ውዥንብሩ ይጥራ!

የታገቱት ተማሪዎች ነጻ ይውጡ! ለታገቱት ልጆቻችን፣ እህትና ወንድሞቻችን ድምጽ የሆናችሁ ሁሉ ሕዝባዊ ወገናዊነታችሁ ይቀጥል! በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን መከታተል ሳይችሉ ቀርተው ወደቤታቸው ለመመለስ መንገድ የጀመሩ የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች እገታ ተሰማ። እነሆ እገታው ከተካሄደ ሁለት ወራት ቢያልፉም እስከአሁን ስለሁኔታው የጠራ መረጃ የለም። ይህ የሀገር ማፈሪያ የሆነና ለማንም ኢትዮጵያዊ፣ በተለይም ለወጣቶቹና ለወላጆቻቸው አስደንጋጭ እና የስቃይ ምንጭ ለሆነ […]

ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ለሁለተኛ ጊዜ አስቸኳይ ጥሪ አቀረቡ!!!

የሐረርና የሱማሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ መቃርዮስ ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አገዛዙ አድሏዊ አሠራርን እና ገፊ እንቅስቃሴን በአስቸኳይ እንዲያቆም አጥብቀው አሳስበዋል!!! በሐረር በጥምቀት በዓል ላይ የተነሣውን ግፍ የጠቀሱት ብፁዕነታቸው “የክልሉ መንግሥት አጥፊዎችን ማሰርና ለሕግ ማቅረብ ሲገባው በተቃራኒው ኦርቶዶክሳውያንን እያሰረና እያንገላታ ነው!” ሲሉ ቅሬታቸውን በምሬት ገልጸዋል!!! ብፁዕነታቸው እንደገለጹት ከጥር10 -13 ቀን 2012 ዓ.ም. […]

ሰልፎቹ በቅጥረኞቹ በወጣት ማኅበራት የታለመላቸውን ግብ እንዳይመቱ ጥረት ቢደረግም ከሞላ ጎደል ተሳክተዋል!!!

አገዛዙ በዚህም በዚያም ብሎ ሰልፎቹን ለማክሸፍ ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፡፡ እዚህ አዲስ አበባ ከትናንት አመሻሽ እስከ ዛሬ ዕኩለ ቀን ድረስ ኢንተርኔቱን አጥፍቶት ነበር፡፡ ሰልፍ በሚደረግባቸው አካባቢዎችም በተመሳሳይ ኢንተርኔቱን እንዳቋረጠው እገምታለሁ፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ቅጥረኞቹን አሰማርቶ ሰልፎቹን በመጥለፍ የታለመላቸውን ግብ ሳይመቱ እንዲቀሩ ለማድረግ ብዙ ጥሯል!!! ትናንትና አመሻሹ ላይ “የባሕርዳሩን ሰልፍ አዘጋጅ የባሕርዳር ወጣቶች ማኅበር ነን” ያሉ ቅጥረኞች […]

ሰላማዊ ሰልፉ በብአዴን ተጠልፏል!!!

አማራ አንድ ነገር ባሰበ ቁጥር እየጠለፈ የመውሰድ ግቡን እንዳይመታ የሚያደርገው ቀንደኛ ጠላታችን የወያኔ አህያ ብአዴን ነገ የሚደረገውን ሰልፍ ከጀርባ ተቆጣጥሮት ሰልፎቹ ሕዝቡ ቁጣውንና ስሜቱን የሚገልጥባቸው እንዳይሆኑና እራሱ ያዘጋጃቸው መፈክሮች ብቻ ተሰምቶባቸው የሚበተኑ አልጫ ሰልፎች እንዲሆኑ ለማድረግ ካድሬዎቹንና ቅጥረኞቹን አሠማርቷል!!! ወገን ሆይ! ፀረ አማራው ብአዴን ሰልፎችን የረባ የሕዝብ ድምፅ እንዳይሰማባቸው አድርጎ እንዲበተኑ ለማድረግ ቢጥርም እኛ ግን […]

