በአማራ ክልል ከ600 ሺ በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መጠቃታቸው ተገለጸ

October 22, 2024 – DW Amharic  የወባ በሽታ በአማራ ክልል ከምንጊዜውም በላይ መስፋፋቱን የጤና ባለሙያዎችና ነዋሪዎች ተናገሩ። በሩብ ዓመቱ የወባ በሽታ ምርመራ ከተደረገላቸው ሰዎች ውስጥ ክ600 ሺህ በላይ የሚሆኑት በበሽታው መያዛቸው መረጋገጡን የክልሉ ህብረተስብ ጤና ተቋም አመልክቷል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

በትግራይ ክልል ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች የተጋለጡትን ለማገዝ ያለመው ቴሌቶን

October 22, 2024 – DW Amharic በትግራይ ክልል ለረሃብና ለተለያዩ ማሕበራዊ ችግሮች የተጋለጡ ዜጎች ለማገዝ ያለመ ገቢ ማሰባሰብ ዘመቻ ትናንት እሁድ ተጀመረ። በዚህ ዘመቻ አንድ ቢልዮን ብር ለመሰብሰብ የታቀደ ሲሆን፥ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስትም 130 ሚልዮን ብር ለግሷል። በትግራይ 4 ነጥብ 5 ሚልዮን ዜጎች እርዳታ ፈላጊ መሆናቸው ተመላክቷል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

በትረምፕ እና ሀሪስ ምርጫ ዘመቻ “የውስጥ ጠላት” እና “ያልተረጋጋ” መባባሉ ተባብሷል

October 22, 2024 – VOA Amharic  የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ልንታገለው የሚገባን “የውስጥ ጠላት” አለን የሚለው ንግግር በተቃዋሚዎቻቸው ውስጥ ትልቅ የትችት ማዕበል አስነስቷል፡፡ ይሁን እንጂ ሁለቱ የሪፐብሊካን እና የዴሞክራቲክ እጩዎች በምርጫ ዘመቻው ቅስቀሳቸው የሚጠቀሙባቸው የጋሉ ንግግሮች “ዋይት ሀውስን የማሸነፍ ዕድላቸውን ሊጎዳ ይችላል” በሚል የተንታኞችን ማስጠንቀቂያ አስከትሏል፡፡ የቪኦ… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ […]

ለትግራይ ክልል ተረጂዎች ገቢ ማሰባሰብ ተጀመረ

October 22, 2024 – VOA Amharic  በትግራይ ክልል 4.5 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው፣ “አስቸኳይ ምላሽ ለትግራይ” የተባለ ኮሚቴ አስታወቀ። ኮሚቴው ተጎጂዎቹን ለመርዳት ዛሬ ባስጀመረው የገቢ ማሰባሰቢያ 130 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን እና፣ ፌደራል መንግሥቱ 130 ሚሊዮን ብር ለመስጠት ቃል መግባቱ ታውቋል። /ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/ … … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የኤሌክቶራል ኮሌጅ ሂደት

October 22, 2024 – VOA Amharic  ኤሌክቶራል ኮሌጅ (Electoral College) የአሜሪካ ዜጎች ፕሬዝዳንታቸውን የሚመርጡበት ሂደት ነው። በስተመጨረሻ አሸናፊውን የሚመስኑት የኤሌክቶራል ኮሌጅ አባላት ናቸው።  ሂደቱ እንዴት እንደሚካሄድ ከተያያዘው መግለጫ ይከታተሉ።  … … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

በመርካቶ ሸማ ተራ አከባቢ የእሳት አደጋ ተከሰተ

October 22, 2024 – VOA Amharic  በአዲስ አበባ በመርካቶ ሸማ ተራ አከባቢ ዛሬ ማምሻውን እሳት መከሰቱ ታውቋል። “በተከሰተው የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ለደረሰው ጉዳት እጅግ አዝነናል” ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ “የተከሰተውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር ከእሳት አደጋ  እና ስጋት መከላከል እንዲሁም  ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን ርብርብ እየተደረገ” መሆኑን  አመልክተዋል።  አደጋውን ለመቀ… … ሙሉውን ለማየት […]

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት በሁለት ቋሚ አባል ሀገራት መወከል እንደሚገባት ጉተሬዥ ተናገሩ

October 22, 2024 – VOA Amharic  የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ አዲስ አበባ በሰጡት መግለጫ፣ በፀጥታው ምክር ቤት መሻሻል እና በአፍሪካ ውክልና ላይ በተመድ አባላት መካከል መግባባት መኖሩን ገልጸዋል። ዓለም አቀፉ የገንዘብ ሥርዓትም አፍሪካን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ መሻሻል እንዳለበት ከስምምነት መደረሱን ዋና ጸሐፊው ጠቁመዋል፡፡ ዋና ጸሐፊው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋራ በመሆን እድሳት… … ሙሉውን […]

በአማራ ክልል እየተፈጸመ ያለው የመብት ጥሰት እንዲመረመር የዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ጠየቀ

ዜና በአማራ ክልል እየተፈጸመ ያለው የመብት ጥሰት እንዲመረመር የዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ጠየቀ ሲሳይ ሳህሉ ቀን: October 20, 2024 ከተጀመረ ከአንድ ዓመት በላይ ባስቆጠረውና በአማራ ክልል በሁለት ተፋላሚ ኃይሎች መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት እየደረሰ ያለውን የከፋ የመብት ጥሰት፣ አገር በቀልና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች ምርመራ እንዲያደርጉበት በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ጠየቀ፡፡ ፎረሙ በጦርነት እየታመሰ […]

ኬንያ የቱርክ ስደተኞችን ያለፈቃዳቸው ወደ አገራቸው መመለሷ እንዳሳሰበው የመንግሥታቱ ድርጅት ገለጸ

ከ 9 ሰአት በፊት የኬንያ መንግሥት በመዲናዋ ናይሮቢ ይኖሩ የነበሩ አራት ጥገኝነት ጠያቂ ቱርካውያንን በአስገዳጅ ሁኔታ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ አድርጓል። ይህ ድርጊትም ሰዎችን ነጻነታቸው እና ሕይወታቸው አደጋ ላይ የሚወድቅበት በመሆኑ ሁኔታው እንዳሳሰበው የመንግሥታቱ ድርጅት አስታውቋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽን ከኬንያ ወደ ቱርክ የተመለሱት ስደተኞች ሁኔታ እንዳሳሰበው ገልጿል። የመንግሥታቱ ድርጅት ይህንን መግለጫ ያወጣው በኬንያ […]

ምርጫ ቦርድ የፓርቲዎችን የዕውቅና ምስክር ወረቀት ክፍያ ከ200 ብር ወደ 30 ሺህ ብር አሳደገ

ከ 6 ሰአት በፊት አዲስ የሚመሠረቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተመዝግበው “የሙሉ ዕውቅና” የምስክር ወረቀት ለማግኘት ሲጠየቁ የነበረው የ200 ብር ክፍያ ወደ 30 ሺህ ብር አደገ። በአዲሱ የምርጫ ቦርድ የክፍያ ተመን መሠረት አዲስ የሚቋቋሙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጊዜያዊ እና ሙሉ የዕውቅና ምስክር ወረቀቶችን ለማግኘት በድምሩ 45 ሺህ ብር መክፈል ይጠበቅባቸዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመመዝገብ እንዲሁም […]