የጉምዝ ሕዝብ (ከተማሪዎቼ እንደተረዳሁት) – ውብሸት ሙላት

May 3, 2019 የጉምዝ ሕዝብ (ከተማሪዎቼ እንደተረዳሁት) ውብሸት ሙላት በተደጋጋሚ እንደገለጽኩት ለሦስት ዓመታት ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ከአምስቱ ብሔረሰቦች የተዉጣጡ፣ የመጡ 99 ተማሪዎችን አስተምሬያለሁ፡፡ 100 ነበር የተመደቡት፡፡ አንድኛዉ (ደፋላ የሚባል ተማሪ) እንደ ጀመረ ለሳምንት ያህል ሳይማር አቋረጠ፡፡ ዘጠና ዘጠኙም ተማሪዎች እንዲመረቁ አድርገናል፡፡ ከትምህርት (education) ወደ ሥልጠና (training) እንዲያዘነብል በማድረግ ክልሉ ከፍተኛ የሕግ ባለሙያ እጥረት ስለነበረበት (እንደዉም የለዉም […]

እናሸንፋለንና እናቸንፋለን! (ያሬድ ጥበቡ)

May 3, 2019 እናሸንፋለንና እናቸንፋለን! ያሬድ ጥበቡ ትናንት ማታ ቤቲ ዘኤል ቲቪ ከዶክተር መረራ ጋር ያደረገችውን ቃለምልልስ ስትከፍት በእናሸንፋለንና በእናቸንፋለን ያልረባ ልዩነት እርስ በርሱ ስለተጫረሰው ትውልድ የሚባለውን ክስ ነካ አድርጋ  እንዳስብ አስገደደችኝ ። ቤቲ የመጀመሪያዋ አይደለችም ይህን ስትል፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ቢያንስ ሁለት ጊዜ ተመሳሳይ ትችት ሲያደርጉ አዳምጫለሁ። በእውን ግን ባልረባ የእናሸንፋለንና እናቸንፋለን ልዩነት እርስ በርስ […]

በፕሬስ ነፃነት ቀን – ስለ ኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ነፃነትና ሚና

May 3, 2019 VOA Amharic : ቀደም ባሉ ዓመታት የፕሬስ ነፃነት ቀንን ለመዘከር በዓለም አቀፍ ተቋማት የወጡ ሪፖርቶች ፤ ኢትዮጵያን የመናገርና የመጻፍ ነፃነት የሌለባት፣ ጋዜጠኞችና ጸሐፊዎችን በማሰደድ እና በማሰር ርምጃዎች ከመጀመሪያዎቹ “አፋኝ” አገራት ተርታ ይመድቧት ነበር። በዘንድሮው ሪፖርት ደግሞ ኢትዮጵያ “አንድም የታሰረ ጋዜጠኛ የሌለባት አገር” ተብላለች። •የአዳዲሶቹ ሪፖርቶች ይዘት ኢትዮጵያ የነፃነት አገር የሚለውን መስፈርት ማሟላቷን […]

ሁለተኛው የአፍሪካ- ቻይና የኦንላይ ግብይት ጉባኤ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

May 3, 2019 Source: https://fanabc.com አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሁለተኛው የአፍሪካ- ቻይና የኦንላይን (ኢ-ኮሜርስ) ጉባኤ አዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ጉባኤውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከቻይና አለም አቀፍ የንግድ ድርጅት የኢ-ኮሜርስ ባለሙያዎች ኮሚቴ ጋር በመተባበር እንደሚያዘጋጁት ነው የተነገረው፡፡ ይህንን ጉባኤ ለማዘጋጀት የሚያስችለውን ስምምነትም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ ከቻይና የኢ-ኮሜርስ […]

የደቡብ ሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች የሽግግር መንግሥት ምስረታውን ለማራዘም ስምምነት ላይ ደረሱ

May 3, 2019 Source: https://fanabc.com አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደቡብ ሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች የሽግግር መንግሥት ምስረታውን ለማራዘም ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገለጸ፡፡ የደቡብ ሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች የሽግግር መንግሥት ምስረታውን የማራዘም ውሳኔ ላይ የደረሱት ዛሬ በአዲስ አበባ ባካሄዱ ውይይት ላይ ነው። የደቡብ ሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች ባለፈው መስከረም ወር በአዲስ አበባ በደረሱት ስምምነት መሠረት በያዝነው ወር […]

የሶማሌ ክልል መንግስት ካቢኔ አስቸኳይ ስብስባ – ቢኦኤ / አማርኛ

ግንቦት 04, 2019 አዲስ ቸኮል የሶማሌ ክልል መንግስት ካቢኔ ዛሬ ከሰዓት ባካሄደውሶማሌ የሚበዛባቸው ሶስቱን አወዛጋቢ ቀበሌዎች ወደሶማሌ ክልል እንዲዛወሩ ወስኗል:: ድሬዳዋ —  ካቢኔው ማምሻውን ባወጣው ባለ8 ነጥብ መግለጫ በ2004ዓም ሶስቱ ቀበሌዎች ማለትም ገርበኢሴ; አዳይቱና ኡንዱፎ አብዛኛው ነዋሪያቸው ሶማሌ ሆኖ እያለ ወደአፋር ክልል እንዲካለሉ በወቅቱ የነበሩ አመራሮች የወሰኑት ውሳኔ የሀገሪቱን ህጎች የጣሰ በመሆኑ ከአሁን በሁዋላ እንደማይቀበለው […]

“የማያድጉ ፓርቲዎች እንደምን ያሉ ናቸው?” ፀጋዝአብ ለምለም ተስፋይ

May 1, 2019 የኢኮኖሚክስ መምህርና ጸሓፊ(ሸክም የበዛበት ትውልድ፡ 2009 እና የምሥራቃዊት ኮከብ፡ 2010 መጻሕፍት አዘጋጅ)   በሀገራችን ለረዥም ዘመናት በቆየው ሥርዓት የተነሣ – የፖለቲካ ባሕላችን ሥልጣንን የኹሉ ነገር መነሻና መዳረሻ ብሎም ማዕከሉን ያደረገና የሚያደርግ በመኾኑ  ሀሳባዊነትን መሠረት ካደረገ ፖለቲካ ይልቅ ኃይልን አድርጎ መቆየቱ ይታወቃል፡፡   ኃይል የኹሉ ነገር ምንጭና መሠልጠኛ ኾኗል፡፡ በረዥሙ የሀገራችን ታሪክ ውስጥ ለሥልጣንና ስለሥልጣን […]

መተከልን እንደ ክሬሚያ -መስቀሉ አየለ

April 29, 2019 ክሬሚያ ጥንትንም የሩሲያ ግዛት የነበረች ብትሆንም ክሬሚያን አሳልፎ የሰጠው በወቅቱ የሶቪየትን ኤምፓየር እንዲገዛ በትረ መንግስቱን ስታሊን እጅ ለመረከብ እድል እጁ መዳፉ ውስጥ የገባችለት khushchov ነበር። khushchov ዩክሬን የሩሲያ ግዛት አካል የሆነችበትን ሶስት መቶኛ አመት ምክንያት በማድረግ ክሬሚያን ከሩሲያ ወስዶ ወደ ዩክሬን ለመደባለቅ የፈጀበት አስራ አምስት ደቂቃ ብቻ ሲሆን ሰውየው ይኽን እርምጃ እንዲወስን […]

አብይ አሕመድ እና ደፋሩ ሓቢብ ቡርጊባ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)

April 29, 2019 ለረዢም አማታት ትችቶቼን የተከታተላችሁኝ ሁሉ ፈረንጆች “ቦልድ” የሚሉት “ፈጣጣ” ትችቶችን የምተች ተቺ መሆኔን ታውቃላችሁ። በዚህ ባሕሪየ ብዙ ጠላት አፍርቻለሁ።ደፋር እንጂ አጎብዳጅ አለመሆኔን እጅግ ደስ ይለኛል። በኢትዮጵያ ማሕበረሰብ ተወዳጁና ተጠቃሚው አጎብዳጁ እና አጭበርባሪው ክፍል እንጂ ደፋር እና ቅን ተወዳጅም ተሞጋሽም እምብዛ አይደለም። ይህንን አውቃለሁ። ታሪካችንም ይህንን ይነግረናል። አጼ ቴዎድሮስ በደፋርነታቸው ብዙ ጠላት ተገንብቶባቸው […]

Under Abiy, Ethiopia’s media have more freedom but challenges remain – CPJ

By Muthoki Mumo/CPJ Sub-Saharan Africa Representative on April 29, 2019 Ethiopia’s Prime minister Abiy Ahmed speaks during a press conference at his office in Addis Ababa, on August 25, 2018. (Photo by Michael Tewelde / AFP) During a trip to Addis Ababa in January, it was impossible to miss the signs that Ethiopian media are enjoying unprecedented […]