አገራችን ካልተረጋጋች፣ ለዜጐችም ለመረጠው መንግስትም፣ መከራ ነው

Monday, 27 January 2020 00:00 Written by  ዮሃንስ ሰ ባለፉት ዓመታት፣ በርካታ አደገኛ ቀውሶች የተደራረቡባት አገራችን፣ ለጥቂት “ብትተርፍም”፣ እስካሁን ገና ሙሉ ለሙሉ ያልተረጋጋችና ያላገገመች አገር ናት፡፡ ዘንድሮ እንደገና፤ በፖለቲካ ምርጫ ሰበብ፣ ለሌላ ዙር የጥፋት ቀውስ ከዳረግናትና ከታመሰች፣ መዘዙ ይበዛና፤ መከራችን ይከብዳል፡፡ለወትሮውም፣ ከችጋር ጋር የተቆራኘው የዜጐች ኑሮ፣ በአምስት ዓመታት ተከታታይ ቀውሶች ሳቢያ፣ ክፉኛ እየተናጋ ምንኛ እንደተጐሳቆለ፣ […]

‹‹ወደ ድል የምንሻገርበት ፈተና ስለሆነ ተስፋ እንዳትቆርጡ››

Sunday, 26 January 2020 00:00 Written by  ናፍቆት ዮሴፍ መንግሥት ከጋሞ ሥርዓት ቢማር፣ አገር ለዚህ ሁሉ ቀውስ አትዳረግም ነበር አገርና ሥልጣኔን የገነቡ አባቶች ሊፀለይላቸው ሲገባ እንዴት ይረገማሉ?! ተማሪዎቹ ሁሉ ‹‹ሁለተኛ እጃችንን ለጥፋት አናነሳም›› ብለው ቃል ገብተዋል በጋሞ ባህላዊ ሥርዓት ካኦ ታደሰ ዘውዴ፤ ከዘር ሲቀባበል በመጣው የንግስና ሥርዓት 15ኛው ካኮ (ንጉስ) ናቸው፡፡ በባህላዊውም ሆነ በዘመናዊው ትምህርትና […]

የትናንትናው ቆራጥ የአማራ ታጋይ የዛሬው ቅጥረኛ ማሙሸት አማረ!!!

አቶ ማሙሸት ከብአዴኑ ሚዲያ ከዐሥራት ጋር ያደረገውን ቃለመጠይቅ ክፍል አንድ ተመለከትኩት፡፡ አየ አቶ ማሙሸትiii ኦነግ ሠራዊቱን ይዞ ገብቶ ሀገር እያወከ፣ እንደትናንቱ ሁሉ አማራን የትም በግፍ እየገደለ፣ ባንክ እየዘረፈ፣ ምድረገኝ ላይ ካምፕ ገንብቶ እያሸበረና ወሎን “ሰሜን ኦሮሚያ!” እያለ ጥቅሙን በኃይል እያስከበረስና ለማስከበር እየተንቀሳቀሰ “ሀገር ውስጥ ገብቶ በሰላማዊ ትግል እንዲወዳደር ያበቃነው እኛ ነን!” ብሎ እርፍ!!! አየ የኛ […]

የታገቱት ተማሪዎች፡ የቤተሰብ ሰቀቀን፤ የማሕበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ጩኸት፤ የመንግሥት ዝምታ!! BBC

ከሚማሩበት የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ለደህንነታቸው በመስጋት ወደ ቤተሰቦቻቸው እየተመለሱ ሳለ ማንነታቸው ባልታወቀ ወጣቶች የታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ አሁንም ምላሽ አላገኘም። ተማሪዎቹ ከታገቱ 50 ቀናት አልፏቸዋል። ከሶስት ሳምንታት በፊት ከእገታው ያመለጠችው አስምራ ለቢቢሲ አማርኛ ድምጿን ስትሰጥ ከደንቢ ዶሎ ወደ ጋምቤላ የማመላለሻ አውቶብስ ውስጥ ሳሉ መታገታቸውን ታወሳለች። በወቅቱ ተማሪዎቹ ሲታገቱ እሷን ጨምሮ በቁጥር 18 እንደነበሩ ከእነዚህም መካከል 13ቱ […]