የቤንዚን የችርቻሮ ዋጋ በ11 ብር ጨመረ

24 መጋቢት 2025 የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ትናንት ይፋ ባደረገው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ጭማሪ የአንድ ሌትር ቤንዚን ዋጋ 112 ብር ከ67 ሳንቲም ደረሰ። የነጭ ናፍጣ ዋጋ ደግሞ የዘጠኝ ብር ገደማ ጭማሪ ተደርጎበታል። ከእሁድ መጋቢት 14/2017 ዓ.ም. ምሽት ጀምሮ ተግባራዊ መሆን የጀመረው የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ማሻሻያ በዚህ ዓመት ለሶስተኛ ጊዜ የተደረገ የመሸጫ ዋጋ ጭማሪ […]

አስፈላጊ እየሆነ ስለመጣው ፋይዳ መታወቂያ ሊያውቋቸው የሚገቡ 8 ጉዳዮች

24 መጋቢት 2025 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 21/2015 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ ረቂቅ አዋጅን አጽድቆ ኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያን ከሚጠቀሙ አገራት መካከል እንድትካተት በር ከፍቷል። ፋይዳ የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ዲጂታል መታወቂያ ‘አንድን ሰው’ በልዩ ሁኔታ መለየት የሚያስችል ነው ተብሎለታል። መታወቂያው በሙከራ ደረጃ ሲተገበር ቆይቶ የአዋጁን መውጣት ተከትሎ በይፋ ተግባራዊ መሆን የጀመረው። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ […]

መከላከያ ሠራዊት ጄነራል ምግበይ ኃይለ ላይ ያቀረበውን ክስ የትግራይ የሰላምና የጸጥታ ቢሮ “ኃላፊነት የጎደለው ነው” አለ

24 መጋቢት 2025 የትግራይ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ፣ የመከላከያ ሠራዊት፣ ብርጋዲየር ጄነራል ምግበይ ሃይለን “ለፋኖ ድጋፍ ይሰጣሉ” የሚለውን ጨምሮ ሌሎችም ያቀረባቸውን ክሶች ኃላፊነት የጎደለው ነው ሲል ወቀሰ። የሰላምና ጸጥታ ቢሮው፤ “እሳቱ ባለበት ለማርገብ ከመጣር ይልቅ ማርገብገብ፣ ላጋጠመህ የራስ ችግር ለተግባራዊ መፍትሔ ከመጣር ይልቅ የማይመለከተው ኣካል በመፍጠርና ጣት በመቀሰር ሰላምና ዕድገትን እንዳይጸና የሚያደርግ ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው” […]

‘ምግብ ተቆጣጥሮኝ ነበር’፡ 191 ኪሎግራም በመቀነስ ከሞት አፋፍ የተመለሰው ሰው

24 መጋቢት 2025 አዮን ፖላርድ ሆስፒታል አልጋ ሲይዝ 286 ኪሎግራም ነበር የሚመዝነው። ኩላሊቱ መሥራት እያቆመ ነበር። ለአንድ ቀንም በሕይወት ስለመቆየቱ እርግጠኛ አልነበረም። በወቅቱ 27 ዓመቱ ነበር። ኩላሊቱ በቀዶ ሕክምና መቀየር ነበረበት። ነገር ግን ከልክ ባለፈ ውፍረቱ ምክንያት ቀዶ ሕክምናው ሊካሄድ አልቻለም። “ሰውነቴ እስከሚችለው ድረስ ራሴን እየገፋሁ ነበር። ሐኪሞቹ ቀጣዩቹ ስምንት ሰዓታት በሕይወቴ ቁልፍ ሰዓታት መሆናቸውን […]

በስኮትላንድ በታዳጊው አሜን ተክላይ ግድያ ሶስተኛ ተጠርጣሪ ተያዘ

24 መጋቢት 2025, 08:00 EAT በስኮትላንድ፣ ግላስጎው ነዋሪ የነበረው ታዳጊ አሜን ተክላይ ግድያ ጋር በተያያዘ ሶስተኛ ተጠርጣሪ ተያዘ። የ15 ዓመቱ አሜን ከሶስት ሳምንታት በፊት በከተማዋ ሜሪሂል አካባቢ ክላሬንደር ጎዳና ላይ በተፈጸመበት ጥቃት በጸና ቆስሎ መገኘቱ ይታወሳል። ምንም እንኳ የድንገተኛ ሕክምና ባለሙያዎች በስፍራው ቢደርሱም ሕይወቱ እዚያው ማለፉ ተገልጿል። በአሁኑ ወቅት የ16 ዓመት ታዳጊ የሆነው ሶስተኛው ተጠርጣሪ […]

በአንድ ወቅት በሩሲያ ሥር የነበረው የአሜሪካ ደሴት

24 መጋቢት 2025 ኡናላስካ ደሴት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ወታደራዊ መቀመጫ ነበር። ፓስፊክ ውቅያኖስና ቤሪንግ ባሕር የሚገናኙበት ቦታ ላይ ይገኛል። ከሰሜን አሜሪካ ወደ ሰርቢያ ሲጓዙ ነው ይህንን የአሜሪካ ደሴት የሚመለከቱት። ወደ ምሥራቅ እስያ ቅርብ ስለሆነ ከአላስካ ሩቅ ደሴቶች አንዱ ነው። በምድር ላይ ከባድ ከሆኑ አካባቢዎች አንዱ እንደሆነ ይነገርለታል። 1,100 ማይል የሚሰፋው የአሉይታን ደሴት አካልም ነው። […]

እስራኤል የጋዛው ሆስፒታል ላይ ባደረሰችው ጥቃት በህክምና ላይ የነበሩ የሐማስ ኃላፊ ተገደሉ

24 መጋቢት 2025 እስራኤል እሑድ አመሻሹን ጋዛ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ላይ ባደረሰችው ጥቃት ነባር የሐማስ አመራር እና ረዳታቸው መገደላቸውን ሐማስ ለቢቢሲ አሳወቀ። በኻን ዩኒስ ግዛት ናስር ሆስፒታል ላይ በደረሰው ጥቃት የሐማስ የፋይናንስ ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት ኢስማኢል ባርሁም መገደላቸው ተሰምቷል። ግለሰቡ ከአራት ቀናት በፊት በእስራኤል ጥቃት በደረሰባቸው ጉዳት ምክንያት በሆስፒታሉ ሕክምና እያገኙ እንደነበር የሐማስ ባለሥልጣን ለቢቢሲ […]