ ካለው የቤቶች ፈረሳ ጋራ የተያያዙ፣ 100ሺሕ አቤቱታዎች እንደቀረቡለት ሲናገር፣ የሸገር ከተማ አስተዳደር ደግሞ ይህን ያህል ቅሬታ እንዳልቀረበለት ገልጿል። የሸገር ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጉግሳ ደጀኔ፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ “100ሺሕ አቤቱታዎች” የሚለው መረጃ፣ ውይይት ያልተደረገበት፣ በአግባቡ ያልተጣራና ከአንድ ወገን […]

የዐዲስ አበባ ዙሪያ ተፈናቃዮች “አድልዎ የተሞላበትና ማንነትን የለየ” ያሉትን ቤት ፈረሳ አማረሩ

May 25, 2023 በዐዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ፣ ለዓመታት ጎጆ ቀልሰው ከኖሩበት ቤታቸው፣ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር፣ “ሕገ ወጥ ናችኹ፤” በሚል እንደተፈናቀሉ፣ ቤታቸው ፈርሶ እና ንብረታቸው ተበትኖ ባዷቸውን መቅረታቸውን ነዋሪዎች አማረሩ። በአካባቢው ይኖሩ ከነበሩ ሰዎች፣ በሕጋዊ ውል የገዟቸውን ቤቶች ጨምሮ፣ የአካባቢው አስተዳደር በሚያውቀው ኹኔታ የገነቧቸው ቤቶች፣ በግብረ ኃይል እንዲፈርሱ በመደረጋቸው ለችግር መጋለጣቸውንም፣ ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። የማፍረሱ […]

በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትህና ፍኖተ ካርታ ላይ ውይይት ይካሄዳል ተባለ

May 25, 2023 – DW Amharic በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትህና ቀጣይ የሽግግር ፍኖተ ካርታ መከናወን ያለባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ለማካሄድ በዝግጅት ላይ መሆኑን የኢትዮጵያውያን ሕዝባዊ ማኀበራት ጉባዔ አስታወቀ።በቅርቡ የተቋቋመው የኢትዮጵውያን ህዝባዊ ማኀበራት ጉባኤ፣ (ኢሕማጉ) በውጭ የሚገኙ 11 የኢትዮጵያውያን ሕዝባዊ ማኀበራትና ስብስቦችን ያቀፈ ነው።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የሕገመንግሥት ጉዳይ ጥናት ያስከተለው ውዝግብ

May 25, 2023 – DW Amharic  የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ሕገመንግሥቱን አስመልክቶ ባለፈው ሳምንት ይፋ ያደረገውን ጥናት 16 የፖለቲካ ድርጅቶችን የተካተቱበት የተቃዋሚ ፖለቲካ ስብስብ አጣጥሎ ነቅፎታል ። ሕገመንግሥቱ አይነካብን የሚሉ እንዳሉ ሁሉ እንደውም ሙሉ በሙሉ ተቀዶ መጣል አለበት የሚሉም አሉ ። ከሁለቱም በተለየ መሻሻል አለበት የሚሉም ይታያሉ ።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የአውሮጳ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉባኤ

May 25, 2023 – DW Amharic  ብራስልስ ውስጥ የ27ቱ ያአውሮጳ ኅብረት አባል አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ሰኞ ግንቦት 14 ቀን፤ 2015 ዓ.ም ባደረጉት ስብሰባ በአፍሪቃ ቀንድ የኢትዮጵያ፤ ሱዳን እና ሶማሊያ ጉዳይ ትኩረት ሰጥተዋል ። ዩክሬን እና ሩስያ ጉዳይ ላይም ተወያይተዋል ።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን የሰላም ጥሪ

May 25, 2023 – DW Amharic  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ሁሉም ዜጋ በሀገሩ በእኩልነት፣ በሰላምና በፍቅር ተከባብሮ በአንድነት እንዲኖር ግጭቶችና አለመግባባቶች በውይይት እንዲፈቱ የሰላም ጥሪ አስተላለፈች ። የቤተ ክርስትያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ከግንቦት 1 ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 16 ቀን፣ 2015 ዓ. ም ምልዐተ ጉባኤውን ሲያደርግ ሰንብቷል ።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

መንግሥት የበጀት ጉድለት ለመሸፈን በዘጠኝ ወራት 194.6 ቢሊዮን ብር ከአገር ውስጥ ተበድሯል

May 25, 2023 – DW Amharic  የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ባለፈው ሳምንት ባቀረቡት ሪፖርት የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት 28 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ኪሳራ ማድረሱን ይፋ አድርገዋል። “ግጭት እና ጦርነት በነበረባቸው አካባቢዎች ሦስት ሚሊዮን ዜጎች ወደ ከፋ ድህነት” ገብተዋል። የበጀት ጉድለትና ያለቅጥ የሚሰፋው የክልሎች መዋቅር ያስከተለው ጫና በሪፖርቱ ከተካተቱ መካከል ናቸው… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