በአማራ ክልል ያለውን ግጭት በንግግር ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናገሩ

16 ነሐሴ 2023, 15:39 EAT በአማራ ክልል በመከላከያ እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተፈጠረውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ በንግግር ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት ከፍትህ ሚኒስትሩ አቶ ጌዴዮን ጢሞቲዮስ ጋር በመሆን መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ላደረጉ ዲፕሎማቶች እና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ትናንት ማክሰኞ ነሐሴ 09/2015 […]

በአማራ ክልል “ሁሉንም ኃይሎች” ያካተተ “ጊዜያዊ አስተዳደር” እንዲቋቋም አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጠየቁ – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

August 14, 2023 በሃሚድ አወል የቀድሞው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በአማራ ክልል “ሁሉንም ኃይሎች” ያካተተ “ጊዜያዊ አስተዳደር” እንዲቋቋም ጠየቁ። አቶ ገዱ በአማራ ክልል ያለውን “ችግር በቅንነት ለመፍታት” ፖለቲካዊ ንግግር መደረግ እንዳለበትም አሳስበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ወደ ስልጣን ያመጣውን “ለውጥ” ከመሩ ባለስልጣናት አንዱ መሆናቸው የሚነገርላቸው አቶ ገዱ ይህን ማሳሰቢያ የሰጡት፤ በዋነኛነት በአማራ […]

የተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በአብላጫ ድምጽ አጸደቀ – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

August 14, 2023 በሃሚድ አወል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከአንድ ሳምንት በፊት የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በአብላጫ ድምጽ አጸደቀ። አዋጁን 16 የፓርላማ አባላት ሲቃወሙት፤ 12 አባላት ደግሞ ድምጽ ከመስጠት ታቅበዋል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሐምሌ 28፤ 2015 በሙሉ ድምጽ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት፤ በአማራ ክልል እና “እንዳስፈላጊነቱ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች” ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማጽደቅ […]

ፋኖ እና መንግስት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ጦርነቱን በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ኢሰመኮ ጥሪ አቅርቧል።

August 14, 2023  የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ የአማራ ክልል ግጭትን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ተፋላሚ ወገኖች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ጦርነቱን በአስቸኳይ እንዲያቆሙ፣ ለውይይት ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር እና ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እንዲስማሙ ጥሪ አቅርቧል። በአማራ ክልል በሚገኙ ከተሞች እና የከተሞች ዙሪያ ከባድ ውጊያ እንደነበረ አረጋግጫለሁ ያለው ኢሰመኮ፤ በከባድ መሳሪያዎች ሰላማዊ ሰዎች ላይ ሞትና የአካል […]

የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አዋጅ እና ሰብአዊ መብቶች

August 12, 2023 Press Release ከአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታው ጥብቅ አስፈላጊነት፣ ተመጣጣኝነት በተጨማሪ የፓርላማው የአስቸኳይ ጊዜ ወቅት ክትትል (Parliamentary Oversight) እና የኮሚሽኑ የሰብአዊ መብቶች ክትትል የማድረግ ኃላፊነት ሊረጋገጥ ይገባል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. በሚኒስትሮች ምክር ቤት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 ላይ ያዘጋጀውን ባለ 26 ገጽ የሰብአዊ መብቶች ትንታኔ […]

ዘለቄታዊ ሰላም የሚሰፍነው በንግግርና በድርድር ብቻ ነው!

August 13, 2023 – EthiopianReporter.com  አገራዊ የምክክር ኮሚሽን በቅርቡ ባወጣው መግለጫ በተለያዩ አካባቢዎች የሚካሄዱ ግጭቶች ተልዕኮውን ለማከናወን መሰናክል እንደሆኑበት ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ ለአገር ዘለቄታዊ ሰላም ተስፋ ይፈነጥቃል ተብሎ የሚጠበቀው ብሔራዊ የምክክር ሒደት ሲደናቀፍ፣ መጪው ጊዜ ብሩህ ይሆናል ብሎ መጠበቅ በፍፁም አይቻልም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሐሳብ ልዩነቶችንና አለመግባባቶችን በንግግርና በምክክር መፍታት ሲገባ፣ በተለያዩ አካባቢዎችና በተለያዩ ወገኖች እየተወሰዱ ያሉ የኃይል […]

ኢትዮጵያ ውስጥ ቀላሉ ሥራ ጠመንጃ ይዞ ጫካ መግባት ሆኗል

August 13, 2023 – EthiopianReporter.com ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ቀላሉ ሥራ ጠመንጃ ይዞ ጫካ መግባት ሆኗል›› መረራ ጉዲና (ፕሮፌሰር)፣ የኦፌኮ ሊቀመንበር ፖለቲካ በበጋዜጣዉ ሪፓርተር August 9, 2023 የዕውቆቹ ፖለቲከኞች የለማ፣ የልደቱ አያሌውና የወርቅነህ ገበየሁ መምህር ናቸው፡፡ በደርግ ዘመን የመኢሶን አባል በነበሩበት ወቅት ለሰባት ዓመታት ታስረዋል፡፡ በኢትዮጵያ ፖለቲካ በስፋት ተሳትፎ ከማድረጋቸውም በላይ፣ በአሁኑ ወቅት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር ናቸው፡፡ […]

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ሀገረ ስብከት ሕገወጡን የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት እንደማይቀበል ገለጸ !

August 10, 2023  የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ሀገረ ስብከት ሕገወጡን የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት እንደማይቀበል ገለጸ ! የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ሀገረ ስብከት በትግራይ ክልል የተፈጸመውን ሕገወጥ የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት እንደማይቀበል የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ሐዲስ መምህር ዜናዊ ሀሸተ ለተ.ሚ.ማ ገለጹ። መጋቤ ሐዲስ መምህር ዜናዊ ሀሸተ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ከተዋሕዶ […]

በአማራ ክልል ያለው ሁኔታ ወዴት ያመራል? ምንስ መፍትሄ አለው?

ከ 6 ሰአት በፊት በአማራ ክልል ለወራት የቆየው እና ባለፈው ሳምንት ተባብሶ የቀጠለው ግጭት በበርካታ የክልሉ ከተሞች በመካሄድ ላይ ይገኛል። ባለፉት ዓመታት መንግሥት ሸኔ የሚለው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ግጭቶች ውስጥ የቆየ ሲሆን፣ ከትግራይ ጦርነት ማብቃት በኋላ በአማራ ክልልም ተመሳሳይ ግጭቶች እያጋጠሙ መሆናቸው ሲዘገብ ቆይቷል። ይህ ግጭት በሠላማዊ መንገድ እንዲፈታ […]

ችግሮች በመባባሳቸው ቀጣይ ሥራዎችን በአግባቡ ለማከናወን እንደሚቸገር አገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታወቀ

August 9, 2023 – EthiopianReporter.com  ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያና ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ ሒሩት ገብረ ሥላሴ ዜና ችግሮች በመባባሳቸው ቀጣይ ሥራዎችን በአግባቡ ለማከናወን እንደሚቸገር አገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታወቀ ኢዮብ ትኩዬ ቀን: August 9, 2023 በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ ችግሮች እየተባባሱ በመምጣታቸው፣ ቀጣይ ሥራዎችን በአግባቡ ለማከናወን እንደሚቸገር አገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ ይህንን ያስታወቀው ወቅታዊ ጉዳዮችን በማስመልከት ማክሰኞ ነሐሴ 2 […]