በሩሲያው ተቃዋሚ ግድያ የተፈረደበት እስረኛ ወደ ዩክሬን እንዲዘምት ተለቀቀ

August 11, 2024 – VOA Amharic … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ Level up, hit the battleUnique game modes to discoverHero Wars| SponsoredPlay Now Unsold Laptops Are Selling For Dirt Cheap (See Prices)Discover Discounts & Savings On Unsold Laptops With These Popular Searches.Best Searches| SponsoredLearn More Top Doctor: If You Eat Eggs Every Day, This […]

የትራምፕ ቡድን የውስጥ መረጃዬ በኢራን ተጠልፎብኛል አለ

ከ 5 ሰአት በፊት የዶናልድ ትራምፕ ምርጫ ቅስቀሳ ቡድን የውስጥ የመረጃ ቅብብሎሼ በኢራን የመረጃ ሞጭላፊዎች የጠለፋ ሙከራ ሳይደረግበት አልቀረም አለ። ፖለቲኮ የተሰኘው የአሜሪካ የዜና ድረገጽ በበኩሉ የትራምፕ ቡድን ያቀረበውን አቤቡታ ዐይነት ተከታታይ ኢሜሎች ምናልባትም ከዚሁ ጠላፊ ቡድን ሲደርሱት እንደነበር ይፋ አድርጓል። ፖለቲኮ ይደርሱት የነበሩት ኤሌክትሮኒክ ደብዳቤዎች በተለይ ስለ ኦሃዮ የሕዝብ እንደራሴ ጄዲ ቫንስ ዝርዝር መረጃ የያዙ ናቸው። […]

ጠንካራ ፉክክር በታየበት የሴቶች ማራቶን ትዕግስት አሰፋ ለኢትዮጵያ ብር አስገኘች

ከ 6 ሰአት በፊት በፓሪስ ኦሊምፒክ መዝጊያ ዕለት በተካሄደው እና ጠንካራ ፉክክር በታየበት የሴቶች ማራቶን ትዕግስት አሰፋ ለኢትዮጵያ ብር አስገኘች። ለኔዘርላንድስ የምትሮጠው ሲፈን ሐሰን የኦሊምፒክ ሪከርድን በማሻሻል ወርቁን የግሏ አድርጋለች። በውድድሩ ማብቂያ ላይ ትዕግስት እና ሲፈን ጠንካራ ፉክክር አድርገው ሲፈን 2፡22፡55 በሆነ ሰዓት የኦሊምፒክ ክብረ ወሰንን በማሻሻል ጭምር አሸንፋለች። እስከ ውድድሩ ፍጻሜ ድረስ ትዕግስት እና […]

“የወርቅ ሜዳልያው የራሴ ብቻ ሳይሆን የሲሳይም አደራ ነው” ታምራት ቶላ

ከ 9 ሰአት በፊት ሰኔ መጨረሻ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በፓሪስ ኦሊምፒክ የሚወዳደሩ አትሌቶችን የመጨረሻ ዝርዝር ይፋ ሲያደርግ የታምራት ቶላ ስም በማራቶን በተጠባባቂነት ነበር የተያዘው። ስለዚህም በኦሊምፒክ ላይ የመሳተፉ ነገር እርግጠኛ አልነበረም። ሲሳይ ለማ፣ ዴሬሳ ገለታ እና ቀነኒሳ በቀለ በወንዶች ማራቶን በኦሊምፒክ ኢትዮጵያን ወክለው ለመወዳደር የተመረጡ ሲሆን፣ ታምራት ቶላ ደግሞ አንዳች ነገር ተፈጥሮ ክፍተት ቢፈጠር […]

ህወሓት በምርጫ ቦርድ ‘በልዩ ሁኔታ’ መመዝገቡን እንደማይቀበለው አስታወቀ

ከ 8 ሰአት በፊት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የቀድሞው ሕጋዊ ሰውነቱ እንዲመለስለት እንጂ በምርጫ ቦርድ ዳግም መመዝገብን እንደማይቀበል አስታወቀ። ፓርቲው ይህን ያለው ከቀናት በፊት ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቀድሞው ሕጋዊ ሰውነቱ እንዲመለስ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ በቦርዱ በልዩ ሁኔታ መመዝገቡ ብቻ ይፋ ከተደረገ በኋላ ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነሐሴ 3/2016 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ በዚህ […]

በኦሊምፒክ ሜዳልያ ማሸነፍ ዋጋው ስንት ነው? በኦሊምፒክ ማሸነፍስ ገንዘብ ያስገኛል?

