መንግስት 15 ቀን ሳይሞላው ለቤተክርስቲያን መልስ ሰጠ

March 8, 2023  አጠራጣሪው እና ታማኝነት የጎደለው የመንግስት መልስ የአድዋ በአል እለት የተጠቀመውን ከልክ ያለፈ የሃይል እርምጃ ለመካድ የተሰጠ መግለጫ ነው ተብሏል። የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በአድዋ ክብረ በአል ላይ ቤተክርስቲያን ውስጥ የመንግስት ፖሊሶች አስለቃሽ ጭስ በመወርወር ሲያመልክ የነበረውን ሰላማዊ ሕዝብ መረበሻቸው አንድ ሰውም በጥይት መግደላቸው ይታወቃል። ቤተክርስቲያን ይህን ተከትላ ቁጣዋን በማሰማት በ15 ቀን ውስጥ መልስ እንዲሰጣት በጠየቀችው መሰረት መንግስት መልስ […]

ኢሰመጉ ኢትዮጵያ ሴቶችን እኩልነትን ከቃል ባለፈ በተግባር የምትቀበል እና የምታሳይ አገር እንድትሆን ጥሪ አቀረበ

March 8, 2023  ኢትዮጵያ ሴቶችን እኩልነትን ከቃል ባለፈ በተግባር የምትቀበል እና የምታሳይ አገር እንድትሆን፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ጥሪ አቀረበ። ኢሰመጉ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ ዛሬ ለአዲስ ማለዳ በላከው መግለጫ፣ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በአውሮፓ እና በአሜሪካ በሚገኙ አገራት በነበሩ የሴቶች እንቅስቃሴዎች እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1911 ጀምሮ በዓለም አቀፍ ሁኔታ ሲከበር የቆየ በዓል […]

21 ኢትዮጵያዊያን በኬንያ የረሀብ አድማ ላይ መሆናቸው ተሰማ

March 8, 2023 ኬንያ ውስጥ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የሚገኙ 21 ኢትዮጵያዊያን ከሐሙስ የካቲት 23/2015 ጀምሮ በረሀብ አድማ ላይ እንደሆኑ ተነግሯል፡፡ ታሳሪዎቹ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ በፍርድ ቤት የተወሰነላቸው ቢሆንም የውሳኔው ተግባራዊነት ዘግይቷል በማለት የረሀብ አድማውን መጀመራቸው የተሰማ ሲሆን፣ በዚህ የተነሳም የኬንያ ፖሊስ ድንጋጤ ላይ መውደቁ ተሰምቷል፡፡ የካቲት 10/2015 ጁጃ ኪያምቡ በሚባል አካባቢ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር […]

አዲስ አበባ ሸገር ሲቲ ተብሎ በተሰየመው በተለምዶ ሃያ ሁለት ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የቤቶች ፈረሳ እንደቀጠለነው ተባለ።

March 8, 2023  ዛሬ የካቲት 29/2015 ዓ/ም ከማለዳው ጀምሮ በተካሄደው የቤቶች ፈረሳ ከ400 በላይ ቤቶች መፍረሳቸውን የአሻራ ምጮች ገልፀዋል። የአማራ ተወላጆችን መሰረት ያደረገው የቤቶች ፈረሳ አሁን አሁን የጉራጌ ተወላጆችንም ማካተቱን የአሻራ ምንጮች አረጋግጠዋል። በአንድ ሳምንት ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተዎላጆችን ቤት አልባ እያደረገ የሚገኘው የኦሮሙማው አገዛዝ አሁንም ድረስ ይህንኑ ግፍና በደል አጠናክሮ መቀጠሉን ምንጮች ተናግረዋል። […]

100 ሺህ ተፈናቃዮችን ወደ ኢትዮጵያ ያሰደደው የሶማሊላንድ ግጭት ምክንያቱ ምንድን ነው?

