በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበው ሪፖርት ” ከእውነት የራቀ ነው ” – የትግራይ ኢንዱስትሪ ቢሮ

February 13, 2024  ” የቀረበው ሪፖርት ከእውነት የራቀ ነው ” – የትግራይ ኢንዱስትሪ ቢሮ በትግራይ ክልል ” ከ200 በላይ ኢንዱስትሪዎች ስራ ጀምረዋል ” በሚል ፓርላማ ላይ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበው ሪፖርት ” ከእውነት የራቀ ነው ” ሲል የክልሉ ኢንዱስትሪ ቢሮ ወቀሰ፡፡ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጥር 28 ቀን 2016 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ስብሰባ […]

ዋልታ እና ዋፋ በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ስር ሊጠቃለሉ ነው

13 የካቲት 2024 አንድ “ግዙፍ ሚዲያ” ለመፍጠር በሚል ዋልታ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን ኮርፖሬት እንዲሁም ዋፋ ማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽን፤ በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ስር ሊጠቃለሉ ነው። በፋና እና በዋልታ ውስጥ የ25 በመቶ ድርሻ ያለው የትግራይ መልሶ ማቋቋም ኢንዶውመንት ፈንድ (ኤፈርት) በጉዳዩ ላይ አለመሳተፉን ለቢቢሲ ገልጿል። ከገዢው ፓርቲ ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያላቸው እነዚህ ተቋማት ከሌሎች በተለየ መንግሥታዊ ዜና […]

በአማራ ክልል በጥር ወር ብቻ ከ65 በላይ ሰዎች በመንግሥት ኃይሎች መገደላቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ

ከ 5 ሰአት በፊት በአማራ ክልል ውስጥ በሚገኙት ሦስት የጎጃም ዞኖች በጥር ወር ከ65 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጪ መገደላቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዛሬ ማክሰኞ የካቲት 5/2016 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ በአማራ ክልል እተካሄደ ባለው “የትጥቅ ግጭት” የንጹኃን ሰዎች ላይ ከሕግ ውጪ የሚፈጸም ግድያ አሳሳቢነቱ ቀጥሏል ብሏል። ካለፈው ዓመት […]

“በፌደራል መንግሥቱ እና በህወሓት መካከል አለመተማመን አለ” አቶ ጌታቸው ረዳ

ከ 4 ሰአት በፊት በህወሓት እና በፌደራል መንግሥቱ መካከል አሁንም ድረስ አለመተማመን መኖሩን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ። አቶ ጌታቸው ይህንን ያሉት ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ ከተመሠረተው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ባለፈው ሳምንት የተደረገውን ውይይት አስመልክቶ ለክልሉ መገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ ነው። አቶ ጌታቸው ሰኞ የካቲት 4/2016 […]

የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሆስፒታል በመግባታቸው የኔቶ ስብሰባቸውን ሰረዙ

ከ 9 ሰአት በፊት የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን በወራት ውስጥ ለሦስተኛ ጊዜ ሆስፒታል በመግባታቸው ለሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ስብሰባ የሚያደርጉትን ጉዞ ሰረዙ። የ70 ዓመቱ ኦስቲን ባጋጠማቸው ህመም ምክንያት በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኝ ሆስፒታል ጥብቅ የሕክምና ክትትል በሚያስፈልጋቸው ህሙማን ክፍል ውስጥ ናቸው። ፔንታገን እንዳለው ሚኒስትሩ ሆስፒታል የገቡት ድንገተኛ የሽንት ፊኛ ችግር ገጥሟቸው ነው። […]

አምቡላንሱ ውስጥ የተገደለው የጋዛው ነፍስ አድን ፈጥኖ ደራሽ

13 የካቲት 2024 ማስጠንቀቂያ፡ ይህ ጽሑፍ አሰቃቂ ክስተቶች የሚገለጹበት ይዘት አለው። ዜናው የተሰማው ከሰዓት 8 ሰዓት ገደማ ነው። የሕክምና ሠራተኛው ማህሙድ አል-ማስሪ እና ሌሎች የሥራ አጋሮቹ ሰሜናዊ ጋዛ ከሚገኘው አል-አውዳ ሆስፒታል ሆነው በተጠንቀቅ ይጠብቃሉ። ዜናው በድምፅ ማጉያ ተነበበ። እንዲህ ይላል “አምቡላንስ ቁጥር 5-15 ተመትቷል።” ይህ አምቡላንስ የማህሙድ አባት አምቡላንስ ነው። እሳቸውም እርዳታ ሰጪ ናቸው። ማህሙድ […]

በቴክሳስ ልጇን ይዛ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተኩስ የከፈተችው ታጣቂ ተገደለች

ከ 9 ሰአት በፊት በአሜሪካ ቴክሳስ በሚገኘው ትልቅ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከልጇ ጋር የነበረች አንዲት ታጣቂ ለአምልኮ በተሰባሰቡ ምዕመናን ላይ ተኩስ ከከፈተች በኋላ በፖሊስ በተሰጠ አጸፋ ተገድላለች። ተጠርጣሪዋ ጄንሰስ ኢቮኒ ሞሬኖ እንደምትባል እና ዕድሜዋም 36 እንደነበር ፖሊስ ገልጿል። የኢቮኒ የ7 ዓመት ልጅም በተኩስ ልውውጡ ክፉኛ ተጎድቷል። መርማሪዎች ታጣቂዋ ይዛው የነበረው መሳሪያ ሰደፍ ላይ “ፍልስጤም” የሚል […]

አውሮፓ ራሷን ለመከላከል የሚያስችላትን የጦር መሳሪያ ለማከማቸት 10 ዓመት ያስፈልጋታል ተባለ

ከ 9 ሰአት በፊት አውሮፓ ሙሉ በሙሉ ራሷን የመከላከል አቅም ለማዳበር አስር ዓመት እንደሚያስፈልጋት ግዙፉ የጀርመን የመከላከያ ኩባንያ የሆነው ርሄይንሜታል ኃላፊ ለቢቢሲ ተናገሩ። የአህጉሪቱ የጦር መሳሪያ ክምችት “መመናመኑንም” ነው አርሚን ፓፐርገር የተናገሩት። ኃላፊው ይህንን አስተያየት የሰጡት የጀርመኑ ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ ግዙፍ የተባለውን የጦር መሳሪያ ማምረቻ ኩባንያ የመሰረት ድንጋይ ለመጣል ሎወር ሳክሶኒ በተባለችው ግዛት በተገኙበት ወቅት […]