ከ 9 ሰአት በፊት ዘመናዊው ኦሊምፒክ እአአ በ1896 በአቴንስ ሲጀመር ምንም ዓይነት ፕሮፌሽናል ስፖርተኞች ወይም የገንዘብ ሽልማት የማይፈቀድበት አማተር ውድድር ነበር። በፓሪስ ኦሊምፒክ ግን በዓመት በመቶ ሚሊዮን ዶላሮችን ከሚያፍሱት እጅግ ባለጸጋ ከሆኑት ስፖርተኞች ጀምሮ በስፖርቱ ለመቀጠል እስከሚንገዳገዱት ድረስ የሚሳተፉበት ሆኗል። ስፖርተኞቹ ከተለያዩ ምንጮች ገንዘብ ማግኘት ይችላሉ። ከስፖንሰሮች፣ ከየአገሮቻቸው ከሚያገኙት የገንዘብ ሽልማቶች እና ለመጀመሪያ ጊዜም ከኦሊምፒኩ […]

በአገራቸው ያሉ ሁኔታዎችን በመሸሽ ለውድድር በሄዱባቸው አገራት ጥገኝነት የሚጠይቁ አትሌቶች

ከ 9 ሰአት በፊት “በቶኪዮ ኦሊምፒክ የቤላሩስ ብሔራዊ ቡድን አባል ነበርኩ” ትላለች አትሌት ክሪስቲና ሲማኑስካያ። “አሁን ፓሪስ ላይ ደግሞ ፖላንድን እወክላለሁ” ብላለች። እአአ በ2021 የ27 ዓመቷ አትሌት በትውልድ አገሯ ሊደርስባት የሚችለውን እስራት በመፍራት በቶኪዮ ኦሊምፒክ ጥገኝነት ከጠየቀች በኋላ ዓለም አቀፍ ትኩረትን አገኘች። የቤላሩስ ባለሥልጣናት ያለፈቃድዋ በመጨረሻ ደቂቃ ላይ በ400 ሜትር የዱላ ቅብብል እንድትሳተፍ ማድረጋቸውን ተከትሎ […]

የሂትለርን ዘመን ጥሶ ለዘመናት መሻገር የቻለው፤ የበርሊን ኦሊምፒክስ የወለደው ጓደኝነት

ከ 9 ሰአት በፊት እርግጥ ነው በኦሊምፒክ ታሪክ ውስጥ ከሚነሱ እጅግ አስደናቂ ታሪኮች አንዱ ተደርጎ ይነሳል። ነገር ግን ለጀርመናዊው ረዥም ርቀት ዝላይ አትሌት ሉዝ ሎንግ ሁኔታው አስፈሪ ሊሆን ይችል ነበር። ጄሲ ኦውንስ በ1936 ኦሊምፒክ 8 ሜትር ዘሎ ወርቁን ሲወስድ ትልቁ ተቀናቃኙ የሚባለው ግለሰብ አሸዋውን ተሻግሮ ሄዶ አቅፎ እንኳን ደስ አለህ አለው። በወቅቱ ጀርመንን ያስተዳድር የነበረው […]

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ወታደሮቻቸው ወደ ሩሲያ ግዛት ዘልቀው እያጠቁ እንደሆነ ተናገሩ

ከ 8 ሰአት በፊት የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ሠራዊታቸው የሩሲያን ድንበር ተሻግሮ እያጠቃ መሆኑን ለመጀመርያ ጊዜ አመኑ። ፕሬዝዳንቱ ትናንት ቅዳሜ ለሕዝባቸው ባደረጉት ንግግር፤ “ሠራዊታችን ጦርነቱን ወደ ወራሪዋ አገር ግዛት እየወሰደው ነው” ብለዋል። የዩክሬን ሠራዊት ድንገተኛ ጥቃት የከፈተበት የሩሲያ ግዛት ኩርስክ የሚባለው ክልል ነው። የዩክሬን ኃይል መጠነ ሰፊ ጥቃት ወደ ሩሲያ መሰንዘር የጀመረው ከአምስት ቀናት በፊት […]