8 መጋቢት 2023, 17:13 EAT የሲያድ ባሬ አስተዳደር ተገርስሶ ሶማሊያ በእርስ በርስ ጦርነት ስትታመስ ለሦስት አስር ዓመታት ያህል የተረጋጋ ሰላም የታየባት ሶማሊላንድ በአሁኑ ወቅት በግጭት እየተናጠች ትገኛለች። በዓለም አቀፍ ደረጃ የአገርነት እውቅና ያልተሰጣት የራስ ገዝ አስተዳደሯ ሶማሊላንድ በቅርቡ በተቀሰቀሰው ግጭት 200 ዜጎቿ ሞተዋል፣ እንዲሁም ቢያንስ 100 ሺህ ዜጎቿ ተፈናቅለው ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል። ተፈናቃዮቹ በኢትዮጵያ ዶሎ […]

በዓድዋ በዓል አከባባር ላይ “ያልተገባ ተግባር” በፈጸሙ ፖሊሶች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተነገረ

8 መጋቢት 2023, 18:41 EAT የአንድ ሰው ሕይወት በጠፋበት የአዲስ አበባው የዓድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ያልተገባ ተግባር ፈጽመዋል ባላቸው የፖሊስ አባላት ላይ እርምጃ መውሰዱ ተገለጸ። በእነዚህ የፖሊስ አባላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ መወሰዱን እና ተጨማሪ የምርመራ ተግባር እየተከናወነ ስለመሆኑ የፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይልን ዋቢ አድርገው የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። 127ኛው የዓድዋ ድልን […]

ተመድ በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ተግባራዊ መሆንን እንደሚደግፍ ገለጸ

8 መጋቢት 2023, 11:15 EAT የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቮልከር ቱርክ በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ተግባራዊ እንዲሆን ኮሚሽናቸው ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለጹ። ኮሚሽነር ቮልከር ቱርክ ይህን ያሉት በ52ኛው የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ጉባኤ ላይ የተቋማቸውን እንቅስቃሴ በተመለከተ ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ነው። ኮሚሽነሩ የሽግግር ፍትሕን ጨምሮ በኢትዮጵያ ግጭት ለማቆም በፌደራል መንግሥቱ እና በህወሓት መካከል የተደረሰው […]

ኢትዮጵያ ውስጥ በሴቶች ላይ የሚፈጸመው አሰቃቂ ጥቃት ለምን ጨመረ?

8 መጋቢት 2023 አዶናይ ይሄይስ የ12ኛ ክፍል ተማሪ ነበረች። በጣም ጎበዝ ተማሪ። በአንድ ግለሰብ ተደጋጋሚ አስገድዶ መድፈር ሲፈጸምባት ነበር። መስከረም 14/2015 ዓ.ም. ደግሞ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደለች። በተለያዩ የሰውነት ክፍሎቿ ላይ በስለት ተወግታ ነው የተገደለችው። ይህን ድርጊት የፈጸመው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ውሏል። ድርጊቱን መፈጸሙን አምኗል። የአዶናይን ስቃይ ትንሽ ቀደም ብሎ ማስቆም ለምን አልተቻለም? ሰብለ ንጉሤ በማስተርስ […]

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከቀረበበት ክስ በፍርድ ቤት በነጻ ተሰናበተ

March 8, 2023 በሃሚድ አወል የ“ፍትሕ” መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፤ ከተከሰሰበት የሀሰተኛ መረጃ ማሰራጨት ወንጀል በነጻ ተሰናበተ። ጋዜጠኛው በነጻ የተሰናበተበትን ፍርድ የሰጠው፤  ዛሬ ረቡዕ የካቲት 29፤ 2015 የዋለው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የጸረ ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ችሎት ነው።  የችሎቱን ፍርድ በንባብ ያሰሙት የግራ ዳኛ “ተከሳሹ የቀረበበትን ወንጀል በመከላከሉ በነጻ […]

በሰብዓዊ መብት ጥሰት ምርመራ እና በሽግግር ወቅት ፍትሕ መካከል የቆመችው ኢትዮጵያ

March 8, 2023 – BBC Amharic  7 መጋቢት 2023 የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ተፈጽመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ለመመርመር ሦስት አባላት ያሉት ኮሚሽን ተቋቁሟል። በሰሜን ኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነት ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም ወገኖች ከጦር ወንጀል ጋር የሚስተካከሉ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ስለመፈጸማቸው ኮሚሽኑን ጨምሮ ሌሎች ድርጅቶች ባወጧቸው ሪፖርቶች አሳውቀዋል። የሠላማዊ ሰዎች ግድያ፣ አስገድዶ መድፈርን […]