የፕሬስ ነጻነት ሁኔታ በኢትዮጵያ እና ጋዜጠኞች የሚገጥሟቸው ተግዳሮቶች

May 3, 2023 – BBC Amharic  ከ 5 ሰአት በፊት ለአስርታት ኢትዮጵያ በጋዜጠኞች እስር እና በፕሬስ ነጻነት ላይ ጫናን በማሳደር ስትወቀስ ቆይታ፤ ይህ ሁኔታ ተለውጦ የታሰሩ ጋዜጠኞች ሁሉ ተፈትተው፣ በርካታ የፕሬስ ውጤቶች ወደ ገበያ ተመልሰው ነበር። ነገር ግን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን መምጣት በኋላ በፕሬስ ነጻነት በኩል የተፈጠረው ተስፋ ቀስ በቀስ ፈተና እየገጠመው መሆኑን የጋዜጠኞች […]

አሜሪካ በሰሜን ኢትዮጵያ ተጨማሪ ተቆጣጣሪዎች እንዲሰማሩ ጠየቀች

ከ 4 ሰአት በፊት አሜሪካ የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት ለማብቃት በተደረሰው ስምምነት መሠረት ውጤታማ ትጥቅ የማስፈታት እና ተያያዥ ተግባራትን ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ተቆጣጣሪዎች እንዲሰማሩ ጠየቀች። በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል ለሁለት ዓመታት የተካሄደውን ጦርነት ለማብቃት ፕሪቶሪያ ላይ የተደረሰው ስምምነትን ስድስተኛ ወር ምክንያት በማድረግ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ ሊከናወኑ የሚገቡ ተግባራትን አመልክቷል። በዚህም መሠረት […]

በአውስትራሊያ የጠፋው ዓሣ አስጋሪ በአዞ ሆድ ውስጥ ተገኘ

May 3, 2023 – BBC Amharic  ከ 3 ሰአት በፊት አውስትራሊያ ውስጥ አንድ ዓሣ አስጋሪ ከጠፋ ከቀናት በኋላ አስከሬኑ በአዞ ሆድ ውስጥ ተገኝቷል። ይህ ግለሰብ ከጓደኞቹ ጋር ዓሣ ሲያሰግር ከቆየ በኋላ ነው ጠፍቶ የነበረው። ኬቨን ዳርሞዲ የተባለው ይህ ግለሰብ ለመጨረሻ ጊዜ የታየው በኩዊንስላንድ ግዛት ባለፈው ቅዳሜ ኬኔዲስ ቤንድ የአዞዎች ማዕከል ውስጥ ነበር። በአካባቢው ለሁለት ቀናት ሙሉ ፍለጋ […]

የኦላፍ ሾልስ የኢትዮጵያና የኬንያ ጉብኝት ፋይዳ

May 3, 2023 – DW Amharic  ሁለት ዓመት የዘለቀው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ሳይታሰብ በሰላም ስምምነት ማብቃቱ የሾልስን ትኩረት የሳበ ጉዳይ መሆኑ አልቀረም። ሾልስ ወደ ኢትዮጵያና ኬንያ የሚጓዙት የጀርመን ኩባንያዎች ባለቤቶችንም አስከትለው ነው። ይህ ለኢትዮጵያ ባለወረቶችን ለመሳብ ጥሩ አጋጣሚ እንደሚሆን ይጠበቃል። ይህ የሚሳካው ኢትዮጵያ ተዘጋጅታ ስትጠብቃቸው ብቻ ነው… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

በትግራይ ክልል ትምህርት በይፋ መጀመሩ

May 3, 2023 – DW Amharic  በትግራይ ለሦስት ዓመታት ተቋርጦ የነበረው መደበኛ ትምህርት ዛሬ ዳግም ተጀምሯል ። መቐለ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ከጦርነቱ በኋላ ለመጀመርያ ግዜ ተማሪዎች ወደ መደበኛ ትምህርት እየተመለሱ ይገኛሉ ።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

ዐቢይ «ኢትዮጵያዊያን ያልሆኑ» ያሏቸው ማን ናቸው?

May 3, 2023 – DW Amharic  በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ መግባት የሚፈልጉ «ኢትዮጵያዊያን ያልሆኑ» የተባሉ ኃይሎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ትናንት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የመዝናኛ ቦታ ባስመረቁበት ወቅት ተናገረዋል ።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

ከሱዳን የ42 ሃገራት ተፈናቃዮች በኢትዮጵያ

May 3, 2023 – DW Amharic  ከሦስት ሳምንት በፊት ሱዳን ውስጥ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ሽሽት ከ6 ሺህ በላይ የሚሆኑ የ42 አገር ዜጎች ተፈናቅለው ወደ ምዕራብ ኢትዮጵያ መግባታቸው ተገለጠ ። የውጭ ሃገራት ተፈናቃዮቹ ወደሚፈለጉበት አካባቢ መሸኘታቸውንም በአማራ ክልል የምዕራብ ጎንደር ዞን ዐስታውቋል ። ከተፈናቃዮቹ መካከል 900 የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ናቸው ተብሏል ።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የሕጻናት ሀኪሞች የልምድ ልውውጥ በቦን ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል

May 2, 2023 – DW Amharic  የጨቅላ ሕጻናትና የእናቶች ሞት ምጣኔ የአንድን ሀገር የህክምና ደረጃ እንደሚያሳይ ይነገራል። በበለጸጉት ሃገራት የህክምና አገልግሎቱ ዘመኑን ተከትሎ እያደገ ከመሄዱም በላይ ለሁሉም ዜጋ ስለሚዳረስ ከህክምና ጉድለት ጋር በተገናኘ የጨቅላ ሕጻናትና ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ሞት አይሰማም። እንደኢትዮጵያ ባሉት ሃገራት ግን ትልቅ ችግር ነው።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

· በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ / National Movement of Amhara 13h   · በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ ***** የአማራ ህዝብ በተደጋጋሚ ከተከፈተበት የወረራ ጦርነት ወጥቶ አንጻራዊ መረጋጋት ካሳዬ ገና ጥቂት ወራቶች ብቻ ተቆጥረዋል። በተከፈተበት ተደጋጋሚ ወረራ ለከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት መዳረጉ ይታወቃል። የአማራ ህዝብ ግጭትና ጦርነትን በተግባር የተመለከተ እንጅ በሩቅ የሚያውቀው ጉዳይ አይደለም። የአማራ ህዝብ […]

· ከትግራዩ ጦርነት ሳንማር ሌላ ዙር በአማራ ክልል የጦር ውጥረት መግባታችን ሰሜኑን በተራ የማንበርከክ እንጂ አማራ ክልል ከወለጋ በላይ ለሃገሪቱ ስጋት ለዜጎችም የጭፍጨፋና የማፈናቀል ምክንያት ሆኖ አይደለም።

Derartu Tulu · ከትግራዩ ጦርነት ሳንማር ሌላ ዙር በአማራ ክልል የጦር ውጥረት መግባታችን ሰሜኑን በተራ የማንበርከክ እንጂ አማራ ክልል ከወለጋ በላይ ለሃገሪቱ ስጋት ለዜጎችም የጭፍጨፋና የማፈናቀል ምክንያት ሆኖ አይደለም። ሕግ ማስከበር በምዕራብም እንጂ በሰሜን አልነበረም። ባለፉት አምስት አመታት እንደ አማራና ትግራይ መከራውን ያየ ሕዝብ የለም። ተፈናቀለ ተገደለ ቤቱ ሕገወጥ በሚል ጭካኔ በላዩ ላይ ፈረሰበት። ቢያኮርፉ የተገላይነት […]