“ልደቱ እስስቱ!” ያለው ማን ነበረ???

ህም! ከደቂቃዎች በፊት አቶ ልደቱ ከዐሥራት ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ ክፍል ሁለት ስመለከት ነበር፡፡ እንደተለመደው ቅጥፈትና ሸፍጥ ያዘለ ነበር!!! አቶ ልደቱ ከሁለት ዓመት በፊት የጀቲቪ እንግዳ ሆኖ “እኔ አማራ ሲባል የማውቀው ክርስቲያን ለማለት መሆኑን ነው እንጂ በብሔረሰብ መጠሪያነቱ አላውቀውም!” እንዳላለ ሁሉ ለዚህ ክህደቱ አማራን ይቅርታ ሳይጠይቅ ዛሬ ደግሞ ፈራ ተባ እያለ በነገር መሀል “አማራ ነኝ!” […]

‹‹በሕዝብ የተሰጠኝ ኃላፊነት ሊከበር ይገባል›› ህወኃት … አለማየሁ አንበሴ

Saturday, 25 January 2020 11:47 ‹‹ምደባው ከብሔርና ከማግለል ጋር አይገናኝም›› –ጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት የህወኃት አመራር አባላት ከፌደራልና ከአዲስ አበባ አስተዳደር የኃላፊነት ቦታዎች መነሳታቸውን ህወኃት የተቃወመ ሲሆን ድርጊቱ በሕዝብ የተሰጠኝን ሕጋዊ ኃላፊነት የሚጻረር ነው ብሏል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የህወኃት አመራሮችና አባላት በመሆናቸው ብቻ ከፌደራል መንግሥትና ከአዲስ አበባ አስተዳደር የኃላፊነት ቦታዎች እንዲነሱ እየተደረገ ነው ያለው ህወኃት፤ ይህ ተግባር ፍፁም […]

“በኢትዮጵያ ህልውና ጉዳይ ላይ ከማንም ጋር አንደራደርም” – ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ … አለማየሁ አንበሴ አዲስ አድማስ

Saturday, 25 January 2020 12:08 ከደቡብ ክልል ከተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በክልሉና በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰሞኑን ውይይት ያደረጉት ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፤ መንግስታቸው በኢትዮጵያ ህልውና ከማንም ጋር እንደማይደራደር አሳሰቡ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “የኢትዮጵያን የብልጽግና ጊዜ ማቆም የሚችል ሃይል የለም” ብለዋል፡፡ ከሀገሪቱ ሠላም ማጣትና የህልውና ስጋት ጋር በተያያዘ ከተሰብሳቢዎቹ ጥያቄ የቀረበላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለሠላም መስፈን […]

ለኢትዮጵያ ሕዝብ የቀረበ አስቸኳይ ጥሪ!!!…ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

እናንተየ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሀገርና ለሕዝብ የቆመ የፖለቲካ ድርጅት፣ የሲቪክና የእምነት ተቋማት እንዲሁም ምሁራን አሉ ወይ??? ባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በሚያደርጉት የዓባይ ግድብ ድርድር አሜሪካ በእጅጉ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም እስከወዲያኛው የሚያስቀርና የሚጎዳ የማግባቢያ ሰነድ ላይ እንደተስማሙ መግለጻቸውን ተከትሎ ለፖለቲካ ድርጅቶች፣ ለሲቪክና የእምነት ተቋማት፣ እንዲሁም ለምሁራን ያቀረብኩት አስቸኳይ ጥሪ ነበር!!! ይሄንን አደገኛ የክህደት ውል አገዛዙ ከማንም […]

ከትናንት በስቲያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የሚኒስትሮች ሹም ሽር ማድረጋቸው ተሰምቷል።…..BBC

የህወሃት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር የነበሩት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረ እግዚአብሄር በጠቅላይ ሚንስትሩ ሹም ሽር ከስልጣናቸው ከተነሱት መካከል ተጠቃሽ ናቸው። በተመሳሳይ የህወሃት ከፍተኛ አመራር የሆኑት በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊው ሰለሞን ኪዳነ (ዶ/ር) ከስልጣን እንደሚነሱ ደብዳቤ እንደደረሳቸው ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ይህን ተከትሎ ህወሃት ባወጣው መግለጫ አባላቱን ከፌደራል ከፍተኛ የሃላፊነት […]

የአገዛዙ ትልቅ ፋውል!!!….ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

የአገዛዙ ትልቅ ፋውል!!! ወያኔ/ኢሕአዴግ ሕገመንግሥታቸው እራስን በራስ በማሥተዳደር መብት ሽፋን የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የትግሬ፣ የሐረሪ፣ የአፋር፣ የሱማሌ ወዘተረፈ. እያለ ሀገሪቱን በዘር ሸንሽኖ “ይሄ የዕከሌ ብሔረሰብ ክልል ነው!” ከማለት ጀምሮ “ይሄ የእከሌ ጎሳ ወረዳ ነው፣ ልዩ ወረዳ ነው!” እስከማለት ወርዶ ሀገሪቱን በዘር በጣጥቆ ማደሉንና የብሔረሰቡ ወይም የሕዝቡ ፍላጎት ከሆነ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ክልል የመሆን መብትን መስጠቱን […]

የኢቢሲ ጋዜጠኞች ለምን ይጠፋሉ?..BBc

ከእነዚህም መካከል አንዱ ለ9 ዓመታት በኢቢሲ ከሪፖርተርነት እስከ ዜና ክፍል ምክትል ዋና አዘጋጅነት ያገለገለው ጋዜጠኛ ቢላል ወርቁ ይገኝበታል። ጋዜጠኛው ቢላል በዚህ ሳምንት ሰኞ የተካሄደውን የዩኬ–አፍሪካ የኢንቨስትመንት ፎረም ለመዘገብ በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ከሚመራ ልዑክ ጋር ወደ ለንደን የተጓዘ ሲሆን ጥገኝነት መጠየቁን ለቢቢሲ አረጋግጧል። • የኢቢሲ የትግርኛ ክፍል ሠራተኞች በተቋሙ አስተዳደር ጫና ይደርስብናል አሉ ከቢላል በተጨማሪ […]

የሟቹ የአማራ ብሔርተኝነት ትግል አጭር የሕይዎት ታሪክ!!! …ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

እስከ ዘር ማጥፋት ጥቃት የደረሰ አረመኔያዊ የግፍ ጥቃት፣ ገደብ የለሽ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ በ21ኛው መ.ክ.ዘ. ፈጽሞ የማይጠበቅ የሕግ ሽፋን የተሰጠው የኢፍትሐዊ አሥተዳደር በደል ብሶት፣ ያፈጠጠ የሀገር መፍረስ ሥጋት ወዘተረፈ. የወለደው የአማራ ብሔርተኝነት ትግል ተወልዶ የነበረው የአማራ ብሔርተኝነት ትግል “ተወለደ ወዲያውም ሞተ!” የመባልን ያህል አጭር የሕይዎት ታሪክ ነው ያለው!!! በስንት መከራ ስንት ዋጋ ከፍለንበት ተቀስቅሶ የነበረው […]

በጎንደር የጥምቀት በዓል መቀመጫ ሰገነት ላይ በደረሰ መደርመስ የአሥር ሰዎች ሕይወት አለፈ

22 January 2020 በጋዜጣዉ ሪፓርተር በሳሙኤል ጌታቸው በየዓመቱ የጥምቀት በዓል ከሚከበርባቸው ሥፍራዎች አንዱና ዋነኛ በሆነው ጎንደር ከተማ በደረሰ የመደርመስ አደጋ፣ አሥር ሰዎች መሞታቸውና በርካቶች ቀላልና ከባድ ጉዳት ደረሰባቸው፡፡ ባህረ ጥምቀቱ በተዘጋጀበት የአፄ ፋሲል መዋኛ ገንዳ አካባቢ ለእንግዶች መቀመጫ ተብለው ከተሠሩ የእንጨት ርብራቦች መካከል በአንዱ በደረሰ መደርመስ፣ የአሥር ሰዎች ሕይወት ማለፉን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል አስታውቋል፡፡ […]

ዶናልድ ትራምፕ ኤርትራን ጨምሮ በአራት የአፍሪካ አገራት ላይ የጉዞ ክልከላ ሊያደርጉ መሆኑ ተነገረ።..BBC

…በርካታ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን የጉዞ እገዳ ይጣልባቸዋል የተባሉ አገራት ዝርዝርን ተመልክተናል ያሉ ባለስልጣናትን ዋቢ በማድረግ፤ የጉዞ እገዳው ሰለባ ይሆናሉ የተባሉት የአፍሪካ አገራት ኤርትራ፣ ናይጄሪያ፣ ሱዳን እና ታንዛኒያ መሆናቸውን ዘግበዋል። በስዊትዘርላንድ ዳቮስ እየተካሄደ ባለው የዓለም የምጣኔ ኃብት መድረክ ላይ ከ‘ዎል ስተሪት ጆርናል‘ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ፤ ፕሬዝዳንት ትራምፕ አራት የአፍሪካ አገራት ላይ የጉዞ እገዳ ለመጣል ማቀዳቸውን […]