ስለ ፌደራል መንግሥትና የትግራይ ክልል ግጭት ማን ምን አለ? – ቢቢሲ / አማርኛ

5 ህዳር 2020 ትላንት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ መከላከያ ሠራዊት ሕወሓት ላይ የኃይል እርምጃ እንዲወሰድ መታዘዙን መግለጻቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ትላንት ማምሻውን በሰጡት መግለጫ በሁመራ፣ በዳንሻ እና በቅርቃር አካባቢዎች የአገር መከላከያ ሠራዊት እና የአማራ ክልል ልዩ ኃይልና ሚሊሻ “ሕወሓት ያሻውን ሳያደርግ የሞከራቸው ሙከራዎች ከሽፈዋል” ብለዋል። የአገር መከላከያ ሠራዊትም “የተቃጣበትን ጥቃት በመመከት እንዲሁም በማክሸፍ የሕዝቦችን ደህንነት […]

“የጦርነቱ መዘዝ ለቀጠናውም ይተርፋል” አወል አሎ (ዶ/ር) – ቢቢሲ / አማርኛ

7 ህዳር 2020 ከጊዜ ወደ ጊዜ የሻከረው የትግራይ ክልልና የፌደራል መንግሥት ግንኙነት ወደማይታረቅ ደረጃ ደርሶ ወደ ጦርነት አምርቷል። ለመሆኑ የዚህ ጦርነት መዘዙ ምንድን ነው? የሚሉና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ በዩናይትድ ኪንግደም በኬል ዩኒቨርስቲ መምህርና የምስራቅ አፍሪካ የፖለቲካ የግጭቶች ተንታኝ አወል አሎ ቃሲም (ዶ/ር) ጋር ቢቢሲ ቆይታ አድርጓል። ቢቢሲ፡ -በትግራይ ክልልና በፌዴራል መንግስት የተከሰተው ጦርነት አራተኛ ቀኑን […]

ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ በ97 ዓመታቸው ዐረፉ

November 8, 2020 – ሐራ ዘተዋሕዶ አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ዐረፉ የብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ አጭር ዜና ሕይወትልደት፡- ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ፣ በጎንደር ክፍለ ሀገር፣ በደብረ ታቦር አውራጃ በፋርጣ ወረዳ ልዩ ስሟ መገንታ ቍስቋም በተባለች ደብር፣ ከቄስ ወርቅነህ ትኩ እና ከወይዘሮ አንጓች አታሌ በ1916 ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ – መንፈሳዊ እና ዘመናዊ ትምህርት፡- በሕፃንነት […]

የሁመራ ሱዳን መንገድን ጨምሮ በርካታ ቦታዎችን መከላከያ ሰራዊት ተቆጣጠረ

November 8, 2020 – Konjit Sitotaw ማይዳሊ፣ ዳንሻ፣ ባዕከር፣ ልጉዲ፣ የሁመራ አየር ማረፊያ እንዲሁም የሁመራ ሱዳን መንገድ በቁጥጥር ስር መዋሉን ኢቢሲ ዘግቧል! የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ማይዳሊ፣ ዳንሻ፣ ባዕከር፣ ልጉዲ፣ የሁመራ አየር ማረፊያ እንዲሁም የሁመራ ሱዳን መንገድን እንደተቆጣጠረ ገለጸ። – የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ሰራዊቱ በምዕራብ ግንባር እያደረገ […]

“MR300” ወይም “MR400” የሚባል ሚሳኤል ተብሎ ሲወራ የነበረው በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም የለም !

November 8, 2020 – Konjit Sitotaw ወታደራዊ መረጃ – ሻለቃ ማሞ ለማ– ወያኔ ጦርነት ከመቀስቀሱ ጋር ተያይዞ ሰሞኑን ኢትዮጵያውያን በሶሻል ሚዲያ ላይ የሚቀባበሉት ሚሳኤልና ሮኬትን የተመለከተ ጉዳይ አንዳንድ ከእውነት ጋር የማይገናኙ የተጋነኑ መረጃዎች በመተላለፍ ላይ ስለሚገኙ ያንን ማጥራት አስፈላጊ ሆኗል። – 1ኛ፡ “MR300” ወይም “MR400” የሚባል ሚሳኤል ተብሎ ሲወራ የነበረው በዚህ ዓይነት የሚጠራ ሚሳኤል በኢትዮጵያም […]

ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ዘጋች

ህዳር 07, 2020 ቪኦኤ ዜና ፎቶ ፋይል ፤ ትዮጵያን በሰሜን ምዕራብ በኩል ከሱዳን ጋር በሚያዋስናት ድንበር ሰዎች ሲተላለፉ እ.ኤ.አ ሰኔ 3/2015 ዓ.ም የተነሳ።/ፎቶ- ኤፒ ሙሉ ጌታ አያና ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን ድምበር በከፊል መዝጋቷን ሱና የተሰኘ የሱዳን ዜና ወኪል ዘግቧል። ድምበር መዝጋቱን ሐሙስ ዕለት ያሳወቁት የሃገሪቱ ዋና ጸሐፊ እና ከሳላ የተሰኘው የሱዳን ክፍለ ግዛት አስተዳዳሪ […]

በእንሰት ተክል ላይ የዘረመል ምሕንድስና እንዳይደረግ ማኅበረሰቡ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ – ኢትዮጵያ ሪፖርተር

8 November 2020 EthiopianReporter.com ተመስገን ተጋፋው በኢትዮጵያ ለበርካታ አገልግሎት የሚውለውን የእንሰት ተክል የዘረመል ምሕንድስና እንዳይደረግበት፣ ማኅበረሰቡ ከፍተኛ ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ፡፡ ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን እየሰጠ የሚገኘውን እንሰት የዘረመል ምሕንድስና ቴክኖሎጂን በመጠቀም፣ የዘር ዓይነቱን አንድ ዓይነት ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ ተቋማትን ማስቆም እንደሚገባ ተገልጿል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ የዕፀዋት የሥነ ሕይወት ክፍል የብዝኃ ሕይወት ትምህርት መምህርና […]

የሕዝቡን ራስን በራስ የማስተዳደር መብት የሚያስከብር ጊዜያዊ አስተዳደር በትግራይ ይቋቋማል።

November 7, 2020 የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም በሙሉ ድምፅ ውሳኔ አሳልፏል።–ውሳኔውን አስመልክቶም የምክር ቤቱ አፈጉባኤ አደም ፋራህ እንዳሉት “የሚቋቋመው አስተዳደር በሕገ መንግስቱ ድንጋጌዎች መሰረት የሚሠራና የትግራይን ሕዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት የሚያስከብር ይሆናል” ብለዋል። – “ሕገወጡ የህወሓት ቡድን የትግራይ ሕዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት የሚከበረው በእሱ ብቻ […]

የደፈረሰው ካልጠራ ሰላም የለም ! የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)

የተጀመረውን ጦርነት አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ ! ******//****** ጦርነት በወንድማማች እና እህትማማች ሕዝቦች መሀል የተከሰተ ልዩነትን ለመፍታት ተመራጭ መንገድ ባይሆንም ሁኔታዎች ወደተካረረ ደረጃ ላይ ሲደርሱ አይቀሬ ይሆናል፡፡ ከውጭ ከሚመጣ ወራሪ ጦር ጋር የሚደረግ ጦርነት የቱንም ያህል የሰውና የንብረት ኪሳራ ቢያስከትልም ውጤቱ ነፃነት ሲሆን ተጋድሎው ለትውልድ የሚተላለፍ ኩራት ይሆናል፡፡ የእርስ-በእርስ ጦርነት በምንም መመዘኛ ቢታይ የኩራት ምንጭ አይሆንም፡፡ […]

ጥቅምት 30 ሊጀመር የነበረው አጠቃላይ ትምህርት ላልተወሰነ ጊዜ አራዘመ – ኢትዮጵያ ሪፖርተር

EthiopianReporter.com 8 November 2020 ምሕረት ሞገስ ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም. የተጀመረውን የስምንተኛና የ12ኛ ክፍል የገጽ ለገጽ ትምህርት በመቀጠል፣ ሁሉም ክፍሎች ሰኞ ጥቅምት 30 እንደሚጀምሩ ተወስኖ የነበረ ቢሆንም፣ የተማሪዎቹ የገጽ ለገጽ ትምህርት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡ ይህ ውሳኔ በመማር ላይ የሚገኙትን የስምንተኛና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የማይመለከት መሆኑን ትምህርት ቢሮው ገልጾ፣ የኮሮና